ራሳቸውን ከመንግሥት ስለላ መጠበቅ ለሚፈልጉ ድርጅቶች የሚያገለግሉ ግብዓቶች።
የሚያስተዳድሩት ተቋም የሚሠራው ሥራ በአገርዎ ወይም በሌሎች አገራት መንግሥታት በድብቅ ክትትል ሊደረግበት የሚችል ከኾነ ግንኙነትዎን ማመስጠር የሚችሉበትን መንገድ ማሰብ ይኖርብዎታል። ይህ መመሪያም ተቋማዊ የኾነ ስለላን ለመከላከል በሚያስቡበት ወቅት እንዴት ማቀድ እንዳለብዎት የሚያሳይ ነው።
የሚያስተዳድሩት ተቋም የሚሠራው ሥራ በአገርዎ ወይም በሌሎች አገራት መንግሥታት በድብቅ ክትትል ሊደረግበት የሚችል ከኾነ ግንኙነትዎን ማመስጠር የሚችሉበትን መንገድ ማሰብ ይኖርብዎታል። ይህ መመሪያም ተቋማዊ የኾነ ስለላን ለመከላከል በሚያስቡበት ወቅት እንዴት ማቀድ እንዳለብዎት የሚያሳይ ነው።
ጠቅላላ ውሂብዎን ሁልጊዜ ከሁሉም ሰው ለመጠበቅ መሞከር እጅግ አድካሚ እና የማይቻል ነው፡፡ ነገር ግን መፍራት የለብዎትም! ደኅንነት በጥንቃቄ በሚነደፍ ዕድቅ የሚመራ እና ለእርሶ ትክክለኛ የሆነውን እየተጠቀሙ የሚያዳብሩት ሂደት ነው፡፡ ደኅንነት ማለት እንዳንድ መሳሪያዎች መጠቀም ወይም ሶፍትዌር ማውረድ ማለት አይደለም፡፡ እርስዎ በተለየ የተጋረጠብዎን የደኅንነት ከመረዳት እና እነዚህን ስጋቶች እንዴት መመከት እንደሚቻል ከማወቅ የሚጀምር ነው፡፡.
በኮምፒተር ደኅንነት ስጋት የሚባለው ውሂብዎን ከጥቃት ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት የማሳነስ አቅም ያለው ክስተት ነው፡፡ ምን መከላከል እንደሚፈልጉ እና ከማን መከላከል እንደሚፈልጉ በመለየት ያጋጠመዎትን ስጋት መጋፈጥ ይችላሉ፡፡ ይህ ሂደት “የስጋት ሞዴል” ይባላል፡፡
ይህ መመሪያ የስጋት ሞዴልዎን እንዴት መቅረጽ እንዳለብዎ ወይም የዲጂታል መረጃዎችዎ የሚያጋጥማቸውን አደጋ እንዴት መገምገም እንደሚችሉ እና የትኞቹ መፍትሔዎች ለእርስዎ የተሻለ እንደሆኑ ያስተምራል፡፡
የስጋት ሞዴል እንዴት ያለ ነገር ነው? ቤትዎ እና ንብረትዎን እንዳይዘረፉ ይፈልጋሉ እንበል፡፡ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቀዎች ይጠይቃሉ፡
በቤቴ ውስጥ ያለ ጥበቃ የሚያስፈልገው ነገር ምንድን ነው?
ከማን ነው ራሴን መከላከል የምፈልገው?
መከላከል ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
ይሄንን መከላከል ባልችል ሊደርስብኝ የሚችለው አደጋ መጠኑ ምን ያህል ነው?
ሊደርስብኝ ከሚችል አደጋ ራሴን ለመከላከል ምን ያህል ርቀት ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ?
እነዚህን ጥያቄዎች ለራስዎ ካቀረቡ በኋላ ማድረግ የሚችሉትን ነገር ለመገምገም ዝግጁ ነዎት፡፡ ንብረትዎችዎ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ሆነው ነገር ግን የመዘረፍ እድላቸው ዝቅተኛ ከሆነ ካዝና በመግዛት ብዙ ገንዘብ ማውጣት አይኖርብዎት ይሆናል፡፡ ነገር ግን አደጋው ከፍተኛ ከሆነ ገበያ ላይ የሚገኝ ምርጥ ካዝና መግዛት ይኖርብዎታልም፤ ደኅንነት ስርዓት ለመጨመርን ማሰብ ይኖርብዎታል፡፡
የደኅንነት ስጋት ሞዴል መገንባት የሚያጋጥምዎን የተለየ አደጋ ፣ ንብረትዎችዎን፣ ባለጋራዎችዎን፣ የባላጋራዎችዎን አቅም እና የተጋረጠብዎ አደጋ የመፈጸም ዕድል ምን ያህል እንደሆነ እንዲገነዘቡ ይረዳዎታል፡፡
የስጋት ሞዴል ዋጋ በሚሰጧቸው ነገሮች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ነገሮች እንዲለዩ እና ከማን መጠበቅ እንደሚገባዎ እንዲያውቁ ይረዳዎታል፡፡ የስጋት ሞዴልዎን ሲቀርጹ ለእነዚህ አምስት ጥያቄዎች መልስ ያዘጋጁ:
እያንዳንዱን ጥያቄ በዝርዝር እንመልከት፡፡
ንብረት ዋጋ የሚሰጡት እና እንዳይጠፋብዎ የሚጠብቁት ነገር ነው፡፡ ስለ ዲጂታል ደህንነት በምንነጋገርበት ወቅት እሴት ወይም ንብረት የምንለው ነገር መረጃን እንደኾነ መታወቅ ይኖርበታል። ለምሳሌ የኢሜል አድራሻዎ፣ የወዳጆችዎ ዝርዝር፣ የፈጣን መልዕክት ልውውጥዎ፣ ቦታዎች እና የተለያዩ ሰነድዎችዎ በሙሉ ንብረትዎችዎ ናቸው። በተጨማሪም ኮምፒውተርዎ፣ ስልክዎ እና የመሳሰሉትም ንብረትዎችዎ ናቸው።
የንብረትዎን ዝርዝር፣ ውሂብዎ የት እንደተቀመጠ፣ እነማን መጠቀም እንደሚችሉ እና ሌሎች እንዳይጠቀሙት የሚከለክላቸው ምን እንደኾነ ይጻፉ።.
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ማን እርስዎን አና መረጃዎችዎን ዒላማ ውስጥ ማስገባት ይፈልጋል የሚለውን ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ ግለሰብ ወይም ሌላ አካል ንብረቶችዎ ላይ የሚጥል ሁሉ “ባለጋራዎ” ነው፡፡ አለቃዎ፣ የቀድሞ ባልደረባዎ፣ የቢዝነስ ተፎካካሪዎ፣ የሀገርዎ መንግስት ወይም በህዝባዊ ትይይዝት ላይ ያለ የመረጃ ጠላፊ አቅም ያላቸው የባለጋራዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡
የእርስዎን ውሂብ ወይም የግንኙነት መረጃዎን ማግኘት የሚፈልግ ማን ሊኾን እንደሚችል ጥርጣሬ ውስጥ በማስገባት የባለጋራዎችዎን ዝርዝር ያውጡ። እነርሱም ግለሰቦች፣ የመንግስት አካላት ወይም ተቋማት ሊኾኑ ይችላሉ፡፡
የስጋት ሞዴልዎን ካዘጋጁ በኋላ እንደባለጋራዎችዎ ማንነት፣ በተወሰኑ ሁኔታዎች ውስጥ ይህንን ዝርዝር ማስወገድ ይኖርብዎ ይሆናል፡፡
ባለጋራዎ በመረጃዎ ላይ ጉዳት ወይም አደጋ ሊያደርስ የሚችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ ግንኙነትዎ በኔትወርክ በሚተላለፍበት ወቅት ባለጋራዎ የግንኙነትዎን ይዘት ሊያዳምጥ ወይም ሊያነብ፤ ወይም የግል ውሂብዎን ሊሰረዝ ወይም ሊያበላሽ ይችላል።
ባለጋራዎች የሚያደርሱት ጥቃት የተለያየ እንደኾነ ሁሉ ጥቃት ለመሰንዘር የሚነሱበት አላማም እንዲሁ የተለያየ ነው። ለምሳሌ ፖሊስ ወይም የተለያዩ የሕግ አስፈጻሚ አካላት የፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያሳይ ቪዲዮ ቢኖርዎት መንግስት የዚህን ቪዲዮ ስርጭት ለመቀነስ በማሰብ ቪዲዮውን ለማጥፋት ወይም ተደራሽነቱን ለመቀነስ ሊሞክር ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካዊ ባላንጣዎችዎ እንዲህ ዓይነቱን ድብቅ መረጃ ያለ እርስዎ ዕውቀት በእጃቸው ማስገባት እና ማተም ይፈልጉ ይሆናል።
የስጋት ሞዴል ባለጋራዎ ከንብረትዎ በአንዱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ቢሳካለት የሚያስከትለውን ጉዳት መጠን በመረዳት ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ ይህን ለማድረግ የባለጋራዎን አቀም ከግምት ውሰጥ ማስገባት ይገባል፡፡ ለምሳሌ የስልክ አገልግሎት አቅራቢ በስልክዎ የሚያደርጉትን ግንኙነት በሙሉ ማግኘት ስለሚችል የራስዎን መረጃ በመጠቀም ሊጎዳዎት ይችላል። ክፍት የኾኑ የዋይፋይ ኔትወርኮችን በሚጠቀሙበት ወቅት መረጃ ጠላፊዎች ያልተመሰጠሩ ግንኙነትዎትን ሊያገኙ ይችላሉ። መንግስታት ደግሞ የበለጠ አቅም ይኖራቸዋል፡፡
በመኾኑም ባለጋራዎ በግል ውሂብዎ ማድረግ የሚፈልገው ምን ሊኾን እንደሚችል ይዘርዝሩ።
አደጋ የሚባለው የደኅንነት ስጋት የተወሰነ ንብረትዎን የምር መጠቃት አዝማሚያ ነው፡፡ ይህም ከአቅም ጋር ጎን ለጎን አብሮ የሚሄድ ነው። ምንም እንኳን የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢ የእርስዎን ውሂብ ሙሉ በሙሉ የማግኘት አቅም ቢኖረውም የእርስዎን መልካም ስም ለማጉደፍ ኾን ብለው የግል ውሂብዎን በአደባባይ ላይ የመለጠፍ አዝማሚያው አናሳ ነው።
በስጋት እና በአደጋው የመከሰት አዝማሚያ መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ጠቃሚ ነው። ስጋት ሊከሰት የሚችለው ጉዳት ሲኾን አደጋው የመከሰቱ አዝማሚያ ወይም ሪስክ የሚባለው ደግሞ ይህ ስጋት ሊከሰት የሚችልበት አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል ነው። ለምሳሌ የህንጻ መደርመስ ስጋት ቢኖር ይህ ስጋት ግን ለስምጥ ሸለቆ ቅርብ በሆኑ ከተሞች ሊከሰት የሚችልበት አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል በርቀት ከሚገኙት በጣም ከፍ ያለ ነው።
አደጋው የመከሰቱ አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል ትንተናን ማካሄድ ግለሰባዊ እና በግለሰቡ አመለካከት የተቃኘ ሂደት ነው። ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ስጋትን የሚያይበት እና ቅድሚያ የሚሰጥበት መንገድ ተመሳሳይ አይደለም። በርካታ ሰዎች የተወሰኑ ስጋቶች የመከሰት አዝማሚያቸው ምንም ይሁን ምን ለመጋፈጥ ፈቃደኛ አይደሉም። ምክንያቱም የስጋቱ መኖር ብቻ ከሚያስፈልጋቸው ዋጋ ጋር ሲወዳደር ሚዛን አይደፋም ብለው ስለሚያምኑ ነው። በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ ግለሰቦች አደጋው የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ቢኾንም እንኳን ስጋቱን እንደ ችግር አያዩትም።
በከፍተኛ ትኩረት ሊመለከቷቸው የሚገቡ ስጋቶችዎን በዝርዝር ይጻፉ፤ እንደገናም የመከሰት ዕድላቸው አናሳ የሆኑ ወይም ጉዳት የለሽ በመሆናቸው (ወይም ለመከላከል አዳጋች የሆኑትን) የሚያስጨንቅዎን ያስፍሩ፡፡
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የጉዳት አዝማሚያ ትንታኔ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች አይኖሩትም ወይም ስጋቶችን በተመሳሳይ መንገድ አይመለከትም፡፡
ለምሳሌ በብሔራዊ ደኅነነት ጉዳይ ውስጥ የሚገኝ ደንበኛውን የሚወክል የህግ አማካሪ/ጠበቃ ከአንድ ለልጅዋ አስቂኝ የድመት ቪዲዮዎችን ከምትልክ እናት በበለጠ የተመሰጠሩ ኢሜሎችን ለመጠቀም እና ግንኙነቶቹን ለመጠበቅ ብዙ ርቀት ይጓዛል፡፡
ልዩ ስጋቶችዎ የሚያደርሱብዎን ጉዳት ለመቀነስ ያልዎትን አማራጮች በሙሉ ይዘርዝሩ፤ የገንዘብ እጥረት፣ የቴክኒክ ጉድለት ወይም ማኀበራዊ እንቅፋት ካለብዎም ያስፍሯቸው፡፡
የስጋት ሞዴልዎ እርስዎ ያሉበት ሁኔታ ሲቀየር አብሮ እንደሚቀየር በአእምሮዎ ይመዝግቡ፡፡ በዚህ ምክንያት በየጊዜው የስጋት ሞዴልን መገምገም ጥሩ ልምድ ነው፡፡
በራስዎ ልዩ ሆኔታ ላይ የተመሰረተ የራስዎን የስጋት ሞዴል ይፍጠሩ፡፡ለወደፊት በቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ያድርጉ፡፡ ይህም የስጋት ሞዴልዎን እንዲከልሱ እና አሁን ለሚገኙበት ሁኔታ ተገቢ መሆኑን እንዲፈትሹ ይረዳዎታል፡፡
የቴሌኮሚኒኬሽን ኔትወርኮች እና ኢንተርኔት ከሌሎች ሰዎች ጋር የምናደርገውን ግንኙነት ከምንጊዜውም በተሻለ ቀላል እንዲኾን ቢያደርጉም ክትትል ይበልጥ እንዲበረታ አድርገዋል። ግላዊነትዎን ለመጠበቅ ተጨማሪ እርምጃዎችን ካልወሰዱ እያንዳንዱ የስልክ ጥሪ፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክቾች፣ ኢሜል ምልልሶች፣ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎቶች፣ የድምጽ እና ቪዲዮ ጥሪዎች እና የማኀበራዊ ሚዲያ መልዕክቶች በሙሉ ለሌሎች አድማጮች ተጋላጭ ናቸው።
በአብዛኛውን እና እጅግ በጣም የተሻለው ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት የማድረጊያው መንገድ የመገናኛ አውታሮችን፣ ኮምፒውተሮችን ወይም ሰልኮችን ሳይጠቀሙ በአካል መገናኘት ነው። ነገር ግን ሁልጊዜም መገናኘት ስለማይቻል ቀጣዩ የተሻለ አማራጭ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን መጠቀም ነው፡፡
ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ መረጃው በዋናው መልእክት ላኪ (የመጀመሪያው "ጥግ") ሚስጥራዊ መልዕክት እንዲሆን መደረጉን እና የመጨረሻው ተቀባይ (ሁለተኛ "ጥግ") ብቻ ምስጢራዊው መልዕክት መፈታቱን ያረጋግጣል፡፡ ይህ ማለት ማንም ሰው በመሀል ገብቶ መስማት አይችልም፤ መልዕክትዎን አይፈታምም፡፡ ይህ የኢንተርኔት ካፌዎችን፣ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢው፣የሚጠቀሙት መካነ ድር እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያዎንም ይጨምራል፡፡ በተወሰነ መልኩ በተቃራኒው በስልክዎ ላይ ባለመተግበሪያ የተመለከቱት መልዕክት ወይም በኮምፕዩተርዎ የጎበኙት መካነ ድር ራሳቸው የመተግበሪያው ወይም የመካነ ድሩ ባለቤት ያዩታል ማለት አይደለም፡፡ የጥሩ ምስጠራ ሁነኛ መለያው ምስጠራውን የነደፉት እና የተገበሩት ሰዎች ራሳቸውን እንኳን ሰብረው መግባት የማይችሉት ነው፡፡
በኤስኤስዲ መካነ ድር ላይ መመሪያ የተዘጋጀላቸው መሣሪያዎች በሙሉ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን ይጠቀማሉ፡፡ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን ለማንኛውም አይነት ግንኙነትዎ የድምጽ እና ቪዲዮ ጥሪዎች፣ የጽሑፍ ውይይት እና ኢሜልን ጨምሮ መጠቀም ይችላሉ፡፡
(ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን ከንብርብር ማጓጓዣ ምስጠራ ጋር መምታታት የለብዎትም፡፡ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ መልዕክትዎን ከእርስዎ እስከ ተቀባዩ ድረስ ሲጠብቅ ንብርብር ማጓጓዣ ምስጠራ ደግሞ መልዕክትዎ ከእርስዎ መሣሪያ ወደ መተግበሪያው ሰርቨር ወይም መካነ ድር እና ከመተግበሪያው ሰርቨር ወደ መልዕክት ተቀባዩ መሣሪያ ሲጓጓዝ ብቻ ነው ጥበቃ የሚያደርገው፡፡ በመሀል የእርስዎ መልዕክት መለዋወጫ አገልግሎት አቅራቢ ወይም የጎበኙት መካነ ድር ወይም የተጠቀሙት መተግበሪያ ያልተመሰጠረ የመልዕክትዎን ቅጂ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
ከበስተጀርባ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ የሚሰራው እንዲህ ነው፡፡ ሁለት ግለሰቦች ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን ተጠቅመው መገናኘት ሲፈልጉ(ለምሳሌ አበበ እና ጫልቱ) እያንዳንዳቸው ቁልፎች የሚባሉትን ውሂቦች ማመንጨት አለባቸው። እነዚህ ቁልፎች ማንም ማንበብ የሚችለውን ውሂብ አዛማጅ ቁልፉን ከያዘው ሰው በቀር ማንም ማንበብ ወደማይችለው ውሂብ ይቀይራሉ፡፡ አበበ ለጫልቱ መልዕክትን ከመላኩ በፊት ጫልቱ ብቻ መልዕክቱን መፍታት
እንድትችል በእርሷ መልዕክቱን ያመሰጥረዋል። የተመሰጠረውን መልዕክትም በኢንተርኔት ይልከዋል። ማንኛውም ግለሰብ የአበበ እና የጫልቱን ግንኙነት ቢሰልል እና አበበ መልዕክቱን ለመላክ የተጠቀመውን አገልግሎት (ለምሳሌ የአበበን የኢሜል መለያ) መጠቀም ቢችል እንኳን ሰላዩ የሚያየው የተደበቀውን መልዕክት እንጂ የመልዕክቱን ይዘት አይደለም። ጫልቱ መልዕክቱን በምትቀበልበት ወቅት የራሷን ቁልፍ በመጠቀም ይዘቱን ወደ ሚነበብ መልዕክት መፍታት አለባት።
እንደ ጎግል ሐንጋውት ያሉ አንዳንድ አገልግሎቶች «ምስጠራን» ያስተዋውቃሉ፤ ነገር ግን የሚጠቀሙት በጎግል የተፈጠሩ እና ቁጥጥር ስር ያሉ ቁልፎችን ነው፡፡ ይህ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ አይደለም፡፡ ውይይቱ የምር ደኀንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን "ጥግ"ዎች ብቻ ማመስጠር እና መፍታት የሚችሉበት ቁልፎች ሲኖራቸው ነው፡፡ የሚጠቀሙት አገልግሎት ቁልፎችን የሚቆጣጠር ከሆነ ያ አገልግሎት የማጓጓዣ ንብርብር-ምስጠራ ነው፡፡
ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ማለት ተጠቃሚዎች ቁልፎቻቸውን በሚስጢር የሚይዙበት ነው። በሌላ አገላለጽ ለመመስጠር እና ለመፍታት የሚያገለግሉት ቁልፎችን ትክክለኛ ሰዎችንብረታቸውን ሲያደርጓቸው ማለት ነው። ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን መጠቀም ቁልፎችን በትጋት የሚያረጋግጡ መተግበሪያዎችን መርጦ ከማውረድ ጀምሮ ሰፊ ጥረት ይጠይቃል።ነገር ግን ለተጠቃሚዎች ደኅንነታችን እጅግ በጣም የተሻለው ሁለቱም የሚጠቀሙበትን አገልግሎት ሰጪ አለማመን ነው።
ስለ ምስጠራ ምን አውቃለው? ፣ የምስጠራ መሠረታዊ ጽንሰ ሐሳቦች እና የተለያዩ የምስጠራ አይነቶች በሚሉት ክፍሎች ስለምስጠራ የበለጠ ይማሩ፡፡
በመደበኛም ሆነ ተንቀሳቃሽ ስልክ ሲደውሉ ንግግርዎ ከጥግ እስከ ጥግ አልተመሰጠረም፤ አጭር ጽሑፍ መልዕክት( SMS) ሲልኩ ደግሞ መልዕክቱ ጭራሽ አልተመሰጠረም፡፡ ሁለቱም መንግሥታት ወይም ስልኩ ላይ ስልጣን ያለው ማንኛውም ሰው መልዕክቶችዎን እንዲያነብ ወይም ጥሪዎችዎን እንዲመዘግብ ይፈቅዳሉ፡፡ እርስዎ የተጋላጭነት አዝማሚያ ትንተና መንግስትን የሚያጠቃልል ከሆነ በበይነመረብ የሚንቀሳቀሱ ምስጠራዎችን አማራጮችን ይመርጡ ይሆናል፡፡ እንደ ጉርሻ፣ በአብዛኛው ከእነዚህ የምስጠራ አማራጮች ቪዲዮም ያቀርባሉ፡፡
አንዳንድ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ የጽሑፍ፣ የድምጽ እና ምስል ጥሪዎችን የሚያቀርቡ አገልግሎቶች ወይም ሶፍትዌሮች ምሳሌዎች እነዚህን ይጨምራሉ፡-
አንዳንድ በነባሪነት ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ አገልግሎት የማይሰጡ አገልግሎቶች ምሳሌዎች እነዚህን ይጨምራሉ፡-
እንደ ፌስቡክ ሜሴንጀር እና ቴሌግራም ያሉ አገልግሎቶች ሆን ብለው ካበሯቸው ብቻ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ አግልግሎት ይሰጣሉ፡፡ እንደ አይሜሴጅ ያሉ ደግሞ ከጥግ እስከ ጥግ የተመሰጠረ አገልግሎት የሚሰጡት ሁሉቱም ተጠቃሚዎች ተመሳሳይ መሣሪያዎች ሲጠቀሙ ነው፡፡(አይሜሴጅ የሚሰራው ለአይፎን ተጠቃሚዎች ብቻ ነው፡፡)
ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ከመንግሥታት፣ ጠላፊዎች እና የመልዕክት አገልግሎቱን ከሚሰጠው ድርጅት ከራሱ እርስዎን ሊከላከል ይችላል። ነገር ግን እነዚያ ቡድኖች በሙሉ የምንጠቀምባቸው ሶፍትዌሮች ምሥጢራዊ ለውጦችን ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል። ። ስለዚህ ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን እንደሚጠቀሙ ቢናገሩም እንኳን ባልተመሰጠረ ወይም በተዳከመ ምስጠራ ሊልኩ ይችላሉ።
ኢኤፍኤፍን ጨምሮ ብዙ ቡድኖች የታወቁ አገልግሎት ሰጪዎች (ንብረትነቱ የፌስቡክ እንደሆነው ዋትስአፕ ወይም ሲግናል ያሉ) ቃል የገቡትን ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ የምር እየሰጡ መሆናቸውን ጊዜ ወስደው ይፈትሻሉ። ነገር ግን ለእነዚህ አደጋዎች አሳሳቢ ከሆኑ, በይፋ የሚታወቁ እና ምስጢራዊ ዘዴዎችን የሚጠቀሙ መሳሪያዎችን መጠቀም እና ከሚጠቀሙባቸው የትራንስፖርት ስርዓቶች ነጻ እንዲሆኑ የሚረዱ መሳሪያዎችን መጠቀም ይችላሉ። ኦቲአር እና ፒጂፒ ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህ ስርዓቶች ለመተግበር በተጠቃሚ ላይ የሚመረኮዙ ሲሆኑ በአብዛኛው ጊዜ ለተጠቃሚዎች ምቹ አይደሉም። እና ሁሉንም ዘመናዊ የላቁ የምስጠራ ቴክኖሎጂዎችን የማይጠቀሙ የቆዩ ፕሮቶኮሎች ናቸው።
ኦፍ ዘሪከርድ(ኦቲአር) ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራን የሚጠቀም ፕሮቶኮል ሲሆን የወዲያው መላላኪያ አገልግሎቶች ላይ ተደርቦ መስራት የሚችል ነው። ኦቲአርን ያካተቱ መሣሪያዎች እነዚህን ይጨምራሉ።
ፒጂፒ (ወይም ፐሪቲ ጉድ ፕራይቬሲ) ለኤሜይል ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ የሚሰጥ መደበኛ አገልግሎት ነው። ፒጂፒ ምስጠራን እንዴት መጫን እና መጠቀም እንደሚችሉ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት፡-
ፒጂፒ ኢሜይል እጅግ ተመራጭ የሚሆነው ቴክኒካዊ ልምድ ላላቸው እና ቴክኒካዊ ልምድ ካላቸው ሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር መልዕክት ለሚለዋወጡ እና የፒጂፒን ውስብስብነት እና ውስንነቶችን ለሚያውቁ ነው።
ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ የመስመር ላይ ግንኙነት ይዘትን ብቻ መደበቅ ይችላል። ነገር ግን ግንኙነት ማድረግዎን መደበቅ አይችልም። ይህ ማለት ዲበ ውሂብ አይጠብቅም ማለት ነው። ይህም የኢሜይል ርዕሰ ጉዳይ፣ ከማን ጋር ግንኙነት እያደረጉ እንዳሉ እና ግንኙነቱን መቼ እንደደረጉ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል። ያሉበት ስፍራ ራሱ ዲበ ውሂብ ነው።
የግንኙነትዎ ይዘት ሚስጥር በኾነበት ወቅት እንኳን ዲበ ውሂብ ወይም ስለ እርስዎ እጅግ በጣም ገላጭ መረጃን አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል።
የስልክ ጥሪዎ ዲበ ውሂብ አንዳንድ በጣም ሚስጥራዊ እና ስሱ የኾኑ መረጃዎችን አሳልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። ለምሳሌ፦
ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ለእርስዎ ደኅንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት ለማድረግ አስፈላጊ ከሆኑ ብዙ አገልግሎቶች ውስጥ አንዱ ነው። ከላይ እንደተገለፀው ከጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ኩባንያዎች እና መንግስታት መልዕክቶችዎ ጋር እንዳይደርሱ ለመከላከል ጥሩ ነው። ነገር ግን ለብዙ ሰዎች, ኩባንያዎች እና መንግስታት ትልቁ የሚባሉት አይደሉም። ስለዚህም ጥግ እስከ ጥግ ምስጠራ ምናልባት ከፍተኛው ቀዳሚ ጉዳያቸው ላይሆን ይችላል።
ለምሳሌ አንድ ሰው ስለ ትዳር አጋሩ፣ ወላጆቹ ወይም አሠሪው መሣሪያቸውን የማግኘት ዕድል ከተጨነቀ ፣ በአጭር ጊዜ “የሚጠፉ” መልዕክቶችን የመላክ አቅም መላኪያውን አገልግሎት ለመምረጥ የመወሰኛ ምክንያት ሊሆን ይችላል። ሌላ ሰው የስልክ ቁጥሩን ስለመስጠት ሊጨነቅ ይችላል፤ እናም የስልክ ቁጥር የሌለው "ቅጽል" መጠቀም መቻል አስፈላጊ ሊሆን ይችላል።
በአጠቃላይ ሲታይ የደኅንነት እና የግላዊነት ገጽታዎች ደኅንነቱ የተጠበቀ የመገናኛ ዘዴን ለመምረጥ ብቸኛ ምክንያቶች አይደሉም። ጓደኞችዎ እና እውቅያዎችዎ የማይጠቀሙት ከሆነ ከፍተኛ የደኅንነት ባህሪያት ያለው መተግበሪያ ዋጋ የለውም። በጣም ታዋቂ እና በስፋት ጥቅም ላይ የዋሉ መተግበሪያዎች በአገር እና በማህበረሰብ እጅግ የተለያየ ተደራሽነት ሊኖራቸው ይችላል። ደካማ የአገልግሎቱ ጥራት ወይም መተግበሪያውን ለመጠቀም ክፍያ ለተወሰኑ ሰዎች የማይመች ሊያደርግው ይችላል።
ከደኅንነቱ በተጠበቀ የመግባቢያ ዘዴ ውስጥ ምን ማግኘት እንደሚፈልጉ እና እንደሚያስፈልግዎ ይበልጥ በግልጽ በተረዱ ቁጥር ሰፊ፣ እርስ በርስ የሚጋጩ፣ አንዳንዴም ጊዜ ያለፈባቸው መረጃዎችን ለመለየት ይበልጥ ቀላል ይሆናል።
ስማርት ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም ታብሌት ካልዎት ሁልጊዜም የሚንቀሳቀሱት ከፍተኛ መጠን ያለው ውሂብ ተሸክመው ነው፡፡ የእርስዎ ማኀበራዊ ዕውቂያዎች፣ ግላዊ ግኝኙነቶች፣ የግል ሰነዶች፣ፎቶግራፎች(ምንም አልባትም ደርዘን እና በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ምስጢራዊ መረጃዎች) የመሳሰሉት በዲጂታል መሣሪያዎ ከሚያስቀምጧቸው ነገሮች ውስጥ የተወሰኑ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ በጣም ብዙ ውሂብ ስለምንይዝ እና ስለምናስቀምጥ ደኅንነቱን መጠበቅ ከባድ ነው፡፡ በቀላሉ ሊወሰድ የሚችል መሆኑ ደግሞ የበለጠ ከባድ ያደርገዋል፡፡
ውሂብዎ ድንበር ላይ ሊያዝ፣ መንገድ ላይ ሊሰረቅ ወይም ከቤትዎ ሊዘረፍ እና በጥቂት ሰከንዶች ኮፒ ሊደረግ ይችላል፡፡ እንደአለመታደል ሆኖ በይለፍ ቃል፣ በግላዊ መለያ ቁጥር ወይም በፊት ገጽ ቢቆለፍም እንኳን መሣሪያው ከተያዘ ውሂቡን መጠበቅ አይቻልም፡፡ በአንጻራዊንት እነዚህን ቁልፎች በቀላሉ በማለፍ ወሂብ በቀላሉ በሚነበብ መልኩ ከውስጥ ይገኛል፡፡ ባለጋራ ያለ የይለፍ ቃል የእርስዎን ውሂብ ለመቅዳት ወይም ለማጥናት የሚጠበቅበት ወደ መሣሪያው መግባት ብቻ ነው፡፡
ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት መሣሪያዎን በግዘፍ(ከነ ነፍሱ) የሚሰርቁ ሰዎች በቀላሉ እንዳያገኙት ማድረግ ይችላሉ፡፡የውሂብዎን ደኅንነት መጠበቅ የሚያችልዎት የተወሰኑ መንገዶችን እዚህ ያገኛሉ፡፡
ምስጠራ ከተጠቀሙ የእርስዎን የተመሰጠረ ውሂብ
ለመፍታት ባለጋራዎ የሚያስፈልገው መሣሪያዎ እና የይለፍ ቃልዎን ነው፡፡ ስለዚህ የተሰወኑ ሰነዶችን ማቀፊያዎችን ሳይሆን ውሂብዎን በሙሉ ማመስጠር እጅግ የበለጠ ደኅንነት ይሰጣል፡፡ አብዛኛዎቹ ስማርት ስልኮች እና ኮምፒውተሮች አማራጭ ይሰጣሉ፡፡
ለስማርት ስልኮች እና ታብሌቶች፡-
ለኮምፒውተር፡-
የቢትሎከር ኮድ የተዘጋ እና በባለቤትነት የተያዘ ነው፡፡ ይህም ማለት ምን ያህል አስተማማኝ እንደሆነ ለማወቅ ለውጭ ገምጋሚዎች ከባድ ነው፡፡ ቢትሎከርን ለመጠቀም ማይክሮሶፍት ያለ ምንም የተሸሸገ ተጋላጭነት ደኅንነቱ የተጠበቀ የማከማቻ ስርዓት ያቀርባል ብለው ማመን ይኖርብዎታል፡፡ በሌላ በኩል አስቀድመው ዊንዶውስ እየተጠቀሙ ከሆነ በተመሳሳይ ደረጃ ማይክሮሶፍትን ይተማመኑበታል ማለት ነው፡፡ በዊንዶውስ ወይም በቢትሎከር ውስጥ ባለ የጀርባ የመረጃ መረብ ስለላ ጥቅሙን ሊያውቁ ወይም ሊጠቀሙባቸው ከሚችሉ ባለጋራዎች ካለብዎት እንደ ጂኤንዩ/ሊኒክስ ወይም ቢኤስዲ የመሳሰሉ አማራጭ ክፍት ምንጭ ስርዓቶችን ለመጠቀም ግንዛቤ ውሰዱ፤ በተለይ የደኅንነት ጥቃቶች ለመቋቋም ተብለው የጠነከሩ እንደቴይልስ ወይም ኩብዝ ኦኤስ ያሉትን ይጠቀሙ፡፡ እንደ አማራጭም የሃርድ ድራይቭን ለማመስጠር ቬራክሪፕትየዲስክ ምስጠራ ሶፍትዌርን ለመጫን ያስቡ፡፡
ያስታውሱ፡- መሣሪያዎ ምስጠራውን በፈለገው ስም ይጥራው ጥሩ የሚሆነው እንደ የይለፍ ቃልዎ ጥሩነት ነው፡፡ አንድ ባለጋራ መሳሪያዎን በእጁ ካስገባ የይለፍ ቃልዎን ለማወቅ ረጅም ጊዜ አለው፡፡ ጠንካራና የማይረሳ የይለፍ ቃል ለመፍጠር ዳይስ እና የቃላት ዝርዝር መጠቀም ውጤታማ መንገድ ነው፡፡ እነዚህ ቃላት አንድ ላይ በመሆን "የይለፍ ሐረግ" ይባላሉ፡፡ "የይለፍ ሐረግ" ለተጨማሪ ደኅንነት ሲባል የረዘመ የይለፍ ቃል አይነት ነው፡፡ ለዲስክ ምስጠራ ቢያንስ ስድስት ቃላትን መምረጥ እንመክራለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ጠንካራ የይለፍ ቃል መፍጠር የሚለውን መመሪያችንን ይመልከቱ፡፡
ምንአልባት ለመልመድ እና በስማርት ስልክዎ ወይም ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎ ላይ ረጅም የይለፍ ሐረግን ለመተየብ አስቸጋሪ ሊሆንብዎ ይችላል፡፡ ስለዚህ ምንም እንኳን ምስጠራ በአዘቦት መግባትን ለመከልከል ጠቃሚ ቢሆንም እርስዎ መጠቀም ያለብዎት የምር ምስጢራዊ መረጃዎችን ባለጋራ እንዳይደርስበት ለመደበቅ ነው፤ አሊያ የበለጠ ደኅንነቱ ወደ በተጠበቀ መሣሪያ ይገልብጡት፡፡
ደኅንነቱ የተጠበቀ ከባቢን ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ በጣም ሲጎብዙ የይለፍ ቃሎችን፣ ልማዶችን እና ምናልባትም በዋናው ኮምፒተርዎ ወይም መሣሪያዎ ላይ የሚጠቀሙት ሶፍትዌሮች ሊለውጡ ይችላሉ፡፡ በጣም በሚሰንፉ ጊዜ ደግሞ ምስጢራዊ መረጃን እየረሱ እንደሆነ ወይም አደገኛ ልምዶችን እየተጠቀሙ ስለመሆኑ ዘወትር ቢያሰላስሉም ችግሮችን ሲያውቁ መፍትሄዎችን ላይተገብሩ ይችላሉ ምክንያቱም አንዳንድ ጊዜ ለመነጋገር የሚፈልጉት ሰዎች ደኀንነቱ ያልተጠበቀ የዲጂታል ልምዶችን አሏቸው፡፡ ለምሳሌ፣ የስራ ባልደረባዎች ከእነርሱ የኢሜይል የሚመጡ አባሪዎችን እንዲከፍቱላቸው ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ምንም እንኳን ባለጋራዎ የስራ ባልደረቦችዎ በመምሰል ሸርዌር ሊልክዎ ቢችልም፡፡
ታዲያ መፍትሔው ምንድን ነው? በጣም ጠቃሚ እና ዋጋ ያላቸው ውሂቦች እና ግንኙነቶችን የበለጠ ደኅንነቱ በተጠበቀ መሣሪያ ለማስቀመጥ ያስቡ፡፡ ደኅንነቱ የተጠበቀ መሣሪያዎን የሚስጥራዊ ውሂብዎን ዋና ኮፒ ማስቀመጫ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ይህንን መሣሪያ አስፈላጊ ሲሆን ብቻ ይጠቀሙበት፡፡ ሲጠቀሙም ከሌላው ጊዜ የተለየ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡ የተላኩ አባሪዎችዎን መክፈት ወይም ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ሶፍትዌር መጠቀም ሲፈልጉ በሌላ መሣሪያ ይጠቀሙ፡፡
ተጨማሪ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ ኮምፒውተር እርስዎ እንደሚያስቡት በጣም ውድ አማራጭ አይደለም፡፡ በአብዛኛው ጥቅም ላይ የማይውል እና ጥቂት ፕሮግራሞችን ብቻ የሚያስተዳድረው ኮምፒውተር በጣም ፈጣን ወይም አዲስ መሆን አያስፈልገውም፡፡ ለአንዳንድ ዘመናዊ ላፕቶፕ ወይም ስልክ በሚገዙበት ገንዘብ ሽራፊ ኔትቡክ(ትንሽ ላፕቶፐ) መግዛት ይችላሉ፡፡ አሮጌ ስልኮችም እንደ ቴይልስ ያሉ ሶፍትዌሮችን ከአዳዲስ ሞዴሎች ጋር አብሮ ከሚሰሩት የበለጠ የመስራት ዕድል ይኖራቸዋል፡፡ አንዳንድ አጠቃላይ ምክሮች በአብዛኛው ጊዜ እውነት ናቸው፡፡ መሣሪያ ወይም ሲገዙ የሶፍትዌር ዝማኔዎችን የመጨረሻው ያድርጉ፡፡ ዝማኔዎች ብዙውን ጊዜ ጥቃት በሚያስከትሉ የቆዩ ኮዶች ላይ ያሉ የደኅንነት ችግሮችን ሊጠግኑ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ የቆዩ ስርዓተ ክወናዎች ከአሁን በኋላ ሊሰሩ አይችሉም፤ ለደህንነት ማዘመኛዎችም ጭምር፡፡
አንድ ደኀንነቱ የተጠበቀ አንድ መሣሪያ ጠቃሚ እና ምስጢራዊ መረጃዎች ከባለጋራ ለመጠበቅ ቢረዳም አንድ የታወቀ የጥቃት ዒላማንም ይፈጥራል፡፡ መሣሪያው ከተበላሸ በአንድ ቅጂ ብቻ ያልዎትን ውሂብ የማጣትም አደጋ አለ፡፡ እርስዎ ውሂብዎን በሙሉ ማጣትዎ ባለጋራዎን የሚጠቅም ከሆነ ምንም እንኳን ደኀንነቱ የተጠበቀ ቢሆንም አንድ ቦታ ብቻ አያስቀምጡ፡፡ ቅጂውን አመስጥረው ሌላ ቦታ ያስቀምጡ፡፡
ስለ ደኀንነቱ የተጠበቀ መሣሪያ የሀሳብ መለያየት ደኅንነቱ ያልተጠበቀ መሣሪያ እንዲኖር ያደርጋል፤ ይህ መሣሪያ ወደ ደኅንነቱ ያልተጠበቀ ወይም አደጋ ያለው ሥራ ሲከውኑ የሚጠቀሙት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል በርካታ ጋዜጠኞች እና ተሟጋቾች ሲጓዙ አንድ መሰረታዊ ኔትቡክ ይይዛሉ፡፡ ይህ ኮምፒዩተር ምንም አይነት ሰነዶች ወይም የተለመደው ዕውቂያ ወይም የኢሜይል መረጃ የለውም ስለዚህ ቢቀማ ወይም ቢቃኝ የሚደርሰው ኪሳራ ትንሽ ነው፡፡ ለሞባይል ስልኮች ተመሳሳይ ስልት ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ስማርትፎን የሚጠቀሙ ከሆነ ለተወሰኑ ጉዳዮች ሲጓዙ ርካሽ ተንቀሳቃሽ ስልክ መግዛትን ግምት ውስጥ ያስገቡ፡፡
በቅርቡ የአሜሪካንን ድንበር ማቋረጥ ያስባሉ? መንግሥት ያለ ምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወደ አሜሪካ የሚጓዙ መንገደኛች አለም አቀፍ አውሮጵላን ጣቢያዎችን ጨምሮ በማንኛውም የአሜሪካ ድንበር ሲደርሱ የመፈተሽ ስልጣን እንዳለው ያውቃሉ? ይህ መንግስት በዝውውር ላይ ያሉ ነገሮችን የመቆጣጣር ተለምዷዊ ስልጣኑ አካል ነው። (ያስታውሱ ምንም እንኳ ሕጉ መንገደኞች ከአሜሪካ ወደ ሌላ አገር ሲሻገሩም በመውጫዎች ላይ እንደሚፈተሹ ቢደነግግም መንገደኞች ግን በብዛት ሲፈተሹ አይታይም።)
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በጥልቀት ለመረዳት ከፈለጉ የኢኤፍኤፍ መመሪያ የኾነውን ዲጂታል ግላዊነት በአሜሪካ ድንበር፣ በመሣሪያዎ ላይ ያለው ውሂብ መጠበቅ ይመልከቱ።
ድንበር ጠባቂዎች ዲጂታል ውሂብዎን ሊጠይቁዎ ይችላሉ፡፡ የግል የስጋት ትንተና ምክንያቶች ይመልከቱ፡፡ ምርጫዎን የስደት ሁኔታዎ፣ የጉዞ ታሪክዎ፣ ውሂብዎ የየዛቸው መረጃዎች አደገኛነት፣ እና ሌሎች ሁኔታዎች ምርጫዎን ሊወስኑ ይችላሉ፡፡
ያልተለመዱ ጥንቃቄዎች አንዲጠራጠሩ ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይገንዘቡ፡፡
እነዚህን ጥቆማዎች አንደሚያስታውሱ እርግጠኛ አይደሉምን? የኢኤፍኤፍን በጉዞ ላይ ሳሉ እንዲታተም፣ እንዲታጠፍ እና ኪስዎ ላይ እንዲገባ ሆኖ የተዘጋጀውን የድንበር ላይ ፍተሻ የኪስ መርጃ ጽሁፍ ይመልከቱ፡፡
ቪፒኤን በእንግሊዝኛ “ቨርቿል ፕራይቬት ኔትወርክ” ወይም ምናባዊ የግል አውታረመረብ ማለት ነው። በቪፒኤን አማካኝነት ኢንተርኔት ሲጠቀሙ የሚልኩት ውሂብ(ለምሳሌ ወደ ሰርቨር መካነ ድርን ለመጎብኘት ጥያቄ ሲያቀርቡ) ጥያቄው የቀረበው ከእርስዎ የግል አይኤስፒ(የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢ) ሳይሆን ከራሱ ከቨፒኤኑ ከራሱ የመነጨ ሆኖ ይታያል፡፡ ይህ የአይፒ አድራሻዎን ይከልላል፤ ይህም የአይፒ አድራሻዎ አጠቃላይ አካባቢዎን የሚያመላክት ስለሆነ እና እርስዎን ለመለየት ጥቅም ላይ ሊውል ስለሚችል አይፒዎን መከለሉ የእርስዎን ግላዊነት ለመጠበቅ የሚያስችል ጠቃሚ መሳሪያ ነው፡፡
በተግባር ቪፒኤን ማድረግ የሚችለው፡-
ስለ ቪፒኤንዎች አንዱ የተሳሳተ ግምት የሚያስፈልጉት ለዴስክቶፕ ኮምፒተሮች ብቻ ነው የሚል ነው። በስልክዎ ወደ ያልተለመደ ወይም የማይታወቁ የዋይፋይ ግንኙነቶች መግባት በኮምፒውተርዎ የማይታወቁ የዋይፋይ ግንኙነቶች የመግባትን ያህል አደገኛ ሊሆን ይችላል። በስልክዎ ላይ ቪፒኤን በመጠቀም ግንኙነትዎን በማመስጠር ከመስሪያ ቤትዎ፣ ከበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢ ወይም አይኤስፒ መጠበቅ ይችላሉ።
ስለቪፒኤንዎች ስንናገር አንድ ወጥ የሆነ ለሁሉም የሚሆን መፍትሔ የለም። ልክ እንደ ኢሜይል፣ ብዙ የቪፒኤን አገልግሎቶች ስላሉ ከእነርሱ መካከል ለእርስዎ በተሻለ ሁኔታ የሚሰራ አገልግሎት መምረጥ አለብዎት። በመረጡት ምርጫ ላይ በመመርኮዝ በመደበኛነት የደኅንነት ሁኔታቸውን በማያስተማምን አውታረመረብ ላይ ሊጠቀሙባቸው ይችላሉ። ይሄ ማለት ግን በራሱ በቪፒኤኑ ላይ እምነት ይጥላሉ ማለት አይደለም።
ይህ በሴንተር ፎር ዴሞክራሲ እና ቴክኖሎጂ የተዘጋጀው ይህ ማብራሪያ ቪፒኤንን ሲገልጸው ሌሎች የእርስዎን የውሂብ ትራፊክን እንዳይቆጣጠሩ ወይም ለውጦችን እንዳያሻሽሉ እንደዋሻ የሚያገለግል መተላለፊያ የሚፈጥር መሳሪያ ነው። በዋሻው ውስጥ ያለው ትራፊክ የተመሰጠረ ሲሆን ወደ እርስዎ ቪፒኤን ይላካል፤ ይህም በህዝባዊ ዋይፋይ ላይ የቪፒኤን ተጠቃሚውን ትራፊክ የሚያዘንፉ እንደ የበይነመረብ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ አይኤስፒስ ወይም ጠላፊዎች ወይም የመሳሰሉት ሶስተኛ ወገኖች በጣም ከባድ ያደርገዋል። ከዚያ ትራፊኩ ቪፒኤኑን ይተውና የተጠቃሚውን የአይፒ አድራሻ በመከለል ወደ ዋናው መዳረሻው ይሄዳል።ይህም ትራፊኩ ቪፒኤኑን ለቆ ሲሄድ በመከታተል ተጠቃሚው በአካል ያለበት ቦታን ለመለየት ከሚሞክር ከማንኛውም ሰው ለመሸሸግ ይረዳል።
ከመቀጠልዎ በፊት ቪፒኤንዎች ምን እንደሆኑ እና እንዴት እንደሚሰሩ የለበጠ ለመረዳት የሴንተር ፎር ዴሞክራሲ እና ቴክኖሎጂ ጽሑፍ ከጥግ እስከ ጥግ እንዲያነቡ እንመክራለን።
ቪፒኤን በጋራ ኔትወርክ ላይ ከሚደረጉ የኢንተርኔት ስለላዎች ሊከላከልልዎ ቢችልም እርስዎ ከሚጠቀሙትን የግል ኔትወርክ ግን ውሂብዎትን አይሸሽግም። የኮርፖሬት ቪፒኤን የሚጠቀሙ ከኾነ የኮርፖሬት ቪፒኤኑን የሚያስተዳድረው ማንኛውም ሰው የእርስዎን ውሂብ ማየት ይችላል። የንግድ ቪፒኤንን የሚጠቀሙ ከኾነ የንግድ ቪፒኤንኑን የሚያስተዳድረው ማንኛውም ሰው የእርስዎን ውሂብ ማየት ይችላል።
የማይታመን የቪፒኤን አገልግሎት ሆን ብሎ የግል መረጃን ወይም ሌላ ጠቃሚ መረጃዎችን ሊሰበስብ ይችላል።
የኮርፖሬት ወይም የንግድ ቪፒኤን አስተዳዳሪ የእነርሱን አውታረ መረብ ተጠቅመው የላኩትን ውሂብ ለመንግሥት ወይም ለሕግ አስፈጻሚ አካላት እንዲያስረክብ ተፅዕኖ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል። የቪፒኤን አገልግሎት አቅራቢው ውሂብዎን ለመንግሥት ወይም ለሕግ አስፈጻሚ አካላት በምን ዓይነት ኹኔታ ሊያስረክብ እንደሚችል የግላዊነት ፖሊሲውን ማየት ይኖርብዎታል።
የቪፒኤን አቅራቢው በየትኞቹ አገራት ውስጥ አገልግሎት እንደሚሰጥ ማወቅ ይኖርብዎታል። አገልግሎት አቅራቢው አገልግሎት በሚሰጥባቸው አገራት ሕግ ሊገዛ ይችላል። ይህም የእርስዎን ውሂብ በተመለከተ ከመንግሥት የሚቀርብ ጥያቄን እና ከአገራቱ ጋር የሚኖርን የሕግ ዕርዳታ ስምምነት ይጨምራል። ሕጎቹ ከሀገር ሀገር ይለያሉ።በአንዳንድ አጋጣሚዎች ሕጉ ባለስልጣናት መረጃዎችዎን እንዲሰበስቡ የሚፈቅደው ለእርስዎ ሳያሳውቁ ወይም ጥያቄው ተግባራዊ እንዳይኾን የመከላከል ዕድል ሳይሰጥዎ ነው። ምናልባትም የቪፒኤን አቅራቢው ስራውን ከሚያከናውንባቸው ሀገራት ጋር ሕጋዊ የትብብር ስምምነት ላላቸው ሀገራት የሚመጣ ህጋዊ ጥያቄዎች ተገዥ ሊሆን ይችላል።
አብዛኛዎቹ የንግድ ቪፒኤን አቅራቢዎች የክሬዲት ካርድ መረጃዎን ተጠቅመው እንዲከፍሉ ይፈልጋሉ። ነገር ግን እርስዎ ደግሞ ይህን መረጃዎን ለቪፒኤን አገልግሎት ሰጪው ማሳወቅ ላይፈልጉ ይችላሉ። የክሬዲት ካርድ መረጃዎን ለንግድ የቪፒኤን አገልግሎት አቅራቢ መስጠት ባይፈልጉ ቢትኮይን የሚቀበል የቪፒኤን አገልግሎት አቅራቢን መጠቀም ወይም ጊዜያዊ የክሬዲት ካርድ ቁጥሮችን መጠቀም ይችላሉ። በተጨማሪም ምንም እንኳን አማራጭ የክፍያ ስርዓት ቢጠቀሙም የቪፒኤን አቅራቢው አገልግሎታቸውን በሚጠቀሙበት ወቅት የእርስዎን የአይፒ አድራሻ ሊወስዱ እንደሚችሉ እና የእርስዎን ማንንነት ለማወቅ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ይገንዘቡ። የአይፒ አድራሻዎን ከቪፒኤን አቅራቢዎ መደበቅ ቢፈልጉ ከቪፒኤን ጋር ሲገናኙ ቶርን መጠቀም ይችላሉ።
ሁሉም ሰው ቪፒኤንን መጠቀም ተስፋ ሲያደርግ ፍላጎቱ የተለያየ ነው፤ የቪፒኤን አገልግሎት ጥራቱም ከአንድ አገልግሎት ሌላው ይለያል። ለእርስዎ ትክክለኛ የሆነውን ቪፒኤን ለመምረጥ ቪፒኤኖችን በሚቀጥሉት መስፈርቶች መመዘን ይችላሉ፡-
የቪፒኤን አቅራቢው ስለ ምርቱ ወይም አገልግሎቶቹ ብዙ ቃል ይገባሉ? ምን አልባትም የማንኛውም ተጠቃሚ የግንኙነት ውሂብ (ከዚህ በታች ያለውን የውሂብ ክምችት ይመልከቱ) አንመለከትም ሊሉ ይችላሉ፤ ወይም ውሂብዎን እንደማያጋሩ ወይም እንደማይሸጡ ኃላፊነት ይገቡ ይሆናል። ይህ የተገባ ቃል/ኃላፊነት ዋስትና አይሆንም፤ ስለዚህ እነዚህን የተገቡ ኃላፊነቶች በእርግጥ እንደሚተገበሩ ያረጋግጡ። ምንም እንኳን ቪፒኤን በቀጥታ ለሶስተኛ ወገን በቀጥታ ባይሸጥም ውሂብዎ እንዴት ገቢ እንደሚፈጠርባቸው ዝርዝር መረጃ ለመፈለግ ወደ የቪፒኤን አቅራቢዎች የግላዊነት መመሪያን በጥልቀት በመግባት ይመርምሩ።
ምንም እንኳን አንድ ቪፒኤን ውሂብዎን ባይሸጥ፣ በተወሰነ መልኩ አገልግሎት እየሰጠ መቆየት መቻል አለበት። የቪፒኤን አገልግሎቱን ካልሸጠው የንግድ ድርጅቱ እንዴት ገበያ ውስጥ መቆየት ይችላል? እርዳታዎች እንዲደረጉለት ይጠይቃል? የአገልግሎቱ የንግድ ሞዴል ምንድን ነው? አንዳንድ ቪፒኤኖዎች በ"ፍሪሚየም" ሞዴል ይሠራሉ። ማለትም ለመቀላቀል ነጻ ናቸው፤ ነገር ግን የተወሰኑ ውሂቦችን ካስተላለፉ በኋላ ያስከፍሉዎታል። በጀትዎ የተገደበ ከሆነ ይህን መረጃ ማወቅ ጠቃሚ ነው።
ከቪፒኤኑ ጋር የሚዛመዱ ሰዎች እና ድርጅቶች ምንነት ማጣራት ጠቃሚ ነው። በደኅንነት ባለሙያዎች ጸድቋል? ቪፒኤኑ ስለራሱ የተጻፈ የዜና ዘገባ አለው? ቪፒኤኑ በታወቁ የመረጃ ደኅንነት ማህበረሰብ ሰዎች ከተመሰረተ፣ የበለጠ እምነት የሚጣልበት ነው። ማንም ሰው የግል ዝናውን ማካተት የማይፈልግበትን ወይም ማንም የማያውቀው ኩባንያ፣ የሚያስተዳድረውን አገልግሎት ከሚያቀርብ ቪፒኤንን ተጠንቀቁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ውሂብን የማይሰበስብ አገልግሎት ያልሰበሰበውን ውሂብ ሊሸጥ አይችልም። የግላዊነት መመሪያውን ሲመለከቱ፣ ቪፒኤኑ እርግጥ የተጠቃሚን ውሂብ ይሰብስብ እንደሆነ ይመልከቱ። የተጠቃሚ ግንኙነት ውሂብ እንደማይሰበሰብ በግልጽ ካላስቀመጠ የመሆን እድል ነው ያለው። እንዲሁም መንግሥት የስልጣን ወሰን ውስጥ የሚገባ ከሆነ ውሂብ ሊጠይቅ ወይም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሊያወጣ ይችላል።
አንድ ኩባንያ የግንኙነት ውሂብን ለማግኘት እንደማይገባ ቃል ቢገባም ይሄ ሁልጊዜ የጥሩነት ዋስትና ላይሆን ይችላል። ቪፒኤኖች በመገናኛ ብዙሃን የተጠቀሱባቸውን አጋጣሚዎች እንዲመረምሩ እናበረታታለን። ምናልባት ደንበኞቻቸውን ሲያታልሉ ወይም ሲዋሹ መደበቅ ተይዘው ሊሆን ይችላል። ቀላል ፍለጋ መካሄድ ለረጅም ጊዜ የሚያስተማምን ነገር እንድናገኝ ሊረዳን ይችላል።
ዋናው መሥሪያ ቤቱ ያለበትን ስፍራ አይተው ቪፒኤኑን መርጠው ሊሆን ይችላል። የዚያን ሀገር የውሂብ ግለኝነት ፖሊሲን መሠረት በማድረግ ቪፒኤን ለመምረጥ አንደኛው ምክንያት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ሕጎች እና ፖሊሲዎች ሊቀየሩ እንደሚችሉም ማሰብ አለብዎት።
የቪፒኤን ምስጠራ ምን ያህል ደኅንነቱ የተጠበቀ ነው? አንድ ቪፒኤን እንደ ከነጥብ ወደ ነጥብ የዋሻ ፕሮቶኮል (PPTP) ያለ -የተሰበረ ምስጠራን ወይም ደካማ ምስጠራን የመሳሰሉ ምስጢራዊ ምስጠራዎችን እየተጠቀመ ከሆነ- በዚህ የሚያልፍ ማንኛውም መረጃ በአይኤስፒዎች ወይም በአገርዎ መንግስት በቀላሉ ሊፈታ እና ሊታይ ይችላል። የስራ ቪፒኤን የሚጠቀሙ ከሆነ ስለ ግንኙነቱ ደኅንነት የኮምፒውተር ባለሙያ ማግኘት አለብዎት። በቪፒኤን ውስጥ የምስጠራውን ጥንካሬን መገምገም አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤ በዚህ ምክንያት በዋን ፐራይቬሲ ሳይት የተዘጋጀውን ወደ 200 የሚጠጉ የቪፒኤን አገልግሎት ሰጭዎችን በሚዳኙበት ወሰን ክልል እና ፖሊሲዎቻቸውን በመመርኮዝ የሚተነትነውን ይህን የቪፒኤን ማነጻጸሪያ ገበታ መመልከት ያስፈልግዎት ይሆናል።
ኢኤፍኤፍ ስለቪፒኤኖች ደረጃ ማረጋገጫ መስጠት አይችልም። አንዳንድ እንደ አርአያ ሊጠቀስ የሚችል የግላዊነት ፖሊሲ ያላቸው የቪፒኤን አገልግሎቶች በአታላዮች የሚመሩ ሊኾኑ ይችላሉ። የማያምኑትን የቪፒኤን አገልግሎት አይጠቀሙ።
ያስታውሱ:- አንድ ወጥ የሆነ ለሁሉም የሚሆን ቪፒኤን የለም። ቪፒኤን ሲመርጡ ከግምት ውስጥ የሚገቡ ብዙ ነገሮች አሉ። ዲጂታል ደኅንነትዎን ለመጠበቅ ስለሚጠቀሙዋቸው መሣሪያዎች ማንኛውንም ውሳኔ ከማድረግዎ በፊት ሁልጊዜ የእርስዎን የስጋት ሞዴል ያስታውሱ።