Surveillance
Self-Defense

የልእለ መረጃ አስፈላጊነት

Last reviewed: 
8-10-2015
ይህ ገጽ ከእንግሊዘኛው ቅጂ የተተረጎመ ነው፡፡ የእንግሊዘኛው ቅጂ ምን አልባት የበለጠ የዘመነ ይሆናል፡፡

በዲጂታል ግንኙነት አውድ ውስጥ ልእለ መረጃ ከፖስታ ጋር ተመጣጣኝነት አለው። ስለ ላኩት እና ስለ ተቀበሉት መልእክት መረጃ ያለው ነው። የኢሜልዎ ርእሰ ጉዳይ፣ የውይይትዎ ርዝመት፣ እና ግንኙነቱን የት ቦታ ሆነው እንዳደረጉ (በተጨማሪም ከማን ጋር እንዳደረጉ) የሚያሳዩ የመረጃ አይነቶች በሙሉ ልእለ መረጃ ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ ከግንኙነትዎ ይዘት ውጪ ያለ ማንኛውም መረጃ እንደ ልእለ መረጃ ይገለጻል።

ልእለ መረጃ በታሪክ አሜሪካን ጨምሮ በአንዳንድ ሀገሮች ውስጥ ከግንኙነት ይዘት ይልቅ አነስ ያለ የህግ ጥበቃ ይደረግለታል። ለምሳሌ በበርካታ ሀገሮች ፖሊስ ስልክዎትን ጠልፍዎ የሚያወሩትን ከመስማት ይልቅ ባለፈው ወር ለማን ስልክ እንደደወሉ የሚያሳይ መረጃ በቀላሉ ማግኘት ይችላል።

ልእለ መረጃን የሚሰበስቡ ወይም የሚጠይቁ መንግስታት ወይም የቴሌኮሚኒኬሽን ኩባንያዎች የሚከራከሩት ልእለ መረጃን መስጠት (እና መሰብሰብ) ምንም ጉዳት አያስከትልም በማለት ነው። እንዳለመታደል, ሆኖ ይህ የመከራከሪያ ነጥብ ትክክል አይደለም። በጣም ትንሿ የልእለ መረጃ ናሙና እንኳን የአንድን ግለሰብ ህይወት የቅርብ መረጃ ሊሰጥ ይችላል።  ልእለ መረጃን መሰብሰብ ለመንግስታት እና ለኩባንያዎች ምን ያህል መግለጥ እንደሚችል በምሳሌ እንመልከት፦

  • በ2:24 am ላይ ስልክ በመደወል ለ18 ደቂቃዎች እንዳወሩ ያውቃሉ። ስለምን እንዳወሩ ግን አያውቁም።
  • ከጎልደን ጌት ድልድይ ለእራስ ማጥፋት መከላከያ አገልግሎት መደወልዎን ያውቃሉ ነገር ግን የደወሉበት የመነጋገሪያ ርእስ ሚስጥር እንደሆነ ይቆያል።
  • ከHIV ምርመራ አገልግሎት የኢሜል መልእክት እንዳገኙ፣ በመቀጠል ዶክተርዎ ጋር እንደደወሉ እና በተመሳሳይ ሰአት የHIV የምክር አገልግሎት ቡድንን ድረ ገጽ እንደጎበኙ ያውቃሉ። ነገር ግን የተላከልዎት ኢሜል ይዘት ምን እንደሆነ ወይም በስልክ ስለ ምን እንዳወሩ አያውቁም።
  • ከዲጂታል መብት አራማጆች ቡድን ርእሰ ጉዳዩ ላይ “SOPAን ለማስቆም 52 ሰአታ ቀርቷል” የኢሜል መልእክት እንደደረስዎ እና በመቀጠል ወዲያውኑ ለህዝብ ተወካይ እንደደወሉ ያውቃሉ። ነገር ግን የግንኙነቱ ይዘት ከመንግስት ጣልቃ ገብነት እንደተጠበቀ ይቆያል።
  • የማህጸን ስፔሻሊስት ጋር ደውለው እና ለግማሽ ሰአት እንዳወሩ እና በመቀጠልም በአካባቢዎ የሚገኝ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ጋር እንደደወሉ ያውቃሉ። ነገር ግን ምን እንዳወሩ ማንም አያውቅም።

ሶስተኛ አካላት ስኬታማ በሆነ መንገድ ግንኙነቱን እንዲፈጽሙ ለማድረግ ልእለ መረጃን ማግኘት ስለሚያሥፈልጋቸው ልእለ መረጃን ውጫዊ በሆነ አካል እንዳይሰበሰብ ማድረግ ቴክኒካዊ አዳጋችነት አለው።  የፖስታው የውጭ ክፍል በፖስታ ሰራተኛው መነበብ እንዳለበት ሁሉ የዲጂታል ግንኙነቶችም አብዛኛውን ጊዜ መነሻቸው እና መድረሻቸው መመልከት አለበት። የተንቀሳቃሽ ስልክ ኩባሊያዎች የሚደረግልዎትን የስልክ ጥሪዎችን ለማስተላለፍ በደምሳሳው ያሉበትን ስፍራ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል።

እንድ ቶር ያሉ አገልግሎቶች እና እንደ ሪኮሼት ያሉ የሙከራ ፕሮጀችቶች የተለመዱ የመስመር ላይ ግንኙነቶች የተነሳ የሚፈጠሩ የልእለ መረጃዎችን መጠን ለመቀነስ ተስፋ ያደርጋሉ። ከልእለ መረጃ ጋር የተያያዙ ህግጋት እስኪሻሻሉ ድረስ እና ልእለ መረጃን የሚቀንሱ መሳሪያዎች እስካልተስፋፉ ድረስ አንድ ገለስብ ማድረግ የሚችለው በግንኙነት ወቅት ምን አይነት ልእለ መረጃ እንደሚያሥተላልፍ፣ ያንን መረጃ ማን እንደሚያገኘው እና እንዴት በጥቅም ላይ ሊውል እንደሚችል በደንብ ማወቅ ነው።

JavaScript license information