Surveillance
Self-Defense

የማክ ኮምፒውተር ተጠቃሚ ነዎት?

 • የማክ ኮምፒውተር ተጠቃሚ ነዎት?

  መረጃዎችን እና ግንኙነትዎን ለመጠበቅ የሚያስችልዎ ምክሮች እና መሣሪያዎች።

  ይህ ዝርዝር የማክ ተጠቃሚዎች የመስመር ላይ ግንኙነታቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ እና የጆሮ ጠቢዎች ክትትልን ለመከላከል እንዲረዷቸው ታስበው የተዘጋጁ የምክሮች እና የአጋዥ የመሣሪያዎች ስብስብ ነው።

 • የሚያጋጥምዎ አደጋዎችን መገምገም

  ጠቅላላ ውሂብዎን ሁልጊዜ ከሁሉም ሰው ለመጠበቅ መሞከር እጅግ አድካሚ እና የማይቻል ነው፡፡ ነገር ግን መፍራት የለብዎትም! ደኅንነት በጥንቃቄ በሚነደፍ ዕድቅ የሚመራ እና ለእርሶ ትክክለኛ የሆነውን እየተጠቀሙ የሚያዳብሩት ሂደት ነው፡፡ ደኅንነት ማለት እንዳንድ መሳሪያዎች መጠቀም ወይም ሶፍትዌር ማውረድ ማለት አይደለም፡፡ እርስዎ በተለየ የተጋረጠብዎን የደኅንነት ስጋት ከመረዳት እና እነዚህን ስጋቶች እንዴት መመከት እንደሚቻል ከማወቅ የሚጀምር ነው፡፡.

  በኮምፒተር ደኅንነት ስጋት የሚባለው ውሂብዎን ከጥቃት ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት የማሳነስ አቅም ያለው ክስተት ነው፡፡ ምን መከላከል እንደሚፈልጉ እና ከማን መከላከል እንደሚፈልጉ በመለየት ያጋጠመዎትን ስጋት መጋፈጥ ይችላሉ፡፡ ይህ ሂደት “የስጋት ሞዴል” ይባላል፡፡

  ይህ መመሪያ የስጋት ሞዴልዎን እንዴት መቅረጽ እንዳለብዎ ወይም የዲጂታል መረጃዎችዎ የሚያጋጥማቸውን አደጋ እንዴት መገምገም እንደሚችሉ እና የትኞቹ መፍትሔዎች ለእርስዎ የተሻለ እንደሆኑ ያስተምራል፡፡

  የስጋት ሞዴል እንዴት ያለ ነገር ነው? ቤትዎ እና ንብረትዎን እንዳይዘረፉ ይፈልጋሉ እንበል፡፡ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቀዎች ይጠይቃሉ፡

  በቤቴ ውስጥ ያለ ጥበቃ የሚያስፈልገው ነገር ምንድን ነው?

  • የንብረትዎ ዝርዝር ጌጣጌጦች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣ የባንክ ሰነዶች፣ የመጓጓዣ ሰነዶች ወይም ፎቶግራፎችን ሊጨምሩ ይቻላሉ፡፡

  ከማን ነው ራሴን መከላከል የምፈልገው?

  • የባለጋራዎችዎ ዝርዝር፡- ዘራፊዎችን፣ ደባልዎችዎን ወይም እንግዳዎችን ሊጨምር ይቻላል፡፡

  መከላከል ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

  • ጎረቤቶቼ ከዚህ በፊት ተዘርፈው ያውቃሉ? ደባሎቼ ወይም እንግዶቼ ምን ያህል ታማኝ ናቸው? ባለጋራዎቼ እኔን ማጥቃት የሚያስችል ምን አቅም አላቸው? ግምት ውስጥ የማስገባቸው አደጋዎች ምንድን ናቸው?

  ይሄንን መከላከል ባልችል ሊደርስብኝ የሚችለው አደጋ መጠኑ ምን ያህል ነው?

  • በቤቴ ያለ ልተካዉ የማልችለው ነገር ምን ምንድን ነው? እነዚህን ነገሮች መተካት የሚያስችል ገንዘብ እና ጊዜ አለኝ? የገባኹት የመድኅን ዋስትና ከቤቴ የተዘረፉ ንብረቶችን ይጨምራል?

  ሊደርስብኝ ከሚችል አደጋ ራሴን ለመከላከል ምን ያህል ርቀት ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ?

  • ለአደጋ የተጋለጡ ሰነዶችን ማሰቀመጫ የሚሆን ካዝና ለመግዛት ፍቃደኛ ነኝ? እጅግ አስተማማኝ ቁልፎችን የመግዛት አቅም አለኝ? በአቅራቢያዬ የሚገኝ ባንክ የደኅንነት ሳጥን ተከራይቼ ውድ ንብረቶቼን ለማስቀመጥ ጊዜ አለኝ?

  እነዚህን ጥያቄዎች ለራስዎ ካቀረቡ በኋላ ማድረግ የሚችሉትን ነገር ለመገምገም ዝግጁ ነዎት፡፡ ንብረትዎችዎ ትልቅ ዋጋ ያላቸው ሆነው ነገር ግን የመዘረፍ እድላቸው ዝቅተኛ ከሆነ ካዝና በመግዛት ብዙ ገንዘብ ማውጣት አይኖርብዎት ይሆናል፡፡ ነገር ግን አደጋው ከፍተኛ ከሆነ ገበያ ላይ የሚገኝ ምርጥ ካዝና መግዛት ይኖርብዎታልም፤ ደኅንነት ስርዓት ለመጨመርን ማሰብ ይኖርብዎታል፡፡

  የደኅንነት ስጋት ሞዴል መገንባት የሚያጋጥምዎን የተለየ አደጋ ፣ ንብረትዎችዎን፣ ባለጋራዎችዎን፣ የባላጋራዎችዎን አቅም እና የተጋረጠብዎ አደጋ የመፈጸም ዕድል ምን ያህል እንደሆነ እንዲገነዘቡ ይረዳዎታል፡፡

  የስጋት ሞዴል ምንድን ነው? ከየትስ ነው የሚጀምረው?

  የስጋት ሞዴል ዋጋ በሚሰጧቸው ነገሮች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ነገሮች እንዲለዩ እና ከማን መጠበቅ እንደሚገባዎ እንዲያውቁ ይረዳዎታል፡፡ የስጋት ሞዴልዎን ሲቀርጹ ለእነዚህ አምስት ጥያቄዎች መልስ ያዘጋጁ:

  1. ምንድን ነው መከላከል የምፈልገው?
  2. ራሴን መከላከል የምፈልገው ከማን ነው?
  3. ይሄንን መከላከል ባልችል ሊደርስብኝ የሚችለው አደጋ መጠኑ ምን ያህል ነው?
  4. ራሴን መከላከል ምን ያህል ነው የሚያስፈልገኝ?
  5. ሊደርስብኝ ከሚችል አደጋ ራሴን ለመከላከል ምን ያህል ርቀት ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ?

  እያንዳንዱን ጥያቄ በዝርዝር እንመልከት፡፡

  ምንድን ነው መከላከል የምፈልገው?

  ንብረት ዋጋ የሚሰጡት እና እንዳይጠፋብዎ የሚጠብቁት ነገር ነው፡፡ ስለ ዲጂታል ደህንነት በምንነጋገርበት ወቅት እሴት ወይም ንብረት የምንለው ነገር መረጃን እንደኾነ መታወቅ ይኖርበታል። ለምሳሌ የኢሜል አድራሻዎ፣ የወዳጆችዎ ዝርዝር፣ የፈጣን መልዕክት ልውውጥዎ፣ ቦታዎች እና የተለያዩ ሰነድዎችዎ በሙሉ ንብረትዎችዎ ናቸው። በተጨማሪም ኮምፒውተርዎ፣ ስልክዎ እና የመሳሰሉትም ንብረትዎችዎ ናቸው።

  የንብረትዎን ዝርዝር፣ ውሂብዎ የት እንደተቀመጠ፣ እነማን መጠቀም እንደሚችሉ እና ሌሎች እንዳይጠቀሙት የሚከለክላቸው ምን እንደኾነ ይጻፉ።.

  ራሴን መከላከል የምፈልገው ከማን ነው?

  ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ማን እርስዎን አና መረጃዎችዎን ዒላማ ውስጥ ማስገባት ይፈልጋል የሚለውን ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ ግለሰብ ወይም ሌላ አካል ንብረቶችዎ ላይ ስጋት የሚጥል ሁሉ “ባለጋራዎ” ነው፡፡ አለቃዎ፣ የቀድሞ ባልደረባዎ፣ የቢዝነስ ተፎካካሪዎ፣ የሀገርዎ መንግስት ወይም በህዝባዊ ትይይዝት ላይ ያለ የመረጃ ጠላፊ አቅም ያላቸው የባለጋራዎች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

  የእርስዎን ውሂብ ወይም የግንኙነት መረጃዎን ማግኘት የሚፈልግ ማን ሊኾን እንደሚችል ጥርጣሬ ውስጥ በማስገባት የባለጋራዎችዎን ዝርዝር ያውጡ። እነርሱም ግለሰቦች፣ የመንግስት አካላት ወይም ተቋማት ሊኾኑ ይችላሉ፡፡

  የስጋት ሞዴልዎን ካዘጋጁ በኋላ እንደባለጋራዎችዎ ማንነት፣ በተወሰኑ ሁኔታዎች ውስጥ ይህንን ዝርዝር ማስወገድ ይኖርብዎ ይሆናል፡፡

  ይሄንን መከላከል ባልችል ሊደርስብኝ የሚችለው አደጋ መጠኑ ምን ያህል ነው?

  ባለጋራዎ በመረጃዎ ላይ ጉዳት ወይም አደጋ ሊያደርስ የሚችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ ግንኙነትዎ በኔትወርክ በሚተላለፍበት ወቅት ባለጋራዎ የግንኙነትዎን ይዘት ሊያዳምጥ ወይም ሊያነብ፤ ወይም የግል ውሂብዎን ሊሰረዝ ወይም ሊያበላሽ ይችላል።

  ባለጋራዎች የሚያደርሱት ጥቃት የተለያየ እንደኾነ ሁሉ ጥቃት ለመሰንዘር የሚነሱበት አላማም እንዲሁ የተለያየ ነው። ለምሳሌ ፖሊስ ወይም የተለያዩ የሕግ አስፈጻሚ አካላት የፈጸሙትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚያሳይ ቪዲዮ ቢኖርዎት መንግስት የዚህን ቪዲዮ ስርጭት ለመቀነስ በማሰብ ቪዲዮውን ለማጥፋት ወይም ተደራሽነቱን ለመቀነስ ሊሞክር ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካዊ ባላንጣዎችዎ እንዲህ ዓይነቱን ድብቅ መረጃ ያለ እርስዎ ዕውቀት በእጃቸው ማስገባት እና ማተም ይፈልጉ ይሆናል።

  የስጋት ሞዴል ባለጋራዎ ከንብረትዎ በአንዱ ላይ ጥቃት ለመፈጸም ቢሳካለት የሚያስከትለውን ጉዳት መጠን በመረዳት ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ ይህን ለማድረግ የባለጋራዎን አቀም ከግምት ውሰጥ ማስገባት ይገባል፡፡ ለምሳሌ የስልክ አገልግሎት አቅራቢ በስልክዎ የሚያደርጉትን ግንኙነት በሙሉ ማግኘት ስለሚችል የራስዎን መረጃ በመጠቀም ሊጎዳዎት ይችላል። ክፍት የኾኑ የዋይፋይ ኔትወርኮችን በሚጠቀሙበት ወቅት መረጃ ጠላፊዎች ያልተመሰጠሩ ግንኙነትዎትን ሊያገኙ ይችላሉ። መንግስታት ደግሞ የበለጠ አቅም ይኖራቸዋል፡፡

  በመኾኑም ባለጋራዎ በግል ውሂብዎ ማድረግ የሚፈልገው ምን ሊኾን እንደሚችል ይዘርዝሩ።

  መከላከል ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

  አደጋ የሚባለው የደኅንነት ስጋት የተወሰነ ንብረትዎን የምር መጠቃት አዝማሚያ ነው፡፡ ይህም ከአቅም ጋር ጎን ለጎን አብሮ የሚሄድ ነው። ምንም እንኳን የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢ የእርስዎን ውሂብ ሙሉ በሙሉ የማግኘት አቅም ቢኖረውም የእርስዎን መልካም ስም ለማጉደፍ ኾን ብለው የግል ውሂብዎን በአደባባይ ላይ የመለጠፍ አዝማሚያው አናሳ ነው።

  በስጋት እና በአደጋው የመከሰት አዝማሚያ መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ጠቃሚ ነው። ስጋት ሊከሰት የሚችለው ጉዳት ሲኾን አደጋው የመከሰቱ አዝማሚያ ወይም ሪስክ የሚባለው ደግሞ ይህ ስጋት ሊከሰት የሚችልበት አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል ነው። ለምሳሌ የህንጻ መደርመስ ስጋት ቢኖር ይህ ስጋት ግን ለስምጥ ሸለቆ ቅርብ በሆኑ ከተሞች ሊከሰት የሚችልበት አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል በርቀት ከሚገኙት በጣም ከፍ ያለ ነው።

  አደጋው የመከሰቱ አዝማሚያ ወይም የመኾን ዕድል ትንተናን ማካሄድ ግለሰባዊ እና በግለሰቡ አመለካከት የተቃኘ ሂደት ነው። ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ስጋትን የሚያይበት እና ቅድሚያ የሚሰጥበት መንገድ ተመሳሳይ አይደለም። በርካታ ሰዎች የተወሰኑ ስጋቶች የመከሰት አዝማሚያቸው ምንም ይሁን ምን ለመጋፈጥ ፈቃደኛ አይደሉም። ምክንያቱም የስጋቱ መኖር ብቻ ከሚያስፈልጋቸው ዋጋ ጋር ሲወዳደር ሚዛን አይደፋም ብለው ስለሚያምኑ ነው። በሌሎች ሁኔታዎች ደግሞ ግለሰቦች አደጋው የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ቢኾንም እንኳን ስጋቱን እንደ ችግር አያዩትም።

  በከፍተኛ ትኩረት ሊመለከቷቸው የሚገቡ ስጋቶችዎን በዝርዝር ይጻፉ፤ እንደገናም የመከሰት ዕድላቸው አናሳ የሆኑ ወይም ጉዳት የለሽ በመሆናቸው (ወይም ለመከላከል አዳጋች የሆኑትን) የሚያስጨንቅዎን ያስፍሩ፡፡

  ሊደርስብኝ ከሚችል አደጋ ራሴን ለመከላከል ምን ያህል ርቀት ለመሄድ ፈቃደኛ ነኝ?

  ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የጉዳት አዝማሚያ ትንታኔ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች አይኖሩትም ወይም ስጋቶችን በተመሳሳይ መንገድ አይመለከትም፡፡

  ለምሳሌ በብሔራዊ ደኅነነት ጉዳይ ውስጥ የሚገኝ ደንበኛውን የሚወክል የህግ አማካሪ/ጠበቃ ከአንድ ለልጅዋ አስቂኝ የድመት ቪዲዮዎችን ከምትልክ እናት በበለጠ የተመሰጠሩ ኢሜሎችን ለመጠቀም እና ግንኙነቶቹን ለመጠበቅ ብዙ ርቀት ይጓዛል፡፡

  ልዩ ስጋቶችዎ የሚያደርሱብዎን ጉዳት ለመቀነስ ያልዎትን አማራጮች በሙሉ ይዘርዝሩ፤ የገንዘብ እጥረት፣ የቴክኒክ ጉድለት ወይም ማኀበራዊ እንቅፋት ካለብዎም ያስፍሯቸው፡፡

  ስጋት ሞዴል እንደ የዘወትር ተግባር

  የስጋት ሞዴልዎ እርስዎ ያሉበት ሁኔታ ሲቀየር አብሮ እንደሚቀየር በአእምሮዎ ይመዝግቡ፡፡ በዚህ ምክንያት በየጊዜው የስጋት ሞዴልን መገምገም ጥሩ ልምድ ነው፡፡

  በራስዎ ልዩ ሆኔታ ላይ የተመሰረተ የራስዎን የስጋት ሞዴል ይፍጠሩ፡፡ለወደፊት በቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ያድርጉ፡፡ ይህም የስጋት ሞዴልዎን እንዲከልሱ እና አሁን ለሚገኙበት ሁኔታ ተገቢ መሆኑን እንዲፈትሹ ይረዳዎታል፡፡

  Last reviewed: 
  2017-09-07
 • አጠቃላይ የመስመር ላይ ግንኙነት ስለማድረግ

  የቴሌኮሚኒኬሽን ኔትወርኮች እና ኢንተርኔት ከሌሎች ሰዎች ጋር የምናደርገውን ግንኙነት ከምንጊዜውም በተሻለ እጅግ ፈጣን እንዲኾን ቢያደርጉም በዛው ልክ የእርስ በእርስ ግንኙነታችን በጣም በተስፋፋ ኹኔታ በሦስተኛ ወገን እንዲሰለል፣ እንዲቀዳ እና እንዲሰማ እድልን ከፍተዋል። ግላዊነትዎን ለመጠበቅ ተጨማሪ እርምጃዎችን ካልወሰዱ እያንዳንዱ የስልክ ጥሪ፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክቾች፣ ኢሜል ምልልሶች፣ ፈጣን የመልዕክት አገልግሎቶች፣ IPን ተጠቅሞ ሚደረጉ የድምጽ (VoIP) ጥሪዎች፣ የቪዲዎ ውይይቶች እና በማህበራዊ ድረ ገጽ የሚደረጉ የመልዕክት ልውውጦች በሙሉ በሦስተኛ ወገን የመደመጥ፣ የመታየት እንዲሁም እንደ ዶክመንት የመያዝ አደጋ አለባቸው።

  አብዛኛውን ጊዜ ከሌሎች ሰዎች ጋር ደህንነቱ የተጠበቀ ግንኙነት የማድረጊያው መንገድ የመገናኛ አውታሮችን፣ ኮምፒውተሮችን ወይም ሰልኮችን ሳይጠቀሙ በአካል መገናኘት ነው። በአካል መገናኘት ሁልጊዜም የማይቻል ነገር ስለሆነ በኔትዎርክ አማካኝነት ግንኙነት በሚፈጽሙበት ወቅት የግንኙነትዎን ይዘት መደበቅ የሚፈልጉ ከኾነ በአካል ከመገናኘት ቀጥሎ ያለው ጥሩ አማራጭ ከዳር እስከ ዳር ምስጠራን መጠቀም ነው።

  ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ እንዴት ይሰራል?

  ሁለት ግለሰቦች ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ኢንተርኔትን ተጠቅመው መገናኘት ሲፈልጉ (ለምሳሌ አበበ እና ጫልቱ) እያንዳንዳቸው የመልዕክት መሰወሪያ ቁልፎችን ማመንጨት አለባቸው። አበበ ለጫልቱ መልዕክትን ከመላኩ በፊት ጫልቱ ብቻ መልዕክቱን መፍታት እንድትችል በእርሷ ቁልፍ መልዕክቱን ያመሰጥረዋል። የተመሰጠረውን መልዕክትም በኢንተርኔት ይልከዋል። ማንኛውም ግለሰብ የአበበ እና የጫልቱን ግንኙነት ቢሰልል እና አበበ መልዕክቱን ለመላክ የተጠቀመውን አገልግሎት (ለምሳሌ የአበበን የኢሜል መለያ) መጠቀም ቢችል እንኳን ሰላዩ የሚያየው የተደበቀውን መልዕክት እንጂ የመልዕክቱን ይዘት አይደለም። ጫልቱ መልዕክቱን በምትቀበልበት ወቅት የራሷን ቁልፍ በመጠቀም ይዘቱን ወደ ሚነበብ መልዕክት መፍታት አለባት።

  ከዚህ በተጨማሪ ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ ከፍ ያለ ጥረትን የሚፈልግ ቢኾንም ሁለቱም ተጠቃሚዎች እየተገለገሉት ያለውን የመሣሪያ ስርዓት ማመን ሳያስፈልጋቸው የግንኙነታቸውን ደህንነት የሚያጣሩበት ብቸኛው መንገድ ነው። እንደ ስካይፕ ያሉ አንዳንድ አገልግሎቶች ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ አገልግሎት እንደሚሰጡ ቢያስረግጡም በተደጋጋሚ እንደታየው ግንኙነታቸው ድብቅ አይደለም። ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲኾን ተጠቃሚዎቹ የሚልኩትን መልዕክት የሚያመሰጥሩበት የመሰወሪያ ቁልፍ መልዕክቱን የሚላክለት ሰው መኾኑን ማረጋገጥ አለባቸው። የግንኙነት ሶፍትዌሩ ይህን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል አቅም ከሌለው ወይም በውስጡ ያልተካተተ ካልኾነ የሚጠቀመው ማንኛውም ምስጠራ በአገልግሎት ሰጪው መጠለፍ ይችላል (ለምሳሌ መንግስት ይህን እንዲያደርጉ ካስገደደ)።

  ከዳር እስከ ዳር ማመስጠሪያን በመጠቀም ፈጣን የጽሑፍ መልዕክቶችን እና ኢሜልን ከጥቃት ለመከላከል በዚህ ዙሪያ ላይ ፍሪደም ኦፍ ዘ ፕረስ ፋውንዴሽን ያወጣውን እንክሪፕሽን ወርክስ የሚለውን ጽሑፍ ያንብቡ። በተጨማሪም የሚከተሉትን የSSD ሞጁሎችን ማንበብ አይዘንጉ፦

  የድምጽ ጥሪዎች

  የቤት ወይም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቅመው ለወዳጅዎ ሲደውሉ የሚያደርጉት ጥሪ ከዳር እስከ ዳር የተመሰጠረ አይደለም። በተንቀሳቃሽ ስልክ የሚጠቀሙ ከኾነ ምናልባት ከስልክ ቀፎዎ እስከ ስልኩ ማማ ድረስ ያለው የስልክ ጥሪዎ ክፍል ሊመሰጥር ይችላል። ነገር ግን መልዕክትዎ ከስልክ ማማ ባሻገር ባለው የስልክ ኔትወርክ በሚተላለፍበት ወቅት የስልክ አገልግሎቱን በሚሰጠው ኩባንያ የመሰለል ዕድሉ ከፍ ያለ ነው። ስለዚህም በስልክ አገልግሎት ሰጪው ላይ ስልጣን ያለው ማንኛውም መንግሥት ወይም ድርጅት ይህንን መረጃ ማግኘት ይችላል ማለት ነው። በመኾኑም የድምጽ ግንኙነት በሚያደርጉበት ጊዜ ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ እንዳልዎት ለማረጋገጥ ቀላሉ መንገድ IPን ተጠቅመው የድምጽ ግንኙነትን (VoIP) ማድረግ የሚያስችሉ ሶፍትዌሮችን መጠቀም ነው።

  በጣም የታወቁት IPን ተጠቅመው የድምጽ ግንኙነት አገልግሎት ሰጪዎች እንደ እስካይፕ እና ጎግል ሃንግአውትስ ያሉት ሰላዮች የግንኙነትዎን ይዘት እንዳይሰሙ የዝውውር ላይ ምስጠራ የሚሰጡ ቢኾንም እራሳቸው አገልግሎት ሰጪዎቹ መልዕክቱን የመስማት አቅም ስለሚኖራቸው ይጠንቀቁ። የስጋት ሞዴልዎን መሠረት በማድረግ ይህ ችግር ሊኾን ወይም ላይኾን ይችላል።

  IPን ተጠቅመው ከዳር እስከ ዳር ምስጠራን የሚሰጡ የድምጽ ግንኙነት (VoIP) አገልግሎት ሰጪዎች የሚከተሉትን ይጨምራል፦

  ከዳር እስከ ዳር የተመሰጠረ የVoIP ውይይት ለማድረግ ሁለቱም የግንኙነት አካላት ተመሳሳይ (ወይም ተኳኋኝ) የኾነ ሶፍትዌርን መጠቀም ይኖርባቸዋል።

  አጭር የጽሑፍ መልዕክት

  መደበኛ አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) የዳር እስከ ዳር ምስጠራ አገልግሎት የለውም። የተመሰጠረ መልዕክትን ከስልክዎ ላይ መላክ ከፈለጉ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ፈንታ የተመሰጠረ ፈጣን የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎት ሶፍትዌር መጠቀምን ከግምት ውስጥ ያስገቡ።

  አንዳንድ ከዳር እስከ ዳር ማመስጠሪያ ፈጣን የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎቶች የራሳቸውን ስርዓት ይጠቀማሉ። ለምሳሌ በአንድሮይድ እና በiOS ላይ እና የሲግናል ተጠቃሚዎች እነዚህን ፕሮግራሞች ከሚጠቀሙ ከሌሎች ሰዎች ጋር ምስጢራዊ ውይይት ማካሄድ ይችላሉ። ቻት ሴኪዩር XMPPን በሚጠቀም ማንኛውም ኔትወርክ ላይ ውይይትን የሚያመሰጥር የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ነው። ይህ ማለት ከብዙ ፈጣን የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎቶች መካከል መምረጥ ይችላሉ ማለት ነው።

  ፈጣን የጽሑፍ መልዕክቶች

  ከምዝገባ ውጪ ወይም ኦፍ ዘ ሪከርድ (OTR) የሚባለው የጽሑፍ መልዕክት ውይይቶችን ከዳር እስከ ዳር የማመስጠር ስነስርዓት ሲኾን በተለያዩ አገልግሎቶች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

  OTRን ከፈጣን የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎት ጋር አጠቃለው የያዙ መሣሪያዎች የሚከተሉትን ይጨምራል፦

  ኢሜል

  አብዛኞቹ የኢሜል አገልግሎት ሰጪዎች እንደ ፋየርፎክስ ወይም ክሮም ያሉ የድረ ገጽ ማሰሻዎችን ተጠቅመው ኢሜልዎን እንዲያነቡ ያስችልዎታል። ከእነዚህ አገልግሎት ሰጪዎች ብዙዎቹ የHTTPS ወይም ትራንስፖርት ለየር ኢንክሪፕሽን ድጋፍን ይሰጣሉ። ኢሜልዎን በሚጠቀሙበት ሰዓት በድር ማሰሻው የላይኛው ክፍል ላይ ያለው URL በHTTP ፋንታ HTTPS (ለምሳሌ፦ https://mail.google.com) በሚል የሚጀምር ከኾነ የኢሜል አገልግሎት ሰጪዎ ይህን አግልግሎት እንደሚሰጥ እና የኢሜል ልውውጥዎ ከሦስተኛ ወገን ጥቃት የተጠበቀ መኾኑን ማረጋገጥ ይቻላሉ።

  የኢሜል አገልግሎት ሰጪዎ የHTTPS ድጋፍ ያለው ኾኖ ይህንን አገልግሎት በነባሪ የማይሰጡ ከኾነ ግን በኢሜልዎ የድር ማሰሻው URL ላይ HTTP የሚለውን HTTPS በሚል ይቀይሩት እና ገጹን ያድሱት። የHTTPS አገልግሎትን በሚሰጡ ሁሉም ገጾች ላይ HTTPSን ሁልጊዜ እንደሚጠቀሙ ማረጋገጥ ከፈለጉ HTTPS በሁሉም ቦታ የተሰኘውን ለፋየርፎክስ ወይም ለክሮም የድር ማሰሻ ተጨማሪ አውርደው ይጫኑ።

  የሚከተሉትን የኢሜል አገልግሎት ሰጪዎች በነባሪው HTTPSን ይጠቀማሉ ፦

  • ጂሜል
  • ራይዝአፕ
  • ያሁ

  አንዳንድ የኢሜል አገልግሎቶች መቼት ውስጥ በመግባት በነባሪው HTTPSን መጠቀምን እንዲመርጡ ምርጫን ይሰጣሉ። እስካሁን ድረስ ይህንን በማድረግ በጣም ታዋቂው ሆትሜል ነው።

  የትራንስፖርት ለየር ምስጠራ የሚሠራው ምንድን ነው ለምንስ ያስፈልግዎታል? በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል HTTPS አልፎ አልፎም SSL ወይም TLS በመባል የሚታወቀው የመስመር ላይ ግንኙነትዎ እርስዎ የሚጠቀሙትን ኔትወርክ በሚጠቀሙ ሌሎች ሰዎች እንዳይነበብ የሚያመሰጥር ስርዓት ነው። ይህም በኤርፖርት ውስጥ የሚገኝን ተመሳሳይ Wi-Fiን የሚጠቀሙ ሰዎች፣ በትምህርት ቤትዎ ወይም በመስሪያ ቤትዎ ያሉ ሰዎች፣ የኢንተርኔት አግልግሎት ሰጪ አስተዳዳሪዎች፣ ሸረኛ መዝባሪዎች፣ መንግሥታት፣ ወይም ሕግ አስፈጻሚ አካላትን ሊጨምር ይችላል። በHTTPS ፋንታ HTTPን በሚጠቀሙበት ወቅት በድር መዳሰሻዎ የሚያደጓቸው የትኞቹም ዓይነት ግንኙነቶች ማለትም የጎበኟቸው ገጾች እና የኢሜል ይዘቶች፣ የጦማር ፖስቶች፣ እና መልዕክቶች በአጥቂዎች ለመጠለፍ እና ለመነበብ የተጋለጡ ናቸው።

  HTTPS የድር ዳሰሳ በሚያካሂዱበት ወቅት ለሁሉም ሰው እንዲጠቀመው የምንመክረው በጣም መሠረታዊው የምስጠራ ደረጃ ነው። በመኾኑም ልክ መኪና ሲነዱ መታጠቂያ ቀበቶዎን እንደሚያስሩ ሁሉ ማንኛውም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሊጠቀመው የተገባ ነው።

  ኾኖም HTTPS የሚከተሉትን ግልጋሎቶች አይሰጥም። በHTTPS የኢሜል ልውውጥ ወቅት የኢሜል አገልግሎት የሚሰጠው ድርጅት የኢሜሎትን ይዘት ሊያነብ ይችላል። መንግስት ወይም የሕግ አስፈጻሚ አካላት ኢሜሎትን ያለ ፈቃዶ ሊያነቡ ይችላሉ። በአሜሪካን ሀገር አብዛኞቹ የኢሜል አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ደምበኞቻቸውን በተመለከተ መንግስት ጥያቄ ቢያቀርብላቸው ጥያቄው እንደቀረበላቸው ለተጠቃሚዎቻቸው እንደሚያሳውቁ የሚገልጽ ፖሊሲ አላቸው። ነገር ግን እነዚህ ፖሊሲዎች በድርጅቶቹ መልካም ፈቃድ ላይ የተመሰረቱ ናቸው። አንዳንድ የኢሜል አገልግሎት ሰጪዎች ለምሳሌ ጎግል፣ ያሁ፣ ማይክሮሶፍት እና ሌሎችም በየአመቱ መንግሥት የሚጠይቃቸውን የተጠቃሚዎችን ዳታ ዝርዝር፣ የትኞቹ አገር ጥያቄውን እንዳቀረቡ እና ለምን ያህሉ ጥያቄ ድርጅቱ መልስ እንደሰጠ የግልጽነት ሪፖርቶች ያወጣሉ።

  የደህንነት ሞዴልዎ የመንግስት አካላትን ወይም የሕግ አስፈጻሚ አካላትን የሚጨምር ከኾነ፣ ወይም የኢሜል አገልግሎት ሰጪዎ የኢሜል ግንኙነትዎ ይዘትን ለሶስተኛ ወገን አሳልፈው መስጠት እንደማይችሉ ማረጋገጥ የሚፈልጉበት ምክንያት ቢኖርዎት የኢሜል ግንኙነት በሚያደርጉበት ወቅት ከዳር እስከ ዳር ማመስጠሪያን መጠቀምን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለብዎት።

  እጅግ መልካም የኾነ ግላዊነት ወይም ፕሪቲ ጉድ ፕራይቬሲ (PGP) የሚባለው ዋናው የኢሜል የዳር እስከ ዳር ማመስጠሪያ ዘዴ ነው። በትክክል ጥቅም ላይ ከዋለ የሚያደርጉትን ማንኛውም የመስመር ላይ ግንኙነት በከፍተኛ ኹኔታ የተጠበቀ ያደርጋል። ለኢሜልዎ የPGP ምስጠራ እንዴት እንደሚጭኑ እና እንደሚጠቀሙ ለበለጠ ማብራሪያ የሚከተሉትን ይመልከቱ፦

  ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ ማድረግ የማይችለው

  ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ የመስመር ላይ ግንኙነት ይዘትን ብቻ መደበቅ ይችላል። ነገር ግን ግንኙነት መፈጠሩን ወይም ግንኙነቱ ከማን ጋር እንደተደረገ መደበቅ አይችልም። ይህ ማለት የግንኙነቱን የመረጃ መረጃን ወይም ሜታ ዳታን አይከላከልም ማለት ነው። የመረጃ መረጃ ማለት ከግንኙነቱ ይዘቱ ውጪ ያሉ እንደ የኢሜል ርዕሰ ጉዳይ፣ ወይም ከማን ጋር ግንኙነት እያደረጉ እንዳሉ እና ግንኙነቱን መቼ እንደደረጉ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

  የግንኙነትዎ ይዘት ሚስጥር በኾነበት ወቅት እንኳን ሜታ ዳታ ወይም የመረጃ መረጃዎች ስለ እርስዎ እጅግ በጣም ገላጭ መረጃን ሊሰጡ ይችላሉ።

  የስልክ ጥሪዎ ሜታ ዳታ ወይም የመረጃ መረጃ አንዳንድ በጣም ሚስጥራዊ እና ስሱ የኾኑ መረጃዎችን አሳልፈው ሊሰጡ ይችላሉ። ለምሳሌ፦

  • ከሌሊቱ 8:24 ላይ በድብቅ እንደደወሉ እና ለ18 ደቂቃ እንዳወሩ ያውቃሉ ነገር ግን ስለ ምን እንዳወሩ አያውቁም።
  • ከጎልደን ጌት ድልድይ ለእራስ ማጥፋት መከላከያ አገልግሎት መደወልዎን ያውቃሉ ነገር ግን የደወሉበት የመነጋገሪያ ርዕስ ሚስጥር እንደኾነ ይቆያል።
  • ከHIV ምርመራ አገልግሎት ጋር፣ በመቀጠልም ከዶክተርዎ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት እንደተነጋገሩ ያውቃሉ ነገር ግን ምን እንደተወያዩ አያውቁም።
  • የማህጸን ስፔሻሊስት ጋር ደውለው ለግማሽ ሰዓት እንዳወሩ እና በመቀጠልም በአካባቢዎ የሚገኝ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ጋር እንደደወሉ ያውቃሉ ነገር ግን ምን እንዳወሩ ማንም አያውቅም።

  ስልክ የሚደውሉት ከተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከኾነ ስላሉበት ስፍራ ያለው መረጃ ሜታ ዳታ ነው። በ2002 ዓ.ም. ማልቴ ስፒትስ የተባለው የግሪን ፓርቲ ፖለቲከኛ ከስድስት ወር በላይ የኾነ የስልክ ውሂቡን እንዲሰጡት ለማስገደድ የDeutsche ቴሌኮምን ከሶ ውሂቡ በጀርመን ጋዜጣ ላይ እንዲገኝ አድርጓል። የዚህ ውጤትም የሚከተሉት ስዕሎች የስፒትስን ንቅናቄ ታሪክ በጥልቀት ያሳያሉ።

  የመረጃ መረጃዎን ከጥቃት ለመከላከል ሌሎች ተጨማሪ መሳሪያዎችን መጠቀም ያስፈልግዎታል። ለምሳሌ ከዳር እስከ ዳር ምስጠራ ጎን ለጎን ቶር መጠቀም ይችላሉ።

  ለምሳሌ የግንኙነትዎን ይዘት እና የመረጃ መረጃዎን ከተለያዩ አቅም ካላቸው አጥቂዎች ለመከላከል፣ ቶር እና HTTPS እንዴት አብረው እንደሚሰሩ ለማየት ይህን ገለጻ መመልከት ይችላሉ።

  Last reviewed: 
  2017-01-12
 • የቁልፍ ማረጋገጫ ብልሃት

  ምስጠራ በጥንቃቄ ጥቅም ላይ ከዋለ የመስመር ላይ ግንኙነትዎ ወይም የመልዕክት ልውውጥዎ ከእርስዎ እና ግንኙነቱን ከሚያደርጉት ሰው በስተቀር በሌላ አካል እንዳይነበብ ያደርጋል። የዳር እስከ ዳር ምስጠራ ውሂብዎ በሌላ በሦስተኛ አካል እንዳይሰለል ይከላከላል። ነገር ግን ግንኙነቱን እያካሄዱት ያለው ማንነቱን ጠንቅቀው ከማያውቁት ግለሰብ ጋር ከኾነ የዳር እስከ ዳር ምስጠራ ጥቅሙ ውስን ይኾናል። የቁልፍ ማረጋገጫ ጥቅም የሚነሳው እዚህ ብላይ ነው። የአደባባይ ቁልፎችን በማረጋገጥ የእርስዎን እና ከእርስዎ ጋር ግንኙነት የሚያደርገው ግለሰብ ማንነትን እርስ በእርስ በማረጋገጥ ለምታደርጉት ግንኙነት ተጨማሪ የደህንነት ጥበቃን ትፈጥራላችሁ። ይህም ግንኙነቱን እየፈጽሙት ያሉት ከትክክለኛው ግለሰብ ጋር መኾኑን እርግጠኛ እንዲኾኑ ይረዳዎታል።

  የቁልፎች ማረጋገጫ ከዳር እስከ ዳር ምስጠራን የሚጠቀሙ ስርዓቶች ዋንኛ ገጽታ ነው። ከእነዚህም ውስጥ በእንግሊዝኛ ምሕጻረ ቃል PGP እና OTR በመባል የሚታወቁት ተጠቃሾች ናቸው። ሲግናል ላይ, እነርሱ "ደህንነት ቁጥሮች." ተብለን እንጠራለን ቁልፎችን በሚያረጋግጡበት ወቅት በሦስተኛ ወገን የመጠለፍ አደጋን ለማስወገድ ቁልፉ የሚያረጋግጡበት መንገድ ምስጠራን ለመጠቀም ከሚፈልጉበት የግንኙነት መንገድ የተለየ ስርዓትን እንዲጠቀሙ ይመከራል። ይህም ስርዓት ከመስመር ውጪ የኾነ ማረጋገጫ (በእንግሊዝኛው አውት ኦፍ ባንድ ቬሪፊኬሽን) ተብሎ ይጠራል። ለምሳሌ የOTR አሻራዎትን የሚያረጋገጡ ከኾነ የጣት አሻራችሁን አንደኛው ለሌላኛው በኢሜል ልትላላኩ ትችላላችሁ። በዚህ ምሳሌ ላይ ኢሜል ሁለተኛው የግንኙነት መንገድ ነው።

  ከመስመር ውጪ ቁልፎችን ማረጋገጥ

  ይህንን ለማድረግ የተለያዩ መንገዶች አሉ። በጥንቃቄ ማቀድ ከተቻለ እና አመቺ ከኾነ ቁልፎችን በአካል ተገናኝቶ ማረጋገጥ ሁነኛው መንገድ ነው። ይሄ በብዛት በቁልፍ ማረጋገጫ ድግሶች እና በሥራ ባልደረባዎች መካከል የሚደረግ ነው።

  ነገር ግን በአካል መግናኘት የማይቻል ከኾነ ግንኙነት የሚያደርጉትን ግለሰብ ቁልፍ ከሚያረጋግጡት የመገናኛ መንገድ የተለየ ሌላ የመገናኛ መንገድን ተጠቅመው ማረጋገጥ ይችላሉ። ለምሳሌ ከኾነ ሰው ጋር የPGP ቁልፎችን ማረጋገጥ የሚፈልጉ ከኾነ ስልክ በመደወል ወይም የOTR አጭር የጽሁፍ መልዕክትን (የኦፍ ዘ ሪከርድ ሜሴጅ) በመጠቀም ቁልፉን ማረጋገጥ ይችላሉ።

  ይህ ከኾነ ዘንዳ ማንኛውንም ዓይነት ፕሮግራም ቢጠቀሙ ሁልጊዜ የእርስዎንም ኾነ የግንኙነት አጋርዎን ቁልፍ ማግኘት ይችላሉ።

  ምንም እንኳ የግንኙነት ቁልፉን የማግኛው መንገድ ከፕሮግራም ፕሮግራም የሚለያይ ቢኾንም የቁልፍ ማረጋገጫው ዘዴ ግን እጅግ በጣም ተቀራራቢ ነው። ይህም የቁልፍ የጣት አሻራዎችን ጮክ ብሎ ማንበብ (በአካል የተገኛኙ ወይም ስልክን የሚጠቀሙ ከኾነ) ወይም የግንኙነት ፕሮግራሞችን የሚጠቀሙ ከኾነ ቀድተው በመለበድ ሊኾን ይችላል። የትኛውንም ዓይነት መንገድ ቢጠቀሙ እያንዳንዳቸው የቁልፉ ሆሄያት እና ቁጥሮች ተመሳሳይ መኾናቸውን ማጣራት አስፈላጊ ነው።

  ከቅርብ ጓደኛችሁ ጋር የቁልፍ ማረጋገጥን በተግባር ተለማመዱ። የቁልፍ ማረጋገጫ በእያንዳንዱ ፕሮግራም ላይ እንዴት እንደሚሠራ ለመማር የየፕሮግራሙን መመሪያ ተመልከቱ።

  Last reviewed: 
  2015-02-10
 • ለማክ የOTR አጠቃቀም

  አዲየም  ነጻ እና ክፍት ምንጨ ኮድ ለOS X የተሠራ የፈጣን መልዕክት ደምበኛ ሲኾን የተለያዩ የመስመር ላይ ውይይት ማድረጊያ ስርዓቶችን ማለትም ጎግል ሃንግአውት፣ ያሁ፣ ሜሴንጀር፣ ዊንዶውስ ላይቭ ሜሴንጀር፣ AIM፣ ICQ፣ እና XMPPን በመጠቀም የመስመር ላይ ውይይት እንዲያደርጉ ይረዳል።

  OTR (ኦፍ-ዘ-ሪከርድ) የሚባለው ሰዎች የሚያውቋቸውን የፈጣን መልዕክት መሣሪያዎች በመጠቀም ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ውይይት እንዲያደርጉ የሚያስችል ስርዓት ነው። ይህ ከጎግል “ከምዝገባ ውጪ” የሚደረግ ውይይት ጋር መምታታት የለበትም። የጎግል ከምዝገባ ውጪ የሚያደርገው መወያያዎን አለማስቻል ሲኾን ውይይቱን የማመስጠር ወይም የውይይቱን ተሳታፊዎች የማመሳከር አቅም የለውም። ለማክ ተጠቃምዎች OTR ከአዲየም ደምበኛ ጋር አብሮገነብ ኾኖ ይመጣል።

  OTR ከዳር እስከ ዳር የኾነ ምስጠራን ይጠቀማል። ይህም ማለት ይህን በመጠቀም እንደ ጎግል ሃንግ አውት ያሉ አግልግሎቶች ላይ ኩባንያዎቹ የግንኙነትዎ ይዘት ምን እንደኾነ ማወቅ ሳይችሉ ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ ማለት ነው። ይህም መወያያዎን ከማያስችለው “ከምዝገባ ውጪ” ብለው  ጎግል  እና   AOL  ከሚጠቀሙት የተለየ ነው። ይህ ምርጫ ውይይቱን የማመስጠር አቅም የለውም።

  አዲየም እና OTRን በአንድ ላይ ለምን መጠቀም አለብኝ?

  የሃንግአውትን ወይም ድረ ገጽን በመጠቀም የጎግል ሃንግአውት ወይም የጽሑፍ ውይይት በሚያደርጉበት ወቅት ውይይቶ በHTTPS የተመሰጠረ ነው። ይህ ማለት የውይይትዎ ይዘት በዝውውር ላይ እያለ ከሰርጎ ገቦች እና ከሌላ ሦስተኛ ወገን የተጠበቀ ነው ማለት ነው። ነገር ግን የውይይትዎ ቁልፍ ካላቸው ከጎግል እይታ የተጠበቀ ነው ማለት አይደለም። እነርሱም የግንኙነትዎን ይዘት ለመንግሥት አሳልፈው ሊሰጡ ይችላሉ።

  አዲየምን በኮምፒውተርዎ ላይ ከጫኑ በኋላ በተመሳሳይ ሰዓት የተለያዩ መለያዎችን በመጠቀም መግባት ይችላሉ። ለምሳሌ ጎግል ሃንግአውትን፣ እና XMPPን በተመሳሳይ ጊዜ መጠቀም ይችላሉ። በተጨማሪም አዲየም OTRን ሳይጠቀሙ እነኚህን መሳሪያዎች በመጠቀም እንዲወያዩ ይፈቅዳል። OTR የሚሠራው በሁለቱም ወገን ያሉ ሰዎች ሲጠቀሙት ብቻ ነው። ይህ ማለት በሌላ ዳር ያለው ግለሰብ OTRን በኮምፒውተሩ ላይ ካልጫነ አዲየምን በመጠቀም ውይይት ማድረግ ይችላሉ።

  በተጨማሪም አዲየም የሚያወሩት ሰው እያወራሁት ነው ብለው የሚያስቡት ሰው እንደኾነ እና በመሃል ለሰርጎ ገብ ሰው ጥቃት ያልተጋለጡ መኾንዎን የሚያስረግጥ ከመስመር ውጪ የኾነ ማረጋገጫን እንዲያደርጉ ይፈቅዳል። ለእያንዳንዷ ውይይት ለእርስዎ እና እየተወያዩት ላለው ሰው ያለውን የቁልፍ የጣት አሻራ ማየት የሚያስችል ምርጫ ይሰጥዎታል። “ቁልፍ የጣት አሻራ” ማለት የተለያዩ ምልክቶች ለምሳሌ እንደዚህ ያለ “342e 2309 bd20 0912 ff10 6c63 2192 1928” ሲኾን ይህም ረዘም ያለ የአደባባይ ቁልፍን ለማረጋገጥ የሚጠቅም ነው። ከማን ጋር እንደሚወያዩ ለማወቅ እና በውይይትዎ ውስጥ ጣልቃ ገቦች እንደሌሉ ለማጣራት የጣት አሻራዎን ሌላ የመገናኛ ዘዴ በመጠቀም ማለትም በትዊተር የቀጥታ መልዕክት ወይም በኢሜል ይቀያየሩ።

  ውስንነቶች፦ አዲየም እና OTRን መጠቀም የሌለብኝ መቼ ነው?

  ቴክኖሎጂስቶች አንድ ፕሮግራም ወይም ቴክኖሎጂ ለውጭ ጥቃት ተጋላጭነቱን ለመግለጽ የሚጠቀሙበት ቃል አለ። ይህም ቃል ትልቅ “የጥቃት ገጽታ” አለው የሚል ነው። አዲየምም ትልቅ የጥቃት ገጽታ አለው። በጣም የተወሳሰበ ፕሮግራም ያለው ቢኾንም የጻፈው ደህንነት ቅድሚያ ባላደረገ መርህ ነው። በርግጠኝነት የተለያዩ ስህተቶች ያሉበት ሲሆን ከነኚህም ጥቂቶቹ ስህተቶች በመንግሥታት ወይም በትልልቅ ኩባንያዎች አዲየምን የሚጠቀሙ ኮምፒውተሮችን ሰብሮ ለመግባት ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ውይይትዎን ለመደበቅ እና ሁሉንም ሰው ከሚያጠቃ ያልተነጣጠረ የኢንተርኔት የመስመር ላይ ስለላ ራስን ለመከላከል አዲየምን መጠቀም ታላቅ የመከላከያ ዘዴ ነው። ነገር ግን በግል አቅም ካለው አካል ለምሳሌ የመንግሥታት የጥቃት ዒላማ እንደሚኾኑ ከተሰማዎት ጠበቅ ያለ ጥንቃቄ መውሰድ ለምሳሌ በPGP የተመሰጠረ የኢሜል ስርዓት መጠቀም ይኖርብዎታል።

  አዲየምን እና OTRን በማክ ኮምፒውተርዎት ላይ መጫን

  አንደኛ ደረጃ፦ ፕሮግራሙን መጫን

  በመጀመሪያ በድር መዳሰሻዎ https://adium.im/ የሚለውን ይክፈቱ። “ዳውንሎድ አዲየም 1.5.9.” የሚለውን ይምረጡ። ፋይሉ እንደ a .dmg፣ ወይም ዲስክ ኢሜጅ ይወርድ እና አብዛኛውን ጊዜ በ“ዳውንሎድ” አቃፊ ውስጥ ይጠራቀማል።

  ፋይሉ ላይ ሁለቴ ጠቅ ሲያደርጉ ይህን የሚመስል አዲስ መስኮት ይከፈታል፦

  ፕሮግራሙን ለመጫን የአዲየም አዶን ወደ “አፕሊኬሽን” አቃፊ ይውሰዱት። ፕሮግራሙ አንዴ ከተጫነ በኋላ በአፕሊኬሽን አቃፊው ውስጥ ይፈልጉት እና ሁለቴ ጠቅ በማድረግ ይክፈቱት።

  ሁለተኛ ደረጃ፦ መለያዎ(ችዎ)ን ማዋቀር

  በመጀመሪያ ከአዲየም ጋር የትኛውን የጽሑፍ ውይይት መሣሪያ ወይም ስርዓት መጠቀም እንደሚፈልጉ መወሰን አለብዎት። ለእያንዳንዱ መሣሪያ የማዋቀር ሂደቱ ተመሳሳይ ቢኾንም ፈጽሞ አንድ አይነት ግን አይደለም። ለእያንዳንዱ መሣሪያ ወይም ስርዓት የመለያ ስምዎትን እንዲሁም የማለፊያ ቃልዎን ማወቅ ይኖርብዎታል።

  መለያን ለማዋቀር በስክሪንዎ የላይኛው ክፍል ወደ ሚገኘው የአዲየም ምናሌ ይሂዱ እና “አዲየም” ላይ በመቀጠልም “ፕሪፈረንስ” ላይ ጠቅ ያድርጉ። ይህም ከላይ ሌላ ምናሌ ያለው መስኮት ይከፍታል። “አካውንትስ” ከመረጡ በኋላ በመስኮቱ የታችኛው ክፍል የሚገኘው የ“+” ምልክት ላይ ጠቅ ያድርጉ። ይህን የሚመስል ምናሌ ያያሉ፦

  መግባት የሚፈልጉበትን ፕሮግራም ይምረጡ። ከዚህ በመቀጠል የተጠቃሚ ስምዎን እና የማለፊያ ቃልዎን እንዲያስገቡ ወይም የአዲየምን የፈቃድ መሣሪያ በመጠቀም ወደ መለያዎ እንዲገቡ የሚጠይቅ ይመጣልዎታል። የአዲየም መመሪያን በጥንቃቄ ይከተሉ።

  የOTR ውይይትን ማስጀመር

  አንዴ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የኾነ መለያዎት ውስጥ ከገቡ በኋላ OTRን መጠቀም መጀመር ይችላሉ።

  ያስታውሱ: OTRን ተጠቅመው ውይይት ለማድረግ ሁለቱም ሰዎች OTRን የሚደግፍ ውይይት የማድረጊያ ፕሮግራም መጠቀም አለባቸው።

  አንደኛ ደረጃ፦ የOTR ውይይት ማስጀመር

  በመጀመሪያ OTR ተጠቃሚን ለይተው ይወቁ እና አዲየም ውስጥ ስማቸው ላይ ሁለቴ ጠቅ በማድረግ ውይይት ይቀስቅሱ። የመወያያ መስኮቱን አንዴ ከከፈቱ በኳላ በመስኮቱ ግራ የላይኛው ክፍል ላይ ትንሽ የተከፈተ የቁልፍ ምልክት ያያሉ። በቁልፍ ምልክቱ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና “ኢንሼት ኢንክሪፕትድ OTR ቻት” የሚለውን ይምረጡ።

  ሁለተኛ ደረጃ፦ ግንኙነትዎን ያረጋግጡ

  አንዴ ውይይቱን ካስጀመሩ እና በሌላ ዳር ያለው ሰውም ግብዥዎትን ከተቀበለ በኋላ የቁልፍ አዶቱ ተዘግቶ ያዩታል። ውይይትዎ ሚስጥራዊ እንደሚኾን የሚያውቁት በዚህ ነው (እንኳን ደስ ያለዎት!) ነገር ግን ይጠብቁ ገና ሌላ ተጨማሪ ደረጃ አለ!

  በዚህ ወቅት የተመሰጠረ ነገር ግን ያልተረጋገጠ ውይይት ማስጀመርዎትን ልብ ያድርጉ። ይህ ማለት ግንኙነትዎ የተመሰጠረ ቢኾንም ውይይት እያደረጉት ያለውን ሰው ማንነት ማወቅ እና ማረገገጥ ግን ገና አልቻሉም። በአንድ ክፍል ውስጥ ኾነው አንዱ የሌላኛውን ስክሪን ማየት እስካልቻለ ድረስ አንዱ የአንዱን ማንነት ማረጋገጡ በጣም አስፈላጊ ነው። ለተጨማሪ መረጃ የቁልፍ ማረጋገጫ የሚለውን ሞጁል ያንብቡ።

  አዲየምን በመጠቀም የሌላ ተጠቃሚን ማንነት ለማረጋገጥ በቁልፍ አዶው ላይ እንደገና ጠቅ በማድረግ “ቬሪፋይ” የሚለውን ይምረጡ። የእርስዎን ቁልፍ እና የሌላኛውን ተጠቃሚ ቁልፍ የሚያሳይ መስኮት ያያሉ። አንዳንድ የአድየም ሥሪቶች በእጅ የሚደረግ የጣት አሻራ ማረጋገጫን ብቻ ይደግፋሉ። ይህ ማለት አንዳንድ ዘዴዎችን በመጠቀም እርስዎ እና ከእርስዎ ጋር ውይይት እያደረገ ያለው ሰው አዲየም እያሳያችሁ ያለው ቁልፍ በትክክል አንድ ዓይነት መኾኑን አጣርታችሁ ማረጋገጥ አለባችሁ ማለት ነው።

  ይህን ለማድረግ ቀላሉ መንገድ በአካል በመገናኘት አንዱ ለሌላኛው ቁልፉን ማንበብ ቢኾንም ይህን ማድረግ ሁልጊዜ አይቻልም። የተለያያ ዕምነት የሚጣልበት ደረጃ ያላቸው ይህን መፈጸም የሚያስችሉ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ አንዱ የሌላኛውን ድምጽ መለየት የሚችል ከኾነ በስልክ ግንኙነት ቁልፉን አንዱ ለሌላኛው በማንበብ ወይም ሌላ እንደ PGP ያለ የተረጋገጠ የግንኙነት መንገድ በመጠቀም ቁልፉን መላክ ነው። አንዳንድ ሰዎች ቁልፋቸውን በድረ ገጻቸው፣ በቲዊተር መለያቸው፣ ወይም በንግድ ካርዳቸው ላይ ለሕዝብ ያሳውቃሉ።

  በጣም አስፈላጊው ነገር እያንዳንዱ የቁልፉ ፊደል እና ቁጥር ትክክለኛ እንደኾነ ማረገገጥ ነው።

  ሶስተኛ ደረጃ፦ መግባትን አለማስቻል

  አሁን ሚስጥራዊ የኾነ ውይይትን ካነሳሱ እና የውይይት አጋሮን ማንነት ከረጋገጡ በኋላ ማድረግ የሚጠበቅብዎት አንድ ተጨማሪ ነገር አለ። ያለመታደል ኾኖ አዲየም በነባሪው በOTR የተመሰጠረውን ውይይትዎትን ያስገባና እና በሃርድ ድራይቭዎ ላይ ያጠራቅመዋል።ይህም ማለት ግንኙነትዎችዎን በትክክል የመሰጠሩ ቢኾኑም እንኳን በሃርድ ድራይቮ ላይ በግልጽ ጽሑፍ ይጠራቀማሉ ማለት ነው።

  መግባትን ላለማስቻል በስክሪኑ በላይኛው ክፍል ከሚገኘው ምናሌ “አዲየሚ” የሚለው ላይ በመቀጠልም “ፕሪፈረንስ” ላይ ጠቅ ያድረጉ። በአዲሱ መስኮት ላይ “ጀነራል” የሚለውን ይምረጡ እና “ሎግ ሜሴጅስ” እና “ሎግ OTR-ሴኪዩርድ ቻትስ” የሚለውን ያቦዝኑ። አሁን መዋቅሮ ይህንን መምሰል አለበት፦

  በተጨማሪም አዲየም የአዲስ መልዕክቶች መምጣትን በሚያሳውቅበት ወቅት የእነዚህ መልዕክቶች ይዘት በOS X ኖትፊኬሽን ማዕከል ሊገባ ይችላል። ይህ ማለት አዲየም በእርስዎ ኮምፒውተር ወይም በሌላ ዳር ካለው የውይይት አጋሮዎት ምንም ዓይነት የግንኙነት ምልክቶችን ባይተውም እንኳ የእርስዎ ወይም በሌላ ዳር ያለው ሰው የOS X ኮምፒውተር ስሪት መዝግቦ ሊያስቀምጥ ይችላል። ይህንን ለመከላከል ኖትፊኬሽንኑን ማቦዘን ይችላሉ።

  ይህን ለማድረግ ከፕሪፈረንስ መስኮት “ኢቨንትስ” የሚለውን ይምረጡ እና “ዲስፕለይ ኤ ኖቲፊኬሽን” የሚል ማሳያ ይፈልጉ። ለእያንዳንዱ መግቢያ አመድማ ቀለም ያለው ባለሦስት ጎን ምልክት ላይ ጠቅ በማድረግ በስፋት እንደ አዲስ በሚታየው መስመር “ዲስፕሌይ ኤ ኖቲፍኬሽን” በሚለው ጽሑፍ ላይ ጠቅ ያድርጉ። በመቀጠልም በታችኛውን የግራ ክፍል የሚገኘው የመቀነስ ምልክት ("-") ላይ ጠቅ በማድረግ መስመሩን ያስወግዱ። በኮምፒተርዎት ላይ የሚቀሩ መዝገቦች እና ሰነዶች ሌላ ሰው እንዳያገኘው የሚፈልጉ ከኾነ ሙሉ የዲስክ ማመስጠርን ያስጀምሩት። ይህም ከማለፊያ ቃልዎ ውጪ ውሂቡ በሦስተኛ ወገን እንዳይገኝ ይረዳዎታል።

  Last reviewed: 
  2017-01-19
 • ለማክ OS X የPGP አጠቃቀም

  እጅግ የተሳካለት ግለሚስጥር ወይም ፕሪቲ ጉድ ፕራይቬሲ (PGP) የተባለው የኢሜል ግንኙነትዎ ከታቀደለት ተቀባይ ግለሰብ በስተቀር በሦስተኛ አካል እንዳይነበብ የሚከላከል ስርዓት ነው። በተጨማሪም ኮምፒውተርዎ ቢሰረቅ ወይም ቢሰበር በኮምፒተርዎ ላይ የተጠራቀሙት ኢሜሎችዎ እንዳይመዘበሩ ይከላከላል።

  ከአንድ ግለሰብ የተላከልዎት ኢሜል በትክክል ከሚያውቁት ግለሰብ ወይም ከሦስተኛ አካል የተላከ የሀሰት መልዕክት መኾኑን ወይም አለመኾኑን ለማረጋገጥ ሊያገለግል ይችላል (ይህ ካልኾነ እውነተኛ የሚመስል ኢሜል በቀላሉ ሊፈጠር ይችላል)። ለስለላ እና የማሳሳት ዘመቻ ዒላማ የሚኾኑ ከኾነ እነዚህ ሁለቱም በጣም አስፈላጊ መከላከያ ናቸው።

  PGPን ለመጠቀም አሁን ከሚጠቀሙበት የኢሜል ፕሮግራም ጋር አብረው የሚሠሩ ተጨማሪ ሶፍትዌሮችን መጫን ይጠበቅብዎታል። በተጨማሪም በግልዎ የሚይዙት የግል ቁልፍ መፍጠር አለብዎት። ይህ የግል ቁልፍ የተላከልዎትን ሚስጥራዊ ኢሜል ለመፍታት እንዲሁም የሚልኳቸውንም በእርግጥም እርሶ እንደላኳቸው ለማሳየት የዲጂታል ፊርማ ለመፈረም የሚጠቀሙበት ነው። በመጨረሻም የአደባባይ ቁልፍዎን እንዴት እንደሚያጋሩ ይማራሉ። የአደባባይ ቁልፍ ሌሎች ሰዎች ለእርስዎ ሚስጥራዊ ኢሜልን ከመላካቸው በፊት ሊያውቁት የሚገባ እና እርሶ የሚልኩትንም እንዲሁ የሚያረጋግጡበት ቅንጣቢ መረጃ ነው።

  ይህ መመሪያ የማክን አብሮገነብ ሜል (built-in Mail) ፕሮግራም ወይም አማራጭ ዝነኛ የኢሜል ፕሮግራም በኾነው በሞዚላ ተንደርበርድ PGPን በአፕል ማክ (በአይፓድ ወይም አይፎን አይደለም) ላይ እንዴት እንደሚጠቀሙ ያሳይዎታል።

  እንደ ጂሜል፣ ሆትሜል፣ ያሁ! ሜል ወይም አውትሉክ ላይቨ ባሉት የድር ኢሜል አገልግሎት ላይ PGPን በቀጥታ መጠቀም አይችሉም። ይኹንና የዌብሜል እድራሻዎን በኮምፒውተርዎ ላይ ካለው ዌብሜይል ወይም ከተንደርበርድ ፕሮግራም ጋር በማዋቀር መጠቀም ይችላሉ።

  ያስተውሉ ይህ እንዲሠራ በሁለቱም የኢሜል ልውውጥ ዳር ያሉ ሰዎች ከPGP ጋር ተኳኋኝ የኾነ ሶፍትዌር መጠቀም ይኖርባቸዋል።

  በመደበኛነት ግለሰቦች ይህን የሚጠቀሙት ከማንኛውም ግለሰብ ጋር በማይጋሩት የራሳቸው ግላዊ መሣሪያዎች ላይ ነው። ጥሩነቱ PGP ለብዙ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች እና ተንቀሳቃሽ ስልኮች ተኳኋኝ ኾኖ ይገኛል። የራሳቸውን ስሪት እንዲያዋቅሩ እንዲረዳቸው ይህንን መመሪያ ይጠቁሟቸው። ይህ መመሪያ ለማክ ተጠቃሚዎች የሚያገለግል ነው።

  በማክ ኮምፒውተርዎ ላይ የGPG መሳሪያዎችን መጫን

  PGP ከአንድ በላይ የኾኑ ሶፍትዌሮች እንዲጠቀሙበት ተደርጎ የተፈጠረ ተኳኋኝ ሶፍትዌር ነው። ለPGP የምንጠቀመው ሶፍትዌር ከGPG መሳሪያዎች በማክ ኮምፒውተሮች ላይ የሚሠራውን GPG ስዩት በመባል የሚታወቀውን አንዱን ስንጥር ነው። ይህም ሶፍትዌር ማንኛውም ሰው እንዲጠቀመው ከክፍያ ነጻ የኾነ ምንጨ-ክፍት ነው። ይህ ማለት ማንኛውም ግለሰብ ህጸጹን እና መምጫውን ለማጣራት ሶፍትዌሩ የተሠራበትን ምንጨ-ኮድ ማግኘት ይችላል።

  አንዴ የGPG ስዩት ከተጫነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቁልፍዎን ማዋቀር፤ በመቀጠልም PGPን በአፕል ሜል እና በአማራጭነት በተንደርበርድ እንዲተገበር ማድረግ ይችላሉ።

  አንደኛ ደረጃ፦ ፕሮግራሙን ይጫኑ።

  በመጀመሪያ በድር መዳሰሻዎ ወደዚህ ገጽ ይሂዱ https://www.gpgtools.org/ እና “ዳውንሎድ GPG ስዩት” የሚለውን ይምረጡ።

  ጠቅ በማድረግ ሶፍትዌሩን ለመጫን የሚያችልዎትን የዲስክ ኢሜጅን ያገኛሉ። በኮምፒውተርዎ ላይ የሦስተኛ ወገን ሶፍትዌር የመጫን ልምድ ከሌለዎት በአቅራቢያዎ የሚገኝ የማክ አዋቂን ይጠይቁ። የቴክኖሎጂ ባለሞያዎቹ ስለ PGP ወይም ምስጢራዊነት ምንም ዕውቀት ባይኖራቸው እንኳ እርስዎን ለማገዝ አያዳግታቸውም።

  ኢንስቶል የሚለውን ጠቅ ማድረግ በኮምፒውተርዎ ላይ የሚጨመሩትን መሣሪያዎች ዝርዝር ይሰጥዎታል።

  እየጫንኩ ያለሁት ነገር በትክክል ምንድን ነው?

  እነዚህ አጋዥ መሣሪያዎች በማክ ኮምፒውተርዎ ከአንድ በላይ የኾኑ ፕሮግራሞች PGPን መጠቀም እዲችሉ አብዛኛውን ጊዜ ከመጋረጃ በስተጀርባ የሚሠሩ ናቸው። እነዚህንም በቀጥታ ከሚጠቀሟቸው መተግበሪያዎች ይልቅ ሌሎች ፕሮግራሞች መጠቀም የሚችሏቸው ፕሮግራሞች እንደኾኑ ያስቧቸው። GPGሜል የተባለው አፕል ሜል የPGP ኢሜልን እንዲልክ እና እንዲያነብ ያደርጋል። GPG ኪይቼን አክሰስ የተባለው በማክዎ ላይ ሌሎች የማለፊያ ቃላትዎን በሚያስቀምጡበት ተመሳሳይ ስርዓት የግል እና የአደባባይ ቁልፎችዎን ያኖርልዎታል። GPG ሰርቪስ ከኢሜል ሌላ ፕሮግራሞች (ለምሳሌ ወርድ ፕሮሰሰር ) ላይ PGPን መጠቀም የሚያስችልዎት በOS X ላይ በምርጫ የኾነ ገጽታ ይጨምርልዎታል። GPGፕሪፈረንስ በአፕል ምርጫ ላይ የPGPን መዋቅር እንዲቀይሩ ያደርጋል። በመጨረሻም ማክGPG2 የተባለው ደግሞ ማንኛውም ፕሮግራም ሚስጥራዊነትን ወይም ፊርማን እንዲከውን የሚያግዝ መሰረታዊ መሣሪያ ነው።

  በጥቅምት 2007 የGPG መሣሪያዎች ቡድን እንዳስታወቀው GPGን ከአፕል ሜል መተገበሪያ ጋር እንዲጠቀሙ የሚረዳዎትን እና ከጥቅሎቻቸው አንዱ ክፍል የኾነውን GPGሜል በቅርቡ እንደሚቀይር አስታውቋል።  ይህ አጋዥ ስልጠና GPGን ከተንደርበርድ ጋር ስለመጠቀም ስለኾነ እነዚህን ምንዝሮችን አይጠቀምም።.  የGPG ስዩትን ክፍል የኾነውን ዚሮ-ኮስት መጠቀም ይችላሉ።  በተጨማሪም እነዚህ አጋዥ መሳሪያዎች ሁሉም “ነጻ ሶፍትዌር” ስለኾኑ በነጻ ሶፍትዌር መንፈስ GPGሜል የተሳራበትን ምንጭ ኮድ በነጻነት መመርመር፣ ማስተካከል እና ማከፋፈል ይችላሉ።  ለተጨማሪ መረጃ ውሳኔያቸውን በተመለከት የGPG ቱልስ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው ይመልከቱ።

  GPG ስዩትን ለመጫን “ኮንቲኒው” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

  የመጫን ሂደቱ እንደተጠናቀቀ የGPG ኪይቼን (የቁልፍ ማህደር) በቀጥታ ተከፍቶ የPGP ቁልፍዎን እንዲያመርቱ ይጠይቅዎታል። ይህ ካልኾነ ግን ወደ ትግበራ ማህደር ሄደው ይክፈቱት።  የPGP ቁልፍዎን ለመፍጠር “ኒው” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

  አሁን የግል እና ይፋዊ ቁልፎች መፍጠር ይጀምራሉ፡፡ የአደባባይ ቁልፎች ስነ መሰውር እና PGP መግቢያ የተሰኘው መመሪያችን ላይ ስለቁልፎች ምንነት ለመረዳት የተጻፈውን ያንብቡ፡፡

  ሁለተኛ ደረጃ፦ የPGP ቁልፍዎን መፍጠር

  አንዳንድ ጊዜ አዲስ ሶፍትዌርን ሲጭኑ ኮምፒውተርዎ እንዴት መመለስ እንዳለብዎት ምክር ሳይሰጥ ግልጽ የኾነ መልስ በሌላቸው ጥያቄዎች ይነዘንዝዎታል። ይህ ያንን ያሚያስታውሱበት ጊዜ ነው።

  አፍታ ወስደው ምን መልስ እንደሚሰጡ ይመከራሉ። ምክንያቱም ዘግይቶ የPGP ቁልፍዎን ዝርዝር መቀየር ከባድ ሊኾን ስለሚችል እና ቁልፍዎን የኾነ ቦታ እንዲታተም ከመረጡ በኋላ እትሙን መቀልበስ ስለማይችሉ ነው። (በሺዎች የሚቆጠሩ እየተንሳፈፉ ያሉ የ1990 አሮጌ ተጣማሪ ቁልፎች ከፈጠሯቸው ሰዎች ስም እና አሮጌ ኢሜል አድራሻ ጋር አሉ።)

  የPGP ቁልፎች ቁልፉን ከእርሶ ጋር የሚያያይዙ ስም እና የኢሜል አድራሻ ይይዛሉ። የኢሜል አድራሻው ሌሎች ግለሰቦች ለእርስዎ መልዕክት ሲያመሰጥሩ የትኛውን ቁልፍ መጠቀም እንዳለባቸው የሚያውቁበት አንዱ መንገድ ነው።

  መቼ ነው እውነተኛ ስሜን እና የኢሜል አድራሻዬን በPGP ቁልፌ ላይ መጠቀም የሌለብኝ? ቁልፌን መጫን የሌለብኝስ መቼ ነው?

  ብዙ ተጠቃሚዎች እውነተኛ የኢሜል አድራሻን በቁልፍዎ ላይ መጨመርዎ እንዲሁም እርስዎን ከትክክለኛው ቁልፍ ጋር የሚያዛምዱበትን ተጣማሪ ቁልፍ አገልጋይ ላይ መጫን ትርጉም ይሰጣቸዋል። በቀጥታ የኢሜል መልዕክት ሊሰዱልዎ ከዛም አልፎ በትክክለኛው ቁልፍ የተሰወረ መኾኑን ማወቅ ይችላሉ። የተፈረመበት ኢሜል ከእርስዎ ሲቀበሉም የዲጂታል ፊርማው የስምዎ ምልክት ያለበት ይኾናል።

  ይኹንና ለአንዳንድ ሰዎች እውነተኛ ስማቸውን በቁልፋቸው ላይ ማኖር ትርጉም አይሰጣቸውም። ለምሳሌ የስጋት ሞዴልዎ የእርሶን ማንነት (እና የኢሜል አድራሻዎን) ከቁልፎ ጋር መያያዝን የሚጨምር ከኾነ ይህ መልካም ሃሳብ አይደለም። ኤድዋርድ ስኖውደን ማንነቱን ከመገለጡ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ሲገናኝ የነበረው PGP እና ስምአልባ የኢሜል አድራሻን በመጠቀም ሲኾን የPGP ቁልፉም በእርግጠኝነት የስሙ ምልክት አልነበረውም።

  ቁልፍዎን መጫን የተለመደ ተግባር ነው። ይኹንና የራስዎን ስም ባይጠቀሙም እንኳ ምስጢራዊነትን እንደሚጠቀሙ ሊያጋልጥ ይችላል። በተጨማሪም እንደምናየው ሌሎች ሰዎች የእርሶን ቁልፍ ይጭኑና ከራሳቸው ቁልፍ ጋር ሊያዛምዱት ይችላሉ። ይህም ከእርሶ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ሊያሳይ ይችላል። ይህንን ግንኙነት ሰዎች እንዲያውቁት የማይፈልጉ ከኾነ ጉዳት ሊያመጣብዎ ይችላል። ምናልባትም ደግሞ ግንኙነት የሌለዎት ሊኾኑ ይችላሉ። አጥቂዎ ግን ሰዎች ዝምድና እንዳለዎት እንዲያስቡ የሚፈልግ ከኾነ አደገኛ ሊኾን ይችላል።

  ምጥን መመሪያ ይኅውልዎ፦ በአጠቃላይ የተለየ የውል ስም ለመጠቀም የሚያስቡ ከኾነ ቁልፍዎን በሚፈጥሩበት ወቅት ያንን የውል ስም (እና ተለዋጭ ኢሜል) ይጠቀሙ። በጣም አደገኛ የኾነ አካባቢ የሚኖሩ ከኾነ ሰዎች በጭራሽ PGPን እንደሚጠቀሙ ወይም ከማን ጋር ግንኙነት እንደሚያደርጉ እንዳያውቁ የሚፈልጉ ከኾነ ቁልፍዎን በአደባባይ የቁልፍ አገልጋይ ላይ አይጫኑ። በተጨማሪም የሚያገኙት ቡድን ስብስብ የእርስዎን ቁልፍ መጫን እንደሌለበት ግንዛቤው እንዳለው ያረጋግጡ። የቁልፍዎን በተጣማሪ የቁልፍ አገልጋይ ላይ መገኘትን የማይጠይቁ ሌሎች የቁልፍ ማረጋገጫ መንገዶች አሉ። እነርሱንም ለማየት የቁልፍ ማረጋገጫን ይመልከቱ።

  ሌሎች በቀላሉ ቁልፍዎን አግኝተው ሚስጥራዊ መልዕክት እንዲሉኩልዎ ከፈለጉ “አፕ ሎድ ፐሊክ ኪይ አፍተር ጀነሬሽን” የሚለውን ሳጥን ጠቅ ያድረጉ። ይህም ልክ የስልክ ቁጥርዎን በአደባባይ የስልክ መዝገብ ላይ እንደማኖር ነው። ለእርስዎ ባያስፈልግም ለሌሎች ግን ለአጠቃቀም ምቹ ነው።

  ቁልፉን ከማምረትዎ በፊት “አድቫንስድ ኦፕሽንስ” የሚለውን ያስፉ። የአስተያያት መስጫውን ባዶውን ይተውት፣ በመቀጠልም የቁልፍ ዓይነቱን በነባሪው “RSA ኤንድ RSA (ዲፎልት)” እንደኾነ ይተውት። ነገር ግን የመጠን (ሌንግዝ) መስኩን ወደ 4096 መቀየርዎን ያረጋግጡ።

  ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የቁልፍዎ የአገልግሎት ዘመን ያበቃል። ይህ በሚኾንበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ለእርሶ በሚልኳቸው አዳዲስ ኢሜልዎች ቁልፉን መጠቀም ያቆማሉ። ይህ ለምን እንደኾነ ማስጠንቀቂያ ወይም ማብራሪያ ላያገኙ ይችላሉ። ስለዚህ በቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ማድረግ እና የቁልፉ አገልግሎት ዘመን ከሚያበቃበት ከወር ወይም ቀደም ብሎ ለጉዳዩ ትኩረት መስጠት ይጠበቅብዎታል።

  ነባሩን ቁልፍ አዲስ የወደፊት የአገልግሎት ዘመን ማብቂያ በመስጠት እና የእድሜ ዘመኑን በማራዘም ወይም ከመነሻው አዲስ ቁልፍን በመፍጠር ነባሩን ቁልፍ መቀየር ይቻላል። በሁለቱም ሂደቶች PGPን ተጠቅመው ኢሜል የሚልኩልዎትን ግለሰቦች ማግኘት እና የተቀየረውን ቁልፍ እጃቸው ማስገባታቸውን ማረጋገጥ ሊያስፈልግዎ ይችላል። የአሁን ሶፍትዌሮች በራስ ሰርነት እምብዛም አይደሉም። ስለዚህ ለራስዎ ማስታወሻ ያኑሩ። ይህን መተግበር የሚችሉ ካልመሰለዎት ደግሞ የቁልፉ የአገልግሎት ዘመን እንዳያበቃ አድርገው ማቀናበርን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ይህን ካደረጉም ለወደፊቱ የግል ቁልፍዎ ቢጠፋብዎት ወይም PGPን መጠቀም ቢያቆሙ ከብዙ ጊዜ በኋላ ሌሎች ሰዎች ከእርስዎ ጋር ለመገናኘት ሊጠቀሙት ይችላሉ።

  ዝግጁ ሲኾኑ “ጀነሬት ኪይ” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

  ኮምፒውተርዎ ሁለቱንም ማለትም የአደባባይ እና የግል ቁልፍዎን መፈብረክ ይጀምራል። ፈብርኮ ለመጨረስ ከጥቂት ደቂቃዎች በላይ መውሰድ የለበትም። (ጥቂት ጊዜን የሚወስደው ቁልፍዎን ለመፈብረክ ኮምፒውተርዎ የተለያዩ ቁጥሮችን ስለሚሰበስብ ነው። ይህንንም ኮምፒውተርዎ ባለ ስድስት ገጽ ጠጠርን (ዳይስ) እጅግ በጣም ብዙ ጊዜ ሲወረውር አድርገው አስቡት።)

  ቁልፍዎን አምርተው ሲጨርሱ በGPG ኪይቼን አክሰስ (የቁልፍ ማኖሪያ ጎታ) ውስጥ ቁልፉ ተዘርዝሮ ያዩታል። በቁልፍዎ ላይ ሁለቴ ጠቅ በማድረግ የPGP ቁልፍዎን በልዩ መንገድ የሚለዩበትን “የጣት አሻራውን” ጨምሮ ማየት ይችላሉ። (ይህን ለማየት የቁልፍ ማረጋገጫ ይመልከቱ)።

  አሁን የመሻሪያ ምስክር ወረቀት ለማተም መልካም ጊዜ ነው።

  ወደፊት የግል ቁልፍዎ በሌላ ሰው እንደተቀዳ ጥርጣሬ የተሰማዎት ከኾነ በአጋጣሚ የግል ቁልፍዎን የሰረዙት ወይም የጣሉት እንደኾነ ወይም የይለፍ ሐረግዎን የረሱ እንደኾነ የመሻሪያ ምስክር ወረቀትን በመጠቀም ለሁሉም ሰው ቁልፉ የተሻረ ወይም የተሰረዘ መኾኑን መንገር ይችላሉ።

  የመሻሪያ የምስክር ወረቀት ለማተም የግል ቁልፍ እና የይለፍ ሐረግ ሲለሚያስፈልግዎ አሁኑኑ አንድ መፍጠሩ የተሻለ ነው። በኋላ ለመፍጠር አስበው ችላ ካሉት ግን እንደኛውን ወይም ሌላኛውን ይጥሉትና ዘግይቶ መፍጠር አይችሉም። ስለዚህ የምስክር ወረቀቱን ለማተም ቁልፍዎ ላይ ጠቅ በማድረግ የ“ኪይ” መግቢያ ምናሌን በመቀጠልም “ክሬት ሪቮኬሽን ሰርትፊኬት”ን ይምረጡ። ሰነዱን እንዲያስቀምጡ የሚጠይቅ ይመጣልዎታል። የቁልፉን የመጠባበቂያ ቅጂ ማስቀመጥ ሊያስፈልግዎት ይችላል (የሚከተለውን ደረጃ ይመልከቱ)።

  ሦስተኛ ደረጃ፦ የPGP ቁልፍዎን መጠባበቂያ ያስቀምጡ

  የግል ቁልፍዎን መጠቀም የማይችሉ ከኾነ አዲስ የሚመጣልዎትን ማንኛውንም የPGP ሜል ወይም ድሮ የተላከልዎትን ኢሜሎች መፍታት እይችሉም። በሌላ በኩል ደግሞ የግል ቁልፍዎን ደህንነት በተቻልዎት አቅም መጠበቅ ይኖርብዎታል።

  በጥንቃቄ በሚያስቀምጡት ፍላሽ ድራይቭ ላይ የቁልፍዎን ቅጂ ማስቀመጥ ሊያስፈልግዎት ይችላል። ይህም የሚያስፈልግዎት ዋና ቁልፍ ከጠፋብዎት ብቻ ቢኾንም ለደህንነትዎ ሲሉ አቅም ያላቸው አጥቂዎች እጅ እንዳይገባ መጠበቅ አለብዎት።

  የPGP የግል ቁልፌ በአጥቂዎቼ ቁጥጥር ስር ገባ ማለት አጥቂዎቼ ሰነዶቼን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት ማለት ነውን?

  ማክዎ የተሰረቀ ወይም የመጠባበቂያ ቁልፍዎ ከእርሶ የተወሰደ ቢኾንስ? የPGP መልዕክትዎ ተጋላጭ ነው ማለት ነውን? አይደለም! ጠንካራ የማለፊያ ሐረግ ከመረጡ እና ምን እንደኾነ ሌሎች ማወቅ እስካልቻሉ ድረስ በአብዛኛው የተጠበቁ ነዎት። እርግጠኛ ለመኾን የድሮውን ቁልፍዎን መሻር እና አዲስ የPGP ቁልፍ መፍጠር ሊያስፍልግዎት ይችላል። ይህም የድሮ ቁልፍዎ ድሮ የተላኩልዎትን ኢሜሎችን መፍታት ባይከለክልም ሌሎች ስዎች አዲስ መልዕክቶችን ሲልኩልዎት የድሮውን ቁልፍ እንዳይጠቀሙ ግን ያደርጋል።

  <

  የቁልፍዎን ተጠባባቂ ለማኖር የGPG ኪይቼን ይክፈቱ። ቁልፍዎን ይምረጡ እና ከሰሪ አሞሌው “ኤክስፖርት” ላይ ጠቅ ያድርጉ። የፍላሽ ድራይቭዎን ኮምፒውተሩ ላይ ያገናኙት እና በ“ሴቭ አስ ... ” መገናኛ ውስጥ “ኸዌር” የሚለው ክፍል ላይ ይምረጡት። “አላው ሴክሬት ኪይ ኤክስፖርት” አመልካች ሳጥንን ያመልክቱ።

  አፕል ሜልን ማዋቀር

  አፕል ሜልን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፍቱ የኢሜል አድራሻዎትን ማዋቀር የሚያስችልዎ ለመጀመሪያ ጊዜ ብቻ የሚመጣ አዋቂ ያሳይዎታል። ስምዎን፣ የኢሜል አድራሻዎን እና የማለፊያ ቃልዎን ያስፍሩና ‘ክሬት’ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

  የሜል አድራሻን የማዋቀሪያ አዋቂ

  እንደ ጂሜል ያለ ታዋቂ ነጻ የኢሜል አገልግሎትን የሚጠቀሙ ከኾነ ‘ኮንቲኒው’ የሚለውን ጠቅ ሲያደርጉ አፕል ሜል የኢሚልዎን ቅንብር በቀጥታ ማግኘት አለበት። ይህን ማድረግ ካልቻለ የIMAP እና የ SMTP ቅንብሩን በትዕዛዝ ማቀናበር ይኖርብዎታል። ለኢሜል የሚጠቀሙትን ኩባንያ ወይም የኢሜል አገልግሎት ሰጪዎን በደንብ የሚያውቅ እና ክህሎት ያለውን ሰው ይጠይቁ። (ይህም ከእርሶ ጋር አንድ ዓይነት የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪን (ISP) የሚጠቀም የመሥሪያ ቤትዎ የIT ሠራተኛ ወይም ሞያ ያለው ጓደኛዎ ሊኾን ይችላል። ስለ PGP ማወቅ አይጠበቅበትም ነገር ግን “የአፕል ሜሌን ልታዋቅርልኝ ትችላለህን?” ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ)።

  የልብ አወቅ ሜል አድራሻ አወቃቀር

  አዲስ መልዕክትን ሲያቀናብሩ ከርዕሰ ነገሩ መስክ በታች ሁለት አዶዎች አሉ። እነዚህም ኢሜሉን የሚያመሰጥሩበት የሰሌዳ ቁልፍ እና ዲጂታ የኢሜል ፊርማ የሚፈርሙበት የኮከብ ምልክት ናቸው። የሰሌዳ ቁልፉ የተቆለፈ ከኾነ ኢሜሉ ምስጢራዊ ይኾናል ማለት ሲኾን ኮከቡ ላይ ምልክት ካለበት ኢሜሉ የዲጂታል ፊርማ ይኖረዋል ማለት ነው።

  በPGP የተፈረመ ወይም የተመሰጠረ ኢሜል መላክ

  የሚቀበለው ሰው የPGP ተጠቃሚ ባይኾንም እንኳን የሚልኩትን ኢሜል ሁልጊዜ መፈረም ይችላሉ። ለመጀመሪያ ጊዜ ኢሜል ሲፈርሙ የማለፊያ ሐረግዎን የሚጠይቅ ብቅ ባይ መስኮት ይከፈታል። ምክንያቱም ኢሜሎችን በዲጂታል መፈረም የምስጢርር ቁልፍ ስለሚያስፈልገው ነው።

  ኢሜልን ማመስጠር የሚችሉት ኢሜሉን የሚልኩለት ሰው የPGP ተጠቃሚ ከኾነ እና የአደባባይ ቁልፉንም እጅዎ ካስገቡ ብቻ ነው። የማመስጠሪያው የሰሌዳ ቁልፍ አዶ ካልተቆለፈ እና አመድማ ከኾነ የተቀባዩን የአደባባይ ቁልፍ በመጀመሪያ ኢንፖርት ማድረግ አለብዎት ማለት ነው። ወይ እንዲልክልዎት ይጠይቁ’ አልያም ቁልፉን ከአደባባይ ቁልፍ አጋልጋይ ለማግኘት የGPG ኪይቼን አክሰስ መተግበሪያን ይጠቀሙ።

  ፍጹም ደህንነቱን ለመጠበቅ ከቁልፍ አገልጋይ ወይም ከባልደረባዎ ያገኙትን ቁልፍ ማረጋገጥ አለብዎት። የቁልፍ ማረጋገጫ የሚለውን ክፍል ይመልከቱ።

  PGPን ከሞዚላ ተንደርበርድ ጋር መጠቀም

  ይህ የሞዚላ ነጻ ምንጨ ኮድ የኾነውን ተንደርበርድ ሜል ደንበኛ እና የኤኒግሜል ተሰኪን ከGPG ጋር በመጠቀም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የኢሜል ምስጠራን የሚያሳይ ነው።

  በመጀመሪያ ተንደርበርድን ከዚህ ያውርዱ https://www.mozilla.org/thunderbird, በGPG ቱልስ እንዳደረጉት የዲስክ ኢሜጁን ቁብ አድርጉ እና ተንደርበርድን ስበው አፕሊኬሽንስ ማህደር ውስጥ ያስገቡት። ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፍቱት ነባሪ የኢሜል ደምበኛዎ ኾኖ እንዲቀመጥ እንደሚፈልጉ ይጠይቅዎታል። ይሂዱና “ሴት አስ ዲፎልት” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

  ከዚያም ለመጀመሪያ የተከፈተውን አዋቂ ያያሉ። ያልዎትን የኢሜል አድራሻ ለማዋቀር “እስኪፕ ዚስ ኤንድ ዩዝ ማይ ኤዚስቲንግ ኢሜል” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ። በመቀጠልም ስምዎን፣ የኢሜል አድራሻዎን እና ለኢሜልዎ የማለፊያ ቃል ያስገቡ።

  እንደ ጂሜል ያለ ስመጥር ነጻ የኢሜል አገልግሎት የሚጠቀሙ ከኾነ ‘ኮንቲኒው’ የሚለውን ጠቅ ሲያደርጉ ተንደርበርድ የኢሚልዎን ቅንብር በቀጥታ ማግኘት አለበት። ይህን ማድረግ ካልቻለ የIMAP እና የSMTP ቅንብሩን በእጅ ማቀናበር ይኖርብዎታል። የኢንተርኔት አገልግሎት አቅራቢዎን ወይም የኢሜል ቅንብርን ማዋቀር የሚችል ሙያዊ እውቀት ያለው ጓደኛዎን እርዳታ ይጠይቁ። አንዳንዴ ተንደርበርድ ትክክለኛውን ቅንብር ሊግምት ይችላል።

  ባለ ሁለት ማጥሪያ ማመሳከሪያ ከጎግል (የስጋት ሞዴልዎን መሠረት አድርገው ሊጠቀሙ ይገባል) ጋር የሚጠቀሙ ከኾነ መደበኛ የጂሜል ማለፊያ ቃልዎን ከተንደርበርድ ጋር መጠቀም አይችሉም። ይልቁንም የጂሜል አድራሻዎን በተንደርበርድ ለመጠቀም ለመተግበሪያው የተወሰነ አዲስ የማለፊያ ቃል መፍጠር ያስፈልግዎታል። ይህን ለማድረግ የራሱ የጎግል መመሪያን ይመልከቱ። 

  ተንደርበርድን ማዋቀር ከጨረሱ በኋላ ኢሜልዎን ለመመልከት ደን የሚለውን ጠቅ ያድርጉ። ከዚያም ኢሜልዎትን ለመጫን ከላይ በግራ በኩል ያለው “ኢንቦክስ” የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ።

  አሁን ተንደርበርድን ጭነው ከኢሜልዎ ጋር እንዲሰራ አዋቅረዋል። በመቀጠል ለተንደርበርድ የGPG ቅጥያ የሆነውን ኤኒግሜልን መጫን ይኖርብዎታል። በተንደርበርድ የላይኛው ቀኝ ክፍል የሚገኘውን ምናሌ አዶ ጠቅ ያድርጉ እና አድ-ኦንስ የሚለውን ይምረጡ።

  በላይኛው ቀኝ ክፍል በሚገኘው የመፈለጊያ ሳጥን “ኤኒግሜል”ን ይፈልጉ።

  ኤኒግሜልን አውርዶ ለመጫን ከኤኒግሜል ቅጥያ አጠገብ ያለውን ኢንስቶል የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። ሲያበቃ ተንደርበርደን እንደገና ለማስጀመር ‘ሪስታርት ናው’ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

  ለመጀመሪያ ጊዜ ኤኒግሜልን አስችለው ተንደርበርድን ሲከፍቱት የOpenPGP ማዋቀሪያ አዋቂን ይከፍታል። ‘ካንስል’ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ። ይልቁን ኤኒግሜልን በእጅ (በትዕዛዝ) እናዋቅረዋለን።

  ሜኑ አዝራር ላይ ጠቅ ያድርጉ፤ በፕሪፈረንስ ላይ ያንዣብቡ እና አካውንት ሴቲንግ የሚለውን ይምረጡ።

  ወደ OpenPGP ሰኪዩሪቲ ትር ይሂዱ። “ኢንኤብልOpenPGP ሰፖርት (ኤኒግሜል) ፎር ዚስ አይደንቲቲ” የሚለው መመልከቱን ያረገግጡ። “ዩዝ ስፔስፊክ OpenPGP ኪይ አይዲ” የሚለው ይምረጡ እና ቁልፍዎ ካልተመረጠ ሴሌክት ኪይ የሚለውን ጠቅ በማድረግ ቁልፍዎን ይምረጡ።

  በተጨማሪም “ሳይን ነን-ኢንክሪፕትድ ሜሴጅ ባይ ዲፎልት”፣ “ሳይን ኢንክሪፕትድ ሜሴጅ ባይ ዲፎልት”፣ እና “ዩዝ PGP/MIME ባይ ዲፎልት” የሚሉትን ሲያመለክቱ ነገር ግን “ኢንክሪፕት ሜሴጅ ባይ ዲፎልት” የሚለው ማመልከት የለብዎትም።

  ኢሜል የሚልኩላቸውን ብዙዎቹ ሰዎች PGPን የሚጠቀሙ ከሆነ (ወይም እንዲጠቀሙ ማበረታታት የሚፈልጉ ከሆነ) በነባሪ መልክትዎ የተመሰጠረ እንዲሆን ይፈልጉ ይሆናል። ሁሉንም የሚልኳቸውን ኢሜልዎች ማመስጠር አይነተኛ ቢሆንም ነገር ግን ሁሌም ይህን ማድረግ አይቻልም። ያስታውሱ የተመሰጠረ ኢሜል መላክ የሚችሉት የPGP ተጠቃሚ ለሆኑ እና በኪይቼንዎ ውስጥ የአደባባይ ቁልፋቸው ላለዎት ሰዎች ብቻ ነው። ስለዚህ ለአብዛኛው ሰው እያንዳንዱን ኢሜል በእጅ እንዲመሰጠር መምረጥ የተሻለ ይሰራል።

  ቀጥሎ ሁሉንም ቅንብሮች እንዲያስቀምጥ ኦኬ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

  እንኳን ደስ አለዎት! አሁን ተንደርበርድ እና ኤኒግሜልን አቀናብረዋል! ጥቂት ምክሮች፦

  • የሜኑ አዝራር ላይ ጠቅ አድርገው OpenPGP ላይ ያንዣብቡ እና የኤኒግሜል አብሮገነብ የፒጂፒ ቁልፍ አስተዳዳሪን ለማየት ‘ኪይ ማኔጅመንት’ የሚለውን ይክፈቱ። ይህም ከGPG ኪይቼን አክሰስ ጋር ተመሳሳይ ሲኾን የሚፈልጉትን መጠቀም የእርስዎ ምርጫ ነው።
  • አዲስ መልዕክትን ሲያቀናብሩ በመስኮቱ ታችኛው የቀኝ ክፍል ሁለት አዶዎች አሉ። እነዚህም ዲጂታል ፊርማ የሚፈርሙበት የእስክሪብቶ እና ኢሜሉን የሚያመሰጥሩበት የቁልፍ ምልክት ናቸው። እነኚህ አዶዎች ወርቃማ ከኾኑ ተመርጠዋል ማለት ሲኾን ብርማ ከኾኑ ግን አልተመረጡም ማለት ነው። እየከተቡ ያሉትን ኢሜል ለመፈረም እና ለማመስጠር ላያቸው ላይ ጠቅ በመድረግ ይቀሯቸው።

  Last reviewed: 
  2015-05-27
 • የኪፓስኤክስ አጠቃቀም

  የኪፓስኤክስ አሰራር

  ኪፓስኤክስ የሚሰራው የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታ ከተባለ ፋይል ጋር ነው። እነኚህ የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎች እንደስማቸው ሁሉንም የማለፊያ ቃሎችን የሚያጠራቅሙ ናቸው። ውሂብ ጎታዎቹ በኮምፒውተርዎ ዋና ዲስክ ላይ በሚጠራቀሙበት ወቅት የተመሰጠሩ ይሆናሉ። ስለዚህ ኮምፒውተርዎ ቢሰረቅ ወይም ቢጠፋ ኮምፒውተርዎን ያገኘው ሰው የማለፊያ ቃሎችዎን ማንበብ አይችልም።

  የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታ በሶስት መንገዶች ሊመሰጥር ይችላል። ይህም ዋና የማለፊያ ቃል በመጠቀም፣ ቁልፍ ፋይል በመጠቀም ወይም ሁለቱንም በአንድነት በመጠቀም ሊሆን ይችላል። የእያንዳንዱን ጥቅም እና ጉዳት እንመልከት።

  ዋና የማለፊያ ቃልን መጠቀም

  ዋና የማለፊያ ቃል የሚሰራው እንደ ቁልፍ ነው። የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታን ለመክፈት ትክክለኛ የዋና ማለፊያ ቃል ያስፈልግዎታል። ከዛ ውጪ ማንም ሰው የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታ ውስጥ ምን እንዳለ ማየት አይችልም። የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን ደህንነት ለመጠበቅ ዋና የማለፊያ ቃልን ሲጠቀሙ ከግምት ውስጥ ሊያስገቧቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ።

  • ይህ የማለፊያ ቃል ሁሉንም የማለፊያ ቃሎችን የሚፈታ ስለሆነ ጠንካራ ሊሆን ይገባል! ይህ ማለት በቀላሉ ሊገመት የማይችል እና ረጅም መሆን አለበት። የማለፊያ ቃሉ በረዘመ ቁጥር የተሻለ ይሆናል! በተጨሪም ረጅም በሆነ መጠን የተለያዩ ምልክቶችን፣ አብይ ፊደላትን ወይም ቁጥሮችን ለመጠቀም ብዙ መጨነቅ አይጠበቅብዎትም። ሁሉም ትንሽ ፊደላት በሆኑ እና በመካከላቸው ክፍተት ባላቸው ስድስት ቃላት ብቻ የተፈጠረ የማለፊያ ቃል በአብይ እና ትንሽ ፊደላት፣ ቁጥሮች እና ምልክቶች ከተሰራ ባለ 12-ምልክት የማለፊያ ቃል ይልቅ ለመሰበር አዳጋች ነው።
  • ይህን የማለፊያ ቃል ማስታወስ ይጠበቅቦታል! ይህ አንድ የማለፊያ ቃል ሁሉንም ሌሎች የማለፊያ ቃሎችዎን እንዲያገኙ የሚረዳዎ ስለሆነ በወረቀት ላይ ሳይጽፉ ማስታወስ እንደሚችሉ ማረጋገጥ ይኖርብዎታል። ይህም ልክ እንደ ዳይስዌር ያለ በዘፈቀደ የተፈጠሩ የቃላት ስብስብን እንዲጠቀሙ ሌላው ምክንያት ነው። ያልተለመዱ የምልክቶች እና የአብይ ፊደላት ስብስብን ለማስታወስ ከመጣር ይልቅ ለማስታወስ ቀላል የሆኑ የተለመዱ ቃሎችን መጠቀም ይችላሉ።

  ቁልፍ ፋይልን መጠቀም

  በአማራጭነት የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታን ለማመስጠር ቁልፍ ፋይልን መጠቀም ይችላሉ። ቁልፍ ፋይል ልክ የማለፊያ ቃልን እንደሚጠቀሙ በተመሳሳይ መንገድ ይሰራል። የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን ለመፍታት በሚፈልጉበት በማንኛውም ወቅት ቁልፍ ፋይሉን ለኪፓስኤክስ ማስገባት አለብዎት። የቁልፍ ፋይሉ መቀመጥ ያለበት በፍላሽ ድራይቭ ወይም በሌላ ተንቀሳቃሽ ማህደረ-መረጃ ሲሆን ይህንንም ከኮምፒውተርዎ ጋር ማገናኘት ያለብዎት የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን መክፈት ሲያስፈልግዎ ብቻ ነው። የዚህም ጥቅሙ የኮምፒውተርዎ ዋና ዲስክ (የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎ) በሰው እጅ ላይ ቢወድቅ እንኳን በውጫዊ ማህደረ መረጃ ከተቀመጠው የቁልፍ ፋይል ውጪ የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን መፍታት አይችሉም። (በተጨማሪም ለባላንጣዎ ቁልፍ ፋይልን መገመት ማንኛውንም የማለፊያ ቃል ከመገመት የበለጠ በጣም ከባድ ነው።) የእዚህ መንገድ የጎንዮሽ ጉዳቱ የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን ለመጠቀም በፈለጉ ቁጥር ፋይሉን ያስቀመጡበት ውጫዊ ማህደረ መረጃ በአቅራቢያዎ ሊያገኙት የግድ መሆኑ ነው (ከጠፋ ወይም ጉዳት ከደረሰበት የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን መክፈት አይችሉም)።

  በማለፊያ ቃል ፈንታ ቁልፍ ፋይልን መጠቀም የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን በቁሳዊ ቁልፍ እንደመክፈት ይቆጠራል። ማድረግ የሚጠበቅብዎት የፍላሽ ድራይቩን ከኮምፒውተርዎ ጋር ማገናኘት፣ ቁልፍ ፋይሉን መምረጥ ብቻ ነው። በዋና የማለፊያ ቃል ፈንታ ቁልፍ ፋይልን መጠቀም ከመረጡ የፍላሽ ድራይቩን ያገኘ ማንኛውም ሰው የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን መክፈት ስለሚችል ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ማስቀመጥዎን ያረጋግጡ።

  ሁለቱንም መጠቀም

  የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን ለማመስጠር በጣም አስተማማኝ መንገዱ ዋና የማለፊያ ቃልን እና ቁልፍ ፋይልን በአንድ ላይ መጠቀም ነው። በዚህ አካሄድ የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን የመፍታት ችሎታዎ በሚያውቁት (ዋና የማለፊያ ቃሎ) እና ባለዎት (ቁልፍ ፋይሎ) ላይ የተመሰረተ ነው። ስለዚህ የማለፊያ ቃልዎችዎን ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሸረኛ አካል ሁለቱንም ማግኘት ይጠበቅበታል። (ይህ ከተባለ ዘንዳ የስጋት ሞዴሎን ያስታውሱ። የማለፊያ ቃልዎችዎን ለማጠራቀም ለሚፈልጉ የቤት ውስጥ ተጠቃሚዎች ጠንካራ ዋና የማለፊያ ቃል ብቻ መጠቀም በቂ ነው። ነገር ግን በመንግስት ደረጃ ካሉ እና ሰፊ ቀመራዊ ሃብት ባለቤት ከሆኑ ሸረኛ አካላት ራስዎን መጠበቅ የሚፈልጉ ከሆነ የደህንነትዎን ጥበቃ ከፍ ማድረግ የተሻለ ነው።)

  አሁን ኪፓስኤክስ እንዴት እንደሚሰራ ስለተረዳችሁ በጥቅም ላይ ማዋልን እንጀምር!

  ኪፓስኤክስን መጀምር

  አንዴ ኪፓስኤክስን ከጫኑ በኋላ ፕሮግራሙን ያስጀምሩት። ፕሮግራሙ ከጀመረ በኋላ ከፋይል ምናሌው ውስጥ “ኒው ዳታቤዝ” የሚለውን ይምረጡ። ዋና የማለፊያ ቃልን እንዲያስገቡ እና/ወይም ቁልፍ ፋይልን እንዲጠቀሙ የሚጠይቅ መገናኛ ብቅ ይላል። ምርጫዎን መሰረት በማድረግ ተገቢውን የማመልከቻ ሳጥን(ኖች) ይምረጡ። ያስተውሉ እያስገቡት ያለውን የማለፊያ ቃል ማየት ከፈለጉ (በነጠብጣብ ከመደበቅ ፈንታ) በቀኝ በኩል የ“አይን” ምልክት ያለበትን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። በተጨማሪም ማንኛውንም ፋይል ለቁልፍ ፋይልነት ለምሳሌ የድመት ስዕልን መጠቀም ይችላሉ። ለቁልፍ ፋይልነት የመረጡት ፋይል መቼም እንደማይቀየር ማረጋገጥ አለብዎት። ምክኒያቱም ይዘቱ ከተቀየረ የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን ለመፍታት አይችልም። በተጨማሪም አንዳንዴ ፋይሉን በሌላ ፕሮግራም መክፈት የፋይሉን ይዘት ለመቀየር በቂ ሊሆን እንደሚችል ይወቁ። ኪፓስኤክስን ለመክፈት ብቻ ካልሆነ በስተቀር ፋይሉን አለመጠቀም አለ የሚባል ምርጥ ልምምድ ነው። (የቁልፍ ፋይሉን ቦታ ወይም ስም መቀየር የተሻለ ድህንነት ይሰጣል።)

  በተሳካ ሁኔታ የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን ካስጀመሩ በኋላ ከፋይል ምናሌው ላይ “ሴቭ ዳታቤዝ” የሚለውን በመምረጥ ያስቀምጡት። (ያስተውሉ በኋላ ላይ የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታ ፋይሉን ወደፈለጉበት ቦታ ማንቀሳቀስ ይችላሉ። ይህም በኮምፒውተርዎ ዋና ዲስክ ላይ ወደተለየ ስፍራ ወይም ወደሌላ ኮምፒውተር ሊሆን ይችላል። ወደሌላ ኮምፒውተር ካንቀሳቀሱት ኪፓስኤክስን እና በፊት የተጠቀሙትን የማለፊያ ቃል/ቁልፍ ፋይል በመጠቀም የውሂብ ጎታውን መክፈት ይችላሉ።)

  የማለፊያ ቃሎችን ማደራጀት

  ኪፓስኤክስ የማለፊያ ቃሎችን በ“ግሩፕስ” እንዲያደራጁ ይፈቅዳል። እነኚህም ግሩፖች ወይም ቡድኖች ማህደሮች እንደ ማለት ናቸው። ከምናሌ አሞሌ ውስጥ “ግሩፕስ” የሚለው ምናሌ ውስጥ በመሄድ ወይም በኪፓስኤክስ መስኮት በግራ በኩል ካለው ንጥል መስኮት ግሩፕ የሚለው ላይ ቀኝ ጠቅ በማድረግ ቡድንን ወይም ንዑስ ቡድንን መፍጠር ወይም መሰረዝ ወይም ማረት ይችላሉ። የማለፊያ ቃሎችን በቡድን ማስቀመጥ ከአመቺ የማደራጃ መሣሪያነቱ ውጪ በኪፓስኤክስ ተግባራዊነት ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ የለም።

  የማለፊያ ቃሎችን ማጠራቀም/ማመንጨት/ማረት

  አዲስ የማለፊያ ቃልን ለመፍጠር ወይም አስቀድመው የፈጠሩትን የማለፊያ ቃል ለማጠራቀም የማለፊያ ቃሉን ማጠራቀም የሚፈልጉበት ቡድን ላይ ቀኝ ጠቅ ያድርጉ እና “አድ ኒው ኢንትሪ” የሚለውን ይምረጡ (ወይም ደግሞ ከምናሌ አሞሌ ላይ “ኢንትሪስ &ጂቲ; አድ ኒው ኢንትሪ” የሚለውን መምረጥ ይችላሉ)። ለመሠረታዊ የማለፊያ ቃል አጠቃቀም የሚከተለውን ያድርጉ፦

  • “ታይትል” በሚለው መስክ ላይ ይህን የማለፊያ ቃል ምዝገባ ለማስታወስ የሚረዳዎትን ገላጭ ርዕስ ያስገቡ።
  • በ“ዩዘርኔም” መስክ ላይ ከዚህ የማለፊያ ቃል ምዝገባ ጋር ተዛማጁን የተጠቃሚ ስም ያስገቡ። (የተጠቃሚ ስም ከሌለው ባዶውን ሊተውት ይችላሉ።)
  • “ፓስወርድ” በሚለው መስክ ላይ የማለፊያ ቃልዎትን ያስገቡ። አዲስ የማለፊያ ቃል እየፈጠሩ ከሆነ (ይህም ድረገጽ ላይ ሊመዘገቡ ቢሆን እና አዲስ፣ ልዩ፣ የዘፈቀደ የማለፊያ ቃል መፍጠር ቢፈልጉ) በቀኝ በኩል የሚገኘውን “ጀን” የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ። ይህም የዘፈቀደ ማለፊያ ቃል ማመንጨት የሚያስችልዎትን የማለፊያ ቃል አመንጪ “ብቅ ባይ” መገናኛ ያመጣልዎታል። በዚህ መገናኛ ውስጥ ብዙ ምርጫዎች አሉ። ከእነዚህም ውስጥ የማለፊያ ቃሉ የትኞቹን ምልክቶች እንዲያካትት እንደሚፈልጉ እና ርዝመቱን ጭምር ይገኙበታል።
   • ያስተውሉ በዘፈቀደ የማለፊያ ቃል ካመነጩ የማለፊያ ቃሉ ምን እንደሆነ ማስታወስ (ወይም ማወቅ!) አይጠበቅብዎትም! ኪፓስኤክስ ያጠራቅምልዎታል። ስለዚህም የማለፊያ ቃሉን መጠቀም በሚያስፈልግዎ በማንኛውም ወቅት በተገቢው ፕሮግራም ላይ ቀድተው መለጠፍ ይችላሉ። ይህም የማለፊያ ቃል ካዝና ዋና አላማ ነው። የማለፊያ ቃሎቹ ምን እንደሆኑ ማወቅ ሳያስፈልግዎት የተለያዩ ረዥም እና በዘፈቀደ የተፈጠሩ የማለፊያ ቃሎችን ለእያንዳንዱ ድረገጽ እና አገልግሎት መጠቀም!
   • በዚህም ምክንያት የማለፊያ ቃሉን አገልግሎቱ የሚፈቅደውን ያህል ማርዘም እና የቻሉትን ያህል የተለያዩ ምልክቶችን መጠቀም ይችላሉ።
   • አንዴ ምርጫዎ ከተስማማዎት የማለፊያ ቃሉን ለማመንጨት በመስኮቱ የታችኛው ቀኝ የሚገኘውን “ጀነሬት” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ እና ቀጥለው “ኦኬ”ን ጠቅ ያድርጉ። የመነጨው የዘፈቀደ የማለፊያ ቃል በቀጥታ “ፓስወርድ” እና “ሪፒት” በሚለው መስክ ላይ ገብቶ ያገኙታል። (የዘፈቀደ የማለፊያ ቃልን የማያመነጩ ከሆነ የመረጡትን የማለፊያ ቃል “ሪፒት” በሚለው መስክ ውስጥ እንደገና ማስገባት ይጠበቅብዎታል።)
  • በመጨረሻም ኦኬ የሚለውን ጠቅ ያደርጉ። የማለፊያ ቃልዎ በማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎ ውስጥ ይጠራቀማል። ለውጦቹ እንደተቀመጡ እርግጠኛ ለመሆን “ፋይል &ጂቲ; ሴቭ ዳታቤዝ” የሚለው ጋር ሄደው አርትዖት የተደረገበትን የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን ማስቀመጥዎን ያረጋግጡ። (በሌላ መልኩ ስህተት ከሰሩ ደግሞ ውሂብ ጎታ ፋይሉን ዘግተው እንደገና በመክፈት ሁሉንም ስህተቶች ማስወገድ ይችላሉ።)

  ያጠራቀሙትን የማለፊያ ቃል መቀየር ወይም አርትዖት ማድረግ ቢያስፈልግዎት የማለፊያ ቃሉ ያለበት ቡድንን ይምረጡ እና በቀኝ በኩል ካለው ንጥል መስኮት አርዕስት ላይ ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ። ከዛም “ኒው ኢንትሪ” መገናኛ እንደገና ብቅ ይላል።

  መደበኛ አጠቃቀም

  በማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎ ያስቀመጡትን ግብዓት ጥቅም ላይ ለማዋል በግብዓቱ ላይ ቀኝ ጠቅ ያድርጉ እና “ኮፒ ዩዘርኔም ቱ ክሊፕቦርድ” ወይም “ኮፒ ፓስወርድ ቱ ክሊፕቦርድ” የሚለውን ይምረጡ እና የተጠቃሚ ስምዎን ወይም የማለፊያ ቃሎን ማስገባት ወደፈለጉበት መስኮት ወይም ድረገጽ ሄደው በተገቢው መስክ ላይ ይለጥፉት። (በግብዓቱ ላይ ቀኝ ጠቅ ከማድረግ በተጨማሪ የሚፈልጉት የግብዓት ተጠቃሚ ስም ወይም ማለፊያ ቃል ላይ ሁለቴ ጠቅ በማድረግ የተጠቃሚ ስሙን ወይም የማለፊያ ቃሉን በቀጥታ በቅንጥብ ሰሌዳው ላይ መቅዳት ይችላሉ።)

  ስልጡን አጠቃቀም

  የቁልፍ ሰሌዳዎ ላይ ልዩ የሆነ የቁልፎች ስብስብን ሲጫኑ የተጠቃሚ ስምዎን እና የማለፊያ ቃልዎን በሌላ ፕሮግራሞች ውስጥ ማስገባቱ የኪይፓስኤክስ ከብዙ በጣም ጠቃሚ ገጽታዎች መካከል አንዱ ነው። ያስተውሉ ይህ ገጽታ በሊኒክስ የሚሰሩ ኮምፒውተሮች ብቻ ላይ የሚገኝ ቢሆንም እንደ ኪፓስ (ኪፓስኤክስ የተመሰረተው በእዚህ ላይ ነው) ያሉ ሌሎች የማለፊያ ቃል ካዝናዎች ይህንን ገጽታ በሌሎች ስርዓተ ክወናዎች (ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች) ላይ በተመሳሳይ መንገድ ይሠራሉ።

  ይህንን ገጽታ ለማስቻል የሚከተለውን ያድርጉ

  1. ሉላዊ የማፍጠኛ ቁልፍዎን ይምረጡ። ከ“ኤክስትራስ” ምናሌ “ሴቲንግስ” የሚለውን ከመረጡ በኋላ “አድቫንስድ” የሚለውን በግራ በኩል ካለው ንጥል መስኮት ላይ ይምረጡ። “ግሎባል አውቶ ታይፕ ሾርትከት” የሚለው መስክ ውስጥ ጠቅ ያድርጉ እና ለመጠቀም የሚፈልጉትን የአቋራጭ ቁልፍ ስብስብ ይጫኑ። (ለምሳሌ Ctrl፣ Alt እና Shiftን ተጭነው ይቆዩ እና ቀጥለው “p”ን ይጫኑ። የሚፈልጉትን የቁልፍ ጥምረት መጠቀም ይችላሉ ነገር ግን ሌሎች መተግበሪያዎች ከሚጠቀሟቸው የማፍጠኛ ቁልፎች ጋር የማይጋጩ መኾኑን ማረጋገጥ አለብዎት። ስለዚህ እንደ Ctrl+X ወይም Alt+F4 ካሉ ጥምረቶች ለመራቅ ይሞክሩ።) ከተስማማዎት “ኦኬ” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

  2. ለማለፊያ ቃል የተወሰነ ራስ ተይብን ማዋቀር የማለፊያ ቃሉን ማስገባት የፈለጉበት መስኮት ክፍት እንደሆነ ያረጋግጡ። በመቀጠል ወደ ኪፓስኤክስ ይሂዱና ራስ ተይብን ማስቻል የሚፈልጉትን ግብዓት ያግኙ እና “ኒው ኢንትሪ” መገናኛውን ለመክፈት በግብዓቱ ርዕስ ላይ ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ።

  3. “ቱልስ” የሚለውን በታችኛው ግራ ክፍል ያለው አዝራር ላይ ጠቅ ያድርጉ እና “አውቶ-ታይፕ: ሴሌክት ታርጌት ዊንዶው” የሚለውን ይምረጡ። ብቅ በሚለው መገናኛ ላይ ተቆልቋይ ሳጥኑን ያስፉ እና የተጠቃሚ ስሙ እና የማለፊያ ቃሉ እንዲገባበት የሚፈልጉትን የመስኮት ርዕስ ይምረጡ። ኦኬ ላይ ጠቅ ያድርጉ እና በድጋሚ ኦኬ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

  ይሞክሩት! አሁን የተጠቃሚ ስምዎን እና የመለፊያ ቃልዎን ራስ ተይብ ለማድረግ ኪፓስኤክስ የተጠቃሚ ስምዎን/የማለፊያ ቃልዎን ራስ ተይብ እንዲያደርግልዎት የሚፈልጉበት መስኮት/ድረ ገጽ ጋር ይሂዱ። ጠቋሚው የተጠቃሚ ስሞን የሚያስገቡበት ቅጥረጹፍ ውስጥ መሆኑን ያረጋግጡ እና ከላይ ለሉላዊ የማፍጠኛ ቁልፍነት የመረጧቸውን የቁልፍ ስብስቦችን ይጫኑ። ኪፓስኤክስ ክፍት እስከሆነ ድረስ (ምንም እንኳ ያነሰ ወይም ትኩረት የሌለበት ቢሆንም) የተጠቃሚ ስምዎት እና የማለፊያ ቃልዎት በቀጥታ መግባት አለበት።

  ያስተውሉ እንደ የድረ ገጹ/የመስኮቱ አወቃቀር ይህ ገጽታ መቶ በመቶ ወዲያውኑ በትክክል ላይሰራ ይችላል። (ለምሳሌ የተጠቃሚ ስሙን አስገብቶ ነገር ግን የማለፊያ ቃሉን ላያስገባ ይችላል።) ምንም እንኳ ይህ ገጽታ እንዲሠራ መላ መፈለግ እና ማበጀት ቢችሉም ለበለጠ መረጃ ይህን የኪፓስ ሰነድ እንዲመለከቱ እናሳስባለን። (በኪፓስ እና ኪፓስኤክስ መካከል አንዳንድ ልዩነቶች ቢኖሩም ይህ ገጽ ትክክለኛውን መንገድ ለመምራት በቂ ነው።)

  በአጋጣሚ ለመጫን አዳጋች የሆነ የቁልፍ ስብስብን እንዲጠቀሙ እናሳስባለን። የባንክ አካውንት የማለፊያ ቁልፍዎን በስህተት የፌስቡክ ገጾ ላይ መለጠፍ አይፈልጉም!

  ሌሎች ገጽታዎች

  በውሂብ ጎታዎ ውስጥ ያስቀመጡትን ግብዓት ለመፈለግ የመፈለጊያ ሳጥን (በዋናው የኪፓስኤክስ መስኮት ሰሪ አሞሌ ውስጥ ያለ ቅጥረጽሑፍ) ውስጥ ስለሚፈልጉት ነገር ይተይቡ እና ከቁልፍ ሰሌዳው ላይ አስገቢ ቁልፍን (enter) ይጫኑ።

  በዋና መስኮት ውስጥ የሚገኘው የአምዱ ራስጌ ላይ ጠቅ በማድረግ ግብዓቶችዎን መደርደር ይችላሉ።

  በተጨማሪም “ፋይል &ጂቲ; ሎክ ወርክስፔስ” የሚለውን በመምረጥ ኪፓስኤክስን “መዝጋት” ይችላሉ። ይህም ኪፓስኤክስን ክፍቱን መተው ያስችልዎታል። ነገር ግን የማለፊያ ቃል ውሂብ ጎታዎን በድጋሚ ከመጠቀምዎ በፊት ዋና የማለፊያ ቃልዎን (እና/ወይም ቁልፍ ፋይልዎን) ይጠይቅዎታል። ኪፓስኤክስን ለተወሰነ ጊዜ ካልተጠቀሙት በቀጥታ ራሱን እንዲዘጋ ማድረግ ይችላሉ። ይህም በሆነ አጋጣሚ ከኮምፒውተርዎ ከራቁ ሌላ ሰው የማለፊያ ቃልዎትን እንዳያገኝ ይከላከላል። ይህን ገጽታ ለማስቻል ከምናሌው “ኤክስትራስ &ጂቲ; ሴቲንግስ” የሚለውን ይምረጡ እና ሴኪዩሪቲ ኦፕሽንስ የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ። ከዛም “ሎክ ዳታቤዝ አፍተር ኢንአክቲቪቲ ኦፍ {ነምበር} ሰከንድስ” የሚለውን ሳጥን ይምረጡ።

  በኪፓስኤክስ ከተጠቃሚ ስም እና ከማለፊያ ቃል በተጨማሪ ሌሎች ነገሮችንም ማጠራቀም ይቻላሉ። ለምሳሌ የአካውንት ቁጥርዎን፣ የምርት መታወቂያ ቁጥር፣ መለያ ቁጥር ወይም የመሳሰሉትን ነገሮች የሚያጠራቅም ምዝገባን መፍጠር ይችላሉ። በ“ፓስወርድ” መስኩ ላይ የሚያስገቡት ውሂብ የማለፊያ ቃል ብቻ መሆን አለበት የሚል መስፈርት የለም። የፈለጉት ነገር ሊሆን ይችላል። በማለፊያ ቃል ፈንታ በ“ፓስወርድ” መስኩ ላይ ማስቀመጥ የፈለጉትን ነገር ያስገቡ (የተጠቃሚ ስም ከሌለው የ“ዩዘርኔም” መስኩን ባዶውን ይተውት) እና ኪፓስኤክስ ደህንነቱ በተጠበቀ እና አስተማማኝ በሆነ መንገድ ያስታውስዎታል።

  ኪፓስኤክስ ለአጠቃቀም ቀላል፣ እና ጠንካራ ሶፍትዌር ስለሆነ ሁሉንም ጠቃሚ ተግባራቱን ለመማር ፕሮግራሙን እንዲያስሱ እንመክራለን።

  Last reviewed: 
  2015-11-23
Next:
JavaScript license information