Surveillance
Self-Defense

ከሸረኛ ሶፍትዌሮች ራሴን እንዴት መከላከል እችላለሁ?

Last reviewed: 
10-31-2014
ይህ ገጽ ከእንግሊዘኛው ቅጂ የተተረጎመ ነው፡፡ የእንግሊዘኛው ቅጂ ምን አልባት የበለጠ የዘመነ ይሆናል፡፡

በእንግሊዝኛው ማልዌር ወይም ማሊሽየስ ሶፍትዌር በአማርኛው ሸረኛ ሶፍትዌር በመባል የሚታወቀው የጥቃት ሶፍትዌር የተለያዩ ኮምፒውተር ተጠቃሚዎችን ለማጥቃት ተንኮለኞች ኾን ብለው የሚሠሩዋቸው ሶፍትዌሮች ናቸው። እነኚህ ማልዌሮች ወይም ሸረኛ ሶፍትዌሮች የኮምፒውተርን መሠረታዊ እንቅስቃሴ በማወክ፣ የተለያዩ መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት፣ እውነተኛ ተጠቃሚን በማስመሰል እና የተለያዩ የውሸት መልዕክቶችን በመላክ፣ የተጠቃሚዎችን ምስጢራዊ መረጃዎች ለማግኘት የሚሞክሩ የምዝበራ ሶፍትዌሮች ናቸው። አብዛኞቹ የሸረኛ ሶፍትዌሮች ለወንጀል ሥራ የሚውሉ ናቸው። እነኚህ የወንጀል ሥራዎች የፋይናንስ መረጃዎችን ከባንክ ወይም ከባንክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በመውሰድ ወይም የኢሚል ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ የመግቢያ ስም እና የማለፊያ ቃል ለመውሰድ ጥቅም ላይ ይውላሉ። በተጨማሪም ሸረኛ ሶፍትዌሮች በተለያዩ የመንግሥት አካላት፣ የሕግ አስፈጻሚ አካላት እና ግለስቦች ተጠዋሚዎችን ለመሰለል ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ። ሸረኛ ሶፍትዌሮች መጠነ ሰፊ የኾነ ችሎታ አላቸው። የድር ካሜራ እና መቅረጸ ድምጽ ግንኙነቶችን መቅዳት፣ አንዳንድ ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች ማስታወቂያ እንዳያሳዩ አድርጎ መቼቱን መቀየር፣ በቁልፍ ሰሌዳ ላይ የነኳቸውን ቁልፎች መቅዳት፣ ኢሜሎች እና የተለያዩ መረጃዎች መቅዳት፣ የይለፍ ቃልን መስረቅ እና የመሳሰሉትን አጥቂዎ እንዲያደርግ ይረዳሉ።

 

ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌር Anchor link

EFF ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌርን በኮምፒውተርዎ እና ስማርት ስልክዎ ላይ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ይኹንና አንደኛው ጸረ ቫይረስ ከሌላኛው ይበልጣል ወይም ያንሳል የሚል አስተያየትን ግን ከመስጠት ይቆጠባል። አንዳንድዎቹ የጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች ብዙ ሰዎችን ለማጥቃት በወንጀለኞች ጥቅም ከሚውሉ ቀላል እና “ያልተነጣጠረ” የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃቶች ለመከላከል በጣም ውጤታማ ሊኾኑ ይችላሉ። ነገር ግን የጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች የተነጣጠሩ ጥቃቶችን በመከላከሉ ረገድ አብዛኛውን ጊዜ ውጤታማ አይደሉም። ለምሳሌ የቻይና መንግስት የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣን ለመሰለል ያደረገውን መጥቀስ ይቻላል።

 

በጥቃት ስር የዋለ ኮምፒውተር ምልክቶች Anchor link

መሣሪያው ላይ የጸረ ቫይረስ ስፍትዌርን በመጠቀም የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት እንደደረሰበት ማወቅ በማይቻልበት ወቅት ጥቃት እንደደረሰበት የሚጠቁሙ ምልክቶች ማግኘት ይቻላል። ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ ጎግል መለያዎ በመንግስት በሚደገፉ አጥቂዎች የጥቃት ኢላማ እንደኾነ የሚገልጽ ማስጠንቀቂያን ለጂሜል ተጠቃሚዎቹ ይሰጣል። በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ የኮምፒውተርዎን ካሜራ (ዌብካም) እርስዎ ሳያበሩት እና በማይጠቀሙበት ወቅት በጥቅም ላይ እየዋለ እንደኾነ የሚያመለክተው መብራት በርቶ (ምንም እንኳን በሳል ሸረኛ ሶፍትዌር መብራቱን ማጥፋት የሚችል ቢኾንም) ሊመለከቱ ይችላሉ። ይህ ኮምፒውተሩ ለጥቃት እንደተጋለጠ የሚያሳይ ሌላ አመልካች ሊኾን ይችላል። ሌሎች አመልካቾች በግልጽ የማይታዩ ናቸው። ለምሳሌ ኢሜልዎ እርስዎ በማያውቁት የIP አድራሻ ጥቅም ላይ ውሎ ወይም የኢሜልዎ መቼት ተቀይሮ የኢሜልዎትን ቅጂዎች በሙሉ ወደማያውቁት ሌላ የኢሜል አድራሻ እንዲልክ ተደርጎ ሊያዩት ይችላሉ። የበይነ መረብ ትራፊክ መስመርን የመገምገም ችሎታ ካለዎት የትራፊኩ ጊዜ እና መጠን ጥቃት እንደደረሰብዎት ሊያመለክት ይችላል። ሌላው አመልካች ሊኾን የሚችለው ኮምፒውተርዎ ከማይታወቅ ትዕዛዝ እና የትዕዛዝ ማዕከል ጋር ግንኙነት ፈጥሮ ሊያዩት ይችላሉ። እነኚህም ሰርቨሮች በሸረኛ ሶፍትዌሩ ለተበከሉት ማሽኖች ትእዛዝን የሚልኩ ወይም ከተበከለት መሳሪያዎች ውሂብን የሚቀበሉ ናቸው።

 

እኔን ለማጥቃት አጥቂዎች ሸረኛ ሶፍትዌርን እንዴት ሊጠቀሙ ይችላሉ? Anchor link

ከሸረኛ ሶፍትዌሮች ጥቃት ራስዎን መከላከያው ጥሩው መንገድ መጀመሪያውኑ በሸረኛ ሶፍትዌር መበከልን ማስወገድ ነው። አጥቂዎ የዜሮ ዴይ አታክ ወይም በአማርኛው ድንገተኛ ያልታሰበ ጥቃት መሰንዘር ከቻለ ይህን ማድረግ አዳጋች ሊኾን ይችላል። የዜሮ ዴይ አታክ በኮምፒውተር መተግበሪያዎች ላይ ያሉ እና ቀድመው ያልታወቁ ተጋላጭነቶችን በመጠቀም የሚደረጉ ጥቃቶች ናቸው። ይህን የጥቃት ዓይነት ለማብራራት የሚከተለውን ምሳሌ ተመልከቱ። ኮምፒውተርዎን ምሽግ እንደኾነ ያስቡ። ወደ ምሽግዎ የሚያስገባ እርስዎ የማያውቁት ነገር ግን አጥቂዎ ያወቀው የተደበቀ የመግቢያ ቀዳዳ ቢኖረው ይህ የመግቢያ ቀዳዳ ዜሮ ዴይ ማለት ነው። በእርግጠኝነት መኖሩን ከማያውቁት እና ከእርስዎ ከተሸሸገ መግቢያ እራስዎን መከላከል አይችሉም። የመንግሥታት እና የሕግ አስፈጻሚ አካላት የተቀነባበረ የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃትን በሰለባዎቻቸው ላይ ለመሰንዘር የዜሮ ዴይ መንገዶችን ይሰበስባሉ። የመስመር ላይ ወንጀለኞች እና ሌሎች ግለሰቦች ይህን ዜሮ ዴይ አታክን የመጠቀም ችሎታ ሊኖራቸው እና በኮምፒውተርዎ ላይም ሸረኛ ሶፍትዌርን ለመጫን ሊጠቀሙት ይችላሉ። ይኹንና ያልታሰበ እና ያልታየ ድብቅ በርን በተለያዩ ሶፍትዌሮች ላይ መኖሩን ማግኘት እጅግ ውድ እና ደግሞ ለመጠቀም የማይቻል (አንዴ ምሽጉን ለመስበር ድብቅ በሩን ከተጠቀሙት በኋላ በሌሎች ሰዎች የመታወቅ እድሉን ይጨምራሉ) ነው። በዚህም የተነሳ አጥቂዎች በብዛት የሚጠቀሙት እርስዎን በማታለል ሸረኛ ሶፍትዌርን በኮምፒውተርዎ ላይ እንዲጭኑ ማድረግን ነው።

በኮምፒውተርዎ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌርን እንዲጭኑ አጥቂዎ እርስዎን ለማታለል ሊጠቀማቸው የሚችሉ የተለያዩ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ በተለያየ የድረ ገጽ ትይይዞች፣ በሰነዶች፣ በPDF ወይም የኮምፒውተርዎን ደህንነት እንዲጠብቁ ታስበው በተሰሩ ፕሮግራሞች ላይ ሸረኛ ሶፍትዌሩን ደብቆ በመጫን ሊኾን ይችላል። በተጨማሪም በኢሜል፣ በስካይፕ እና በትዊተር መልዕት፣ ወይም የፈስቡክ ገጽዎ ላይ በተለጠፈ ትይይዝ አማካኝነት ለሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት ተጋላጭ ሊኾኑ ይችላሉ። ጥቃቱ በጣም የተጠና ከኾነ አጥቂው ሸረኛ ሶፍትዌሩን ለማውረድ አጓጊ አድርጎ ለማቅረብ ብዙ ጥንቃቄ ይወስዳል።

ለምሳሌ በሶሪያ የአሳድ ደጋፊ መዝባሪዎች የሀሰት አቢዮታዊ ሰነዶች እና የሃሰት የጸረ ምዝበራ መሳሪያዎች ላይ የተደበቁ ሸረኛ ሶፍትዌርን በመጠቀም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላቶችን የጥቃት ዒላማ አድርገዋል። ኢራንያውያንም ታዋቂ የቅድመ ምርመራ ማለፊያ ፕርግራምን በመጠቀም የጥቃት ዒላማ ኾነዋል። በተጨማሪም የሞሮኮ አራማጆች ስለ ፖለቲካዊ ቅሌት የሚያወራ ከአልጀዚራ ጋዜጠኛ የተላከ የሚመስል ተያያዥሰነድ ላይ በተደበቀ የሸረኛ ሶፍትዌር አማካኝነት የጥቃት ዒላማ ኾነዋል።

ከእንደዚህ ዓይነት የተነጣጠረ የሸረኛ ሶፍትዌር ብከላ ራስን የመከላከያ ጥሩው መንገድ ከመጀመሪያውኑ ምንም ዓይነት ያልተረጋገጡ ሰነዶችን አለመክፈት እና ሸረኛ ሶፍትዌሩን አለመጫን ነው። የኮምፒውተር ዕውቀታቸው እና ችሎታቸው እጅግ የተሻለ የኾኑ ግለሰቦች የትኛው ሸረኛ እንደሆነ እና የትኛውስ እውነተኛ ሶፍትዌር እንደኾነ በቀላሉ መለየት ቢችሉም ተጠንተው የሚደረጉ ጥቃቶች ግን በጣም አሳማኝ ኾነው ሊቀርቡ ይችላሉ። ጂሜልን የሚጠቀሙ ከኾነ የሚጠራጠሩትን አባሪ ከማውረድ ጎግል ድራቭን ተጠቅሞ ማውረድ ከምፒውተርዎን ከመበከል ሊከላከል ይችላል። እጅግ በጣም ጥቅም ላይ ያልዋሉ ስርዓተ ክወናዎችን ለምሳሌ ኡቡንቱ ወይም ChromeOS በመጠቀም ከብዙ የሸረኛ ሶፍትዌር የማታለል ሰለባነት ራስን መከላከል ቢቻልም ነገር ግን በጣም ውስብስብ ከኾኑ ጥቃቶችም መከላከል አይቻልም።

የሶፍትዌሮች የመጨረሻ ብጅትን መጠቀም እና የመጨረሻ ዝማኔ ላይ ያሉ የደህንነት ጠጋኞችን እንዳወረዱ ሁልጊዜ ማረጋገጥ ኮምፒውተርዎን ከሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት ለመከላከል ሌላው ማድረግ የሚችሉት ነገር ነው። በአንድ ሶፍትዌር ላይ የአደጋ ተጋላጭነት ሲታይ ሶፍትዌሩን ያመረተው ኩባንያ ችግሮቹን ይጠግን እና መጠገኛውን በሶፍትዌር ማዘመኛነት ያቀርበዋል። ነገር ግን በኮምፒውተርዎ ላይ ማዘመኛውን ካልጫኑ በስተቀር የዚህ ሥራ ጥቅም ተካፋይ መኾን አይችሉም። በሕጋዊ መንገድ ያልተገዛ ወይም ያልተመዘገበ የዊንዶውስ ስርዓተ ክወና ቅጂን የሚጠቀም ሰው የደህንነት ዝማኔዎችን ማድረግ አይቻልም ተብሎ ቢታመንም ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ ትክክል አይደለም

 

በኮምፒውተሬ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌር ካገኘሁ ምን ማድረግ አለብኝ? Anchor link

ኮምፒውተርዎ የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት እንደደረሰበት ካወቁ ማድረግ ያለብዎት ወዲያውኑ የኢንተርኔት ግንኙነቱን ማቋረጥ ነው። እያንዳንዱ የሚነኩት የኮምፒውተሩ ቁልፍ በሸረኛ ሶፍትዌሩ አማካኝነት ለአጥቂዎ ሊላክ ይችላል። በተጨማሪም የኮምፒውተር ደህንነት ባለሞያ ጋር በመውሰድ በኮምፒውተርዎ ላይ የተጫነው ሸረኛ ሶፍትዌር ዝርዝር መረጃ ማወቅ አለብዎት። በኮምፒውተርዎ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌር ካገኙ ሸረኛ ሶፍትዌሩን ማስወገድ የኮምፒውተርዎን ደህንነት አያረጋግጥም። አንዳንድ ሸረኛ ሶፍትዌሮች አጥቂው በተጠቃው ኮምፒውተር ላይ ከሩቅ ቦታ በመኾን ሌሎች የኮምፒውተር ኮዶችን እንዲጭን ማድረግ ይችላል። በተጨማሪም አጥቂው ኮምፒውተርዎን በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ በነበረበት ወቅት ተጨማሪ ሌላ ሸረኛ ሶፍትዌሮች ስላለመጫኑ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ የለዎትም።

ከዚህ ጥቃት ራስዎን ለመከላከል ደህንነቱ የተረጋገጠ እንደኾነ በሚያምኑት ኮምፒውተር በመግባት የማለፊያ ቃልዎትን ይቀይሩ። ኮምፒውተርዎ በጥቃት ላይ በነበረበት ወቅት የተጠቀሟቸው የማለፊያ ቃላት በሙሉ በአጥቂዎ እንደተወሰዱ ማሰብ ይኖርብዎታል።

ከደረሰበት የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት ለማንጻት የኮምፒውተርዎን ስርዓተ ክወና እንደ አዲስ መጫን ሊኖርብዎት ይችላል። ይህን ማድረግ አብዛኞቹን ሸረኛ ሶፍትዌሮች ሲያስወግድ ነገር ግን አንዳንድ እጅግ በጣም ውስብስብ የኾኑ ሸረኛ ሶፍትዌሮችን ላያስወግድ ይችላል። ኮምፒውተርዎ መቼ እንደተበከለ የሚያውቁ ከኾነ ጥቃቱ ከደረሰበት ቀን በፊት የነበሩትን ሰነዶች ብቻ ለይተው መገልበጥ አለብዎት። ምክንያቱም ጥቃት ላይ ከወደቀ ቀን በኋላ የተጫኑ ሰነዶች እንደገና ሲገለብጡ ኮምፒውተርዎን በሸረኛ ሶፍትዌር መልሰው ሊበክሉ ስለሚችሉ ነው።

 

ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌር Anchor link

EFF ጸረ ቫይረስ ሶፍትዌርን በኮምፒውተርዎ እና ስማርት ስልክዎ ላይ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ነገር ግን አንደኛው ጸረ ቫይረስ ከሌላኛው ይበልጣል ወይም ያንሳል የሚል አስተያየትን ከመስጠት ይቆጠባል። አንዳንድዎቹ የጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች ብዙ ሰዎችን ለማጥቃት በወንጀለኞች ጥቅም ከሚውል ቀላል እና “ያልተነጣጠረ” የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃቶች ለመከላከል በጣም ውጤታማ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን የጸረ ቫይረስ ሶፍትዌሮች የተነጣጠሩ ጥቃቶችን በመከላከሉ ረገድ አብዛኛውን ጊዜ ውጤታማ አይደሉም። ለምሳሌ የቻይና መንግስት የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣን ለመሰለል ያረገው መጥቀስ ይቻላል።

 

በጥቃት ስር የዋለ ኮምፒውተር ምልክቶች Anchor link

መሳሪያው ላይ የጸረ ቫይረስ ስፍትዌርን በመጠቀም የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት እንደደረሰበት ማወቅ በማይቻልበት ወቅት ጥቃት እንደደረሰበት የሚጠቁሙ ምልክቶች ማግኘት ይቻላል። ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ ጎግል መለያዎ በመንግስት በሚደገፉ አጥቂዎች መለያዎ የጥቃት ኢላማ እንደሆነ የሚገልጽ ማስጠንቀቂያን ለጂሜል ተጠቃሚዎቹ ይሰጣል። በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ የኮምፒውተርዎን ካሜራ (ዌብካም) እርስዎ ሳያበሩት እና በማይጠቀሙበት ወቅት በጥቅም ላይ እየዋለ እንደሆነ የሚያመለክተው መብራት በርቶ (ምንም እንኳን በሳል ሸረኛ ሶፍትዌር መብራቱን ማጥፋት የሚችሉ ቢሆንም) ሊመለከቱ ይችላሉ። ይህ ኮምፒውተሩ ለጥቃት እንደተጋለጠ የሚያሳይ ሌላ አመልካች ሊሆን ይችላል። ሌሎች አመልካቾች በግልጽ የማይታዩ ናቸው። ለምሳሌ ኢሜልዎ እርስዎ በማያውቁት የIP አድራሻ ጥቅም ላይ ውሎ ወይም የኢሜልዎ መቼት ተቀይሮ የኢሜልዎትን ቅጂዎች በሙሉ ወደማያውቁት ሌላ የኢሜል አድራሻ እንዲልክ ተደርጎ ሊያዩት ይችላሉ። የበይነ መረብ ትራፊክ መስመርን የመገምግም ችሎታ ካልዎት የትራፊኩ ጊዜ እና መጠን ጥቃት እንደደረሰብዎት ሊያመለክት ይችላል። ሌላው አመልካች ሊሆን የሚችለው ኮምፒውተርዎ ከማይታወቅ ትእዛዝ እና የትእዛዝ ማእከል ጋር ግንኙነት ፈጥሮ ሊያዩት ይችላሉ። እነኚህም ሰርቨሮች በሸረኛ ሶፍትዌሩ ለተበከሉት ማሽኖች ትእዛዝን የሚልኩ ወይም ከተበከለት መሳሪያዎች ውሂብን የሚቀበሉ ናቸው።

 

እኔን ለማጥቃት አጥቂዎች ሸረኛ ሶፍትዌርን እንዴት ሊጠቀሙ ይችላሉ? Anchor link

ከሸረኛ ሶፍትዌሮች ጥቃት እራስን መከላከያው ጥሩው መንገድ ከመጀመሪያው በሸረኛ ሶፍትዌር መበከልን ማስወገድ ነው። አጥቂዎ የዜሮ ዴይ አታክ ወይም በአማርኛው ድንገተኛ ያልታሰበ ጥቃት መሰንዘር ከቻለ ይህን ማድረግ አዳጋች ሊሆን ይችላል። የዜሮ ዴይ አታክ የሚባለው በኮምፒውተር መተግበሪያዎች ላይ ያሉ ቀድመው ያልታወቁ ተጋላጭነቶችን በመጠቀም የሚደረጉ ጥቃቶች ናቸው። ይህን የጥቃት አይነት ለማብራራት የሚከተለውን ምሳሌ ተመልከቱ። ኮምፒውተርዎን ምሽግ እንደሆነ ያስቡ እና ወደ ምሽግዎ የሚያስገባ እርስዎ የማያውቁት ነገር ግን አጥቂዎ ያወቀው የተደበቀ የመግቢያ ቀዳዳ ቢኖረው ይህ የመግቢያ ቀዳዳ ዜሮ ዴይ ማለት ነው። መኖሩን ከማያውቁት የተደበቀ መግቢያ እራስዎን መከላከል አይችሉም። የመንግስታት እና የህግ አስፈጻሚ አካላት የተቀነባበረ የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃትን በሰለባዎቻቸው ላይ ለመሰንዘር የዜሮ ዴይ መንገዶችን ይሰበስባሉ። የመስመር ላይ ወንጀለኞች እና ሌሎች ግለሰቦች ይህን ዜሮ ዴይ አታክን የመጠቀም ችሎታ ሊኖራቸው እና ተደብቀው በኮምፒውተርዎ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌርን ለመጫን ሊጠቀሙት ይችላሉ። ነገር ግን ያልታሰበ እና ያልታየ ድብቅ በርን በተለያዩ ሶፍትዌሮች ላይ መኖሩን ማግኘት እጅግ ውድ እና ደግሞ ለመጠቀም የማይቻል (አንዴ ምሽጉን ለመስበር ድብቅ በሩን ከተጠቀሙት በኋላ በሌሎች ሰዎች የመታወቅ እድሉን ይጨምራሉ) ነው። በዚህም የተነሳ አጥቂዎች በብዛት የሚጠቀሙት እርስዎን በማታለል ሸረኛ ሶፍትዌርን በኮምፒውተርዎ ላይ እንዲጨኑ ማድረግን ነው።

በኮምፒውተርዎ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌርን እንዲጭኑ አጥቂዎ እርስዎን ለማታለል ሊጠቀማቸው የሚችሉ የተለያዩ መንገዶች አሉ። ለምሳሌ በተለያየ የድረ ገጽ ትይይዝዎች፣ በሰነዶች፣ በPDF ወይም የኮምፒውተርዎን ደህንነት እንዲጠብቁ ታስበው በተሰሩ ፕሮግራሞች ላይ ሸረኛ ሶፍትዌሩን ደብቆ በመጫን ሊሆን ይችላል። በተጨማሪም በኢሜል፣ በስካይፕ እና በቲዊተር መልእት፣ ወይም የፈስቡክ ገጽዎ ላይ በተለጠፈ ትይይዝ አማካኝነት ለሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ። ጥቃቱ በጣም የተጠና ከሆነ አጥቂው ሸረኛ ሶፍትዌሩን ለማውረድ አጓጊ አድርጎ ለማቅረብ ብዙ ጥንቃቄ ይወስዳል።

ለምሳሌ በሶሪያ የአሳድ ደጋፊ መዝባሪዎች የሀሰት አቢዮታዊ ሰነዶች እና የሃሰት የጸረ ምዝበራ መሳሪያዎች ላይ የተደበቁ ሸረኛ ሶፍትዌርን በመጠቀም የተቃዋሚ ፓርቲ አባላቶችን የጥቃት ኢላማ አድርገዋል። ኢራንያዊያንም ታዋቂ የቅድመ ምርመራ ማለፊያ ፕርግራምን በመጠቀም የጥቃት ኢላማ ሆነዋል። በተጨማሪም የሞሮኮ አራማጆች ስለ ፖለቲካዊ ቅሌት የሚያወራ ከአልጀዚራ ጋዜጠኛ የተላከ የሚመስል ሰነድ ላይ በተደበቀ የሸረኛ ሶፍትዌር አማካኝነት የጥቃት ኢላማ ሆነዋል።

ከእንደዚህ አይነት የተነጣጠረ የሸረኛ ሶፍትዌር ብከላ ራስን የመከላከያ ጥሩው መንገድ ከመጀመሪያውኑ ምንም አይነት ያልተረጋገጡ ሰነዶችን አለመክፈት እና ሸረኛ ሶፍትዌሩን አለመጫን ነው። የኮምፒውተር እውቀታቸው እና ችሎታቸው እጅግ የተሻለ የሆኑ ግለሰቦች የቱ ሸረኛ ሶፍትዌር እንደሆነ እና የቱ እውነተኛ ሶፍትዌር እንደሆነ በቀላሉ መለየት ቢችሉም ተጠንተው የሚደረጉ ጥቃቶች ግን በጣም አሳማኝ ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ። ጂሜልን የሚጠቀሙ ከሆነ የሚጠራጠሩትን አባሪ ከማውረድ ጎግል ድራቭን ተጠቅሞ ማውረድ ከምፒውተርዎን ከመበከል ሊከላከል ይችላል። እጅግ በጣም ጥቅም ላይ ያልዋሉ ስርአተ ክወናዎችን ለምሳሌ ኡቡንቱ ወይም ChromeOS በመጠቀም ከብዙ የሸረኛ ሶፍትዌር የማታለል ሰለባነት ራስን መከላከል ቢቻልም ነገር ግን በጣም ውስብስብ ከሆኑ ጥቃቶችም መከላከል አይቻልም።

የሶፍትዌሮች የመጨረሻ ብጅትን መጠቀም እና የመጨረሻ ዝማኔ ላይ ያሉ የደህንነት ጠጋኞችን እንዳወረዱ ሁልጊዜ ማረጋገጥ ኮምፒውተርዎን ከሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት ለመከላከል ሌላው ማድረግ የሚችሉት ነገር ነው። በአንድ ሶፍትዌር ላይ የአደጋ ተጋላጭነት ሲታይ ሶፍትዌሩን ያመረተው ኩባንያ ችግሮቹን ይጠግን እና መጠገኛውን በሶፍትዌር ማዘመኛነት ያቀርበዋል። ነገር ግን በኮምፒውተርዎ ላይ ማዘመኛውን ካልጫኑ በስተቀር የዚህ ስራ ጥቅም ተካፋይ መሆን አይችሉም። በህጋዊ መንገድ ያልተገዛ ወይም ያልተመዘገበ የዊንዶውስ ስርአተ ክወና ቅጂን የሚጠቀም ሰው የደህንነት ዝማኔዎችን ማድረግ አይቻልም ተብሎ ቢታመንም ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ ትክክል አይደለም

 

በኮምፒውተሬ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌር ካገኘሁ ምን ማድረግ አለብኝ? Anchor link

ኮምፒውተርዎ የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት እንደደረሰበት ካወቁ ማድረግ ያለብዎት ወዲያውኑ የኢንተርኔት ግንኙነቱን ማቋረጥ እና መጠቀም ማቆም ነው። እያንዳንዱ የሚነኩት የኮምፒውተሩ ቁልፍ በሸረኛ ሶፍትዌሩ አማካኝነት ለአጥቂዎ ሊላክ ይችላል። በተጨማሪም የኮምፒውተር ደህንነት ባለሙያ ጋር በመውሰድ በኮምፒውተርዎ ላይ የተጫነው ሸረኛ ሶፍትዌር ዝርዝር መረጃ ማወቅ አለብዎት። በኮምፒውተርዎ ላይ ሸረኛ ሶፍትዌር ካገኙ ሸረኛ ሶፍትዌሩን ማስወገድ የኮምፒውተርዎን ደህንነት አያረጋግጥም። አንዳንድ ሸረኛ ሶፍትዌሮች አጥቂው በተጠቃው ኮምፒውተር ላይ ከሩቅ ቦታ በመሆን ሌሎች የኮምፒውተር ኮዶችን እንዲጭን ማድረግ ይችላል። በተጨማሪም አጥቂው ኮምፒውተርዎን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ በነበረበት ወቅት ተጨማሪ ሌላ ሸረኛ ሶፍትዌሮች ስላለመጫኑ ምንም አይነት ማረጋገጫ የልዎትም።

ከዚህ ጥቃት ራስዎን ለመከላከል ደህንነቱ የተረጋገጠ እንደሆነ በሚያምኑት ኮምፒውተር በመግባት የማለፊያ ቃልዎትን ይቀይሩ። ኮምፒውተርዎ በጥቃት ላይ በነበረበት ወቅት የተጠቀሟቸው የማለፊያ ቃላት በሙሉ በአጥቂዎ እንደተወሰዱ ማሰብ ይኖርብዎታል።

ከደረሰበት የሸረኛ ሶፍትዌር ጥቃት ለማንጻት የኮምፒውተርዎን ስርአተ ክወና እንደ አዲስ መጫን ሊኖርብዎት ይችላል። ይህን ማድረግ አብዛኞቹን ሸረኛ ሶፍትዌሮች ሲያስወግድ ነገር ግን አንዳንድ እጅግ በጣም ውስብስብ የሆኑ ሸረኛ ሶፍትዌሮችን ላያስወግድ ይችላል። ኮምፒውተርዎ መቼ እንደተበከለ የሚያውቁ ከሆነ ጥቃቱ ከደረሰበት ቀን በፊት የነበሩትን ሰነዶች ብቻ ለይተው መግልበጥ አለብዎት። ምክኒያቱም ጥቃት ላይ ከወደቀ ቀን በኋላ የተጫኑ ሰነዶች እንደገና ሲገለብጡ ኮምፒውተርዎን በሸረኛ ሶፍትዌር መልሰው ሊበክሉ ስለሚችሉ ነው።

JavaScript license information