የቻትሴኪዩር አጫጫን እና አጠቃቀም

ቻትሴኪዩር ለአይፎን እና አንድሮድ ስልኮች ነጻ የተንቀሻቃሽ ስልክ መተግበሪያ ሲሆን ተጠቃሚዎችን ከመዝገብ ውጪ የሆነ ፈጣን መልዕክት ግንኙነትን እንዲያደርጉ ያግዛል። በተጨማሪም በላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውር ፈንታ የተንቀሳቃሽ ስልክን በመጠቀም ፈጣን መልዕክቶችን እና የመስመር ላይ ውይይቶችን ተጠቃሚዎች እንዲያደርጉ ይረዳል። ቻትሴኪዩር ከአይፎን እና ከአንድሮይድ ስልኮች ጋር ተኳኋኝ ነው።

ቻትሴኪዩር የOTR ምስጠራን በXMPP አማካኝነት ያስችላል። እየተወያዩት ያለው ሰው እንደ ቻትሴኪዩር፣ አዲየም፣ ፒጂን ወይም ጂትሲ የተባሉትን የOTR ተኳኋኝ የፈጣን መልዕክት ደምበኛ እየተጠቀመ እስከሆነ ድረስ በቻትሴኪዩር የሚላኩ ሁሉም መልዕክቶች ሙሉ በሙሉ የግል ናቸው። የመተግበሪያው ተኳኋኝነት የድምጽ መልዕክቶችን፣ ፎቶዎችን፣ ፋይሎችን ወይም የጽሁፍ ምልክቶችን የማድረስ ችሎታ አለው።

ቻትሴኪዩርን ተጠቅመው መልእክቶችን ሲልኩ መልዕክቱ በስልኩ ማህደረ ትውስታ ስርዓት ውስጥ አይቀመጥም። ቻትሴኪዩር ኦርቢት ከተሰኘው የግላዊነት ተሰኪ ጋር ጥቅም ላይ ከዋለ አብዛኛውን ኬላዎች፣ የአውታረ መረብ ገደቦች እና ጥቁር መዛግብትን ማለፍ ይቻላል። ይህ መተግበሪያ ብዙ መለያዎችን በአንድነት ማስተዳደር ያስችላል። ስለዚህ ከፌስቡክ ባልንጀሮች፣ ከጎግል ዕውቂያዎች ወይም የኦቲአር ምስጠራን የሚያስችሉ የፈጣን መልዕክት ፕሮግራሞችን ከሚጠቀሙ ሌሎች ስለ ግላዊነት ንቃተ ህሊና ካላቸው ተጠቃሚዎች ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላሉ።

ቻትሴኪዩርን መጫን እና ማዋቀር እንዴት ይችላሉ Anchor link

1.ቻትሴኪዩርን ማውረድ እና መጫን

የአፕል አፕ ስቶርን ወይም የጎግል ፕሌይ ስቶርን ይጎብኙ እና ቻትሴኪዩር በዘ ጋርዲያን ፕሮጅክት የሚለውን ይፈልጉ። “ኢንስቶል” የሚለውን ይምረጡ እና “አክሴፕት” የሚለውን ጠቅ በማድረግ የአገልግሎት ኹኔታዎችን እና ስምምነቶችን ይቀበሉ። መተግበሪያው ይወርድ እና በቀጥታ ይጫናል።

2. መተግበሪያውን ይክፈቱ እና የማለፊያ ቃልዎን ይፍጠሩ

መተግበሪያውን እንደከፈቱ የማለፊያ ቃልን እንዲፈጥሩ ይጠየቃሉ። በስልኮ ላይ ያሉ ውሂቦን ለማመስጠር የማለፊያ ሐረግ ይፈጥይሩ እንደሆን ፍቃድዎ ይፈለጋል። ይህንን ማድረግ ከመረጡ በመተለለፍ ላይ ያለው እንዲሁም በስልክዎት ላይ ያለው ውሂብ ይመሰጠራል።

ይህን ደረጃ ከዘለሉት በመተላለፍ ላይ ያለው መልዕክትዎ የሚመሰጠር ቢሆንም በስልክዎት ላይ ያለው ውሂብ ግን ደህንነቱ አይጠበቅም። ጠንካራ የማለፊያ ሐረግ አመራረጥን በተመለከተ ለበለጠ መረጃ በማለፊያ ቃል ዙሪያ ላይ የተዘጋጀ ሞጁላችንን ይመልከቱ።

3. መለያዎችዎን ማዋቀር

በቻትሴኪዩር መተግበሪያ ውስጥ የተለያዩ መለያዎችን መጨመር ይችላሉ። የጎግልቶክ ወይም የጎግል ሃንግአውት መለያን ለመጨመር “ጎግል” የሚለውን ይምረጡ። የXMPP ወይም የጃብር የመልዕክት አገልግሎትን ለመጨመር “ጃብር (XMPP)” የሚለውን ይምረጡ። የፌስቡክ መለያዎንም ለመጨመር “ጃብር (XMPP)” ይምረጡ።

መለያዎን አንዴ ከጨመሩ በኋላ ለመግባት የተጠቃሚ ስምዎትን (ወይም የኢሜል አድራሻዎትን) እና የማለፊያ ቃልዎትን ያስገቡ። ዕውቂያዎችዎ ወዲያውኑ ይጫናሉ።

ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መለያን ለመጨመር ከምናሌው ላይ “አካውንትስ” የሚለው ትር ላይ ጠቅ ያድርጉ። በላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ የሚገኘው የ“+” ምልክት ላይ ጠቅ ያድረጉ። ቀጥሎም ቀድሞ የተዘጋጀውን መለያዎን መጨመር ወይም አዲስ መለያ መፍጠር ምርጫዎ ይሆናል።

ቻትሴኪዩርን እንዴት መጠቀም ይችላሉ Anchor link

1. መለያዎችዎ ውስጥ ይግቡ

መለያዎችዎ ውስጥ ለመግባት ከምናሌው ላይ “አካውንትስ” የሚለው ትር ላይ ጠቅ ያድርጉ። በመቀጠልም መጠቀም የሚፈልጉትን መለያ ያስጀምሩ። መለያዎት ውስጥ አንዴ ከገቡ ማንኛውም ሰው ከተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ከዴስክቶፕ የፈጣን መልዕክት መተግበሪያ ከእርስዎ ጋር ግንኙነት ማድረግ ይችላል።

2. ከዳር እስከ ዳር ምስጠራን ማስጀመር

አንዴ መወያየት ከጀመሩ በኋላ በማሳያው የላይኛው ክፍል ምናሌ አሞሌ ላይ ያለውን ያልተቆለፈ የቁልፍ አዶት ጠቅ ያድርጉ። ከዛም “ስታርት ኢንክሪፕሽን” የሚለውን ይምረጡ። እየተወያዩት ያለው ሰው ከOTR ጋር ተኳኋኝ የኾነ የፈጣን መልዕክት ስርዓት ተጠቃሚ ከሆነ የእርስዎን (እና የሱን) የጣት አሻራ የማረጋገጥ ዕድሉ ይኖርዎታል።

ቻትሴኩዩር የOTR የጣት አሻራን የሚያረጋግጡበት ሦስት የተለያዩ አማራጮች አሉት። ነገር ግን እየተወያዩ ያሉት በዴስክቶፕ የፈጣን መልእክት ሜሴንጀር ከሆነ እና በቻትሴኪዩር ካልሆነ የOTR የጣት አሻራን ለማረጋገጥ የተሻለው መንገድ ሌላ የግንኙነት መንገዶችን በመጠቀም ነው። በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (ቴክስትሴኬዩር)፣ የሌላኛውን ሰው ድምጽ የሚለዩት ከሆነ በስልክ በመንገር፣ PGP ኢሜልን በመጠቀም የጣት አሻራዎን መልሰው በመላክ ወይም በአካል በመገናኘት ማረጋገጥ ይችላሉ። “ማኗል ቬሪፊኬሽን” የሚለው ላይ ጠቅ ያድርጉ እና ቻትሴኪዩር የእርስዎን እና የጓደኛዎን የጣት አሻራ ያሳይዎታል። ሁለታችሁም አንድ ዓይነት መረጃ እንዳላችሁ ማረጋገጥ ከቻሉ “ቬሪፋይ” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

ቻትሴኪዩር በእጅ ማረገገጥ ወይም የሌላ ተጠቃሚዎችን መሰውር (QR) በማሰስ ማረጋገጥን ያስችላል። ቁልፉን ከሚያረጋግጡት ሰው ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ከኾኑ መሰውሩን ከስልኩ ላይ በቀላሉ ማሰስ ወይም ቁልፋችሁን አንደኛው ለሌላኛው ማንበብ ትችላላችሁ።

3. ምርጫዎችን መረዳት

  • ልክ እንደሌሎች የዴስክቶፕ ፈጣን መልዕክት አገልግሎት ቻትሴኪዩርም ከመስመር ውጪ፣ ሥራ ላይ ነኝ፣ ስራ ፈቷል ወይም “የለሁም”ን መስለው እንዲቀርቡ ምርጫ ይሰጥዎታል። ይህንን መዋቅር ለመቀየር ከጓደኛዎችዎ ዝርዝር በላይ ያለው የእርሶ ስም ላይ ጠቅ ያድርጉ።
  • ቻትሴኪዩር የቡድን ውይይትን እና አዲስ ዕውቂያን እንዲጨምሩ ይፈቅዳል። ሁለቱንም ከዋናው ምናሌ ላይ ማከናወን ይችላሉ። (ያስተውሉ በOTR ስርዓት ውስንነት የተነሳ ልክ እንደ አንድ ለአንድ ውይይቶች የቡድን ውይይቶችን ደህንነት ማረጋገጥ አይቻልም።)
  • ጓደኛዎ ከዳር እስከ ዳር ማመስጠሪያን የሚጠቀም ከኾነ እና የጓዳኛዎን ማንነት ማረጋገጥ ከቻሉ የመተግበሪያው ማህደር ብዙ መረጃ መላክን፣ ፎቶ ማንሳት፣ እና ፎቶዎችን እና ፋይሎችን ደህንነቱ በተጠቀበቀ መንገድ መላክን ያስችላል።
  • ቻትሴኪዩር የOTR ማመስጠሪያን የሚደግፍ አዲስ የXMPP ወይም የጃብር ሜሴጂንግ መለያን እንዲፈጥሩ ምርጫ ይሰጥዎታል። እስከአሁን የXMPP ሜሴጂንግ ተጠቃሚ ካልሆኑ የXMPP መለያ ለመፍጠር እና ያለክፍያ የሚሰጥ የሜሴጅ አግልግሎትን ለመሞከር መልካም አጋጣሚ ነው።
Last reviewed: 
2014-10-17
ይህ ገጽ ከእንግሊዘኛው ቅጂ የተተረጎመ ነው፡፡ የእንግሊዘኛው ቅጂ ምን አልባት የበለጠ የዘመነ ይሆናል፡፡
JavaScript license information