Surveillance
Self-Defense

ለዊንዶውስ የቶር አጠቃቀም

ይህ መመሪያ በዊንዶውስ ላይ ቶር ብራውዘር በንድልን እንዴት እንደምንጠቀም ይዘረዝራል።

Last reviewed: 
11-4-2015
ይህ ገጽ ከእንግሊዘኛው ቅጂ የተተረጎመ ነው፡፡ የእንግሊዘኛው ቅጂ ምን አልባት የበለጠ የዘመነ ይሆናል፡፡
 

ቶር ምንድን ነው? Anchor link

ቶር መስመር ላይ ማን እንደኾኑ እና የት ሆነው ግንኙነት እንደሚያደርጉ በመሸፈን ድብቅነትን እና ግላዊነትን የሚያስጠብቅ በበጎ ፈቃደኞች የሚሰጥ አገልግሎት ነው። ይህ አገልግሎት ከራሱ ከቶር አውታረ መረብ ጭምር ይከላከላል።

አንዳንድ ድረ ገጾችን በሚዳስሱበት ወቅት አልፎ አልፎ ድብቅነትን እና ግለኝነትን መጠበቅ ለሚፈልጉ ሰዎች የቶር ማሰሻ ፈጣን እና ቀላል የቶር አውታረ መረብን (ኔት ዎርክ) መጠቀሚያ ዘዴ ነው።

የቶር ማሰሻ በንድል የቶር አውታረ መረብን መጠቀሚያ ቀላሉ መንገድ ሲኾን ይህም የድር ማሰሻን፣ ቶር ሶፍትዌርን እና ደህንነቱ በተጠበቀ ኹኔታ ድርን ለማሰስ የሚረዱ ሌሎች ጠቃሚ ሶፍትዌሮችን በአንድነት የያዘ ነው።

የቶር ብራውዘር ግንኙነትዎን በቶር ኔትወርክ አማካኝነት ከማድረጉ በስተቀር የሚሠራው ከሌሎች የድር ማሰሻዎች ጋር በተመሳሳይ መልኩ ነው። ይህም መስመር ላይ ምን እየሠሩ እንደኾነ ማወቅን እና እየተጠቀሙት ያለውን ድረ ገጽ ከየት ኾነው እንደከፈቱት ማወቅ እርስዎን ለሚቆጣጠሩ ሰዎች አዳጋች ያደርግባቸዋል። በቶር ብራውዘር ውስጥ ገብተው የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ብቻ ድብቅ እንደሚኾን ይወቁ። የቶር ብራውዘር በኮምፒውተርዎ ላይ ተጫነ ማለት በተመሳሳይ ኮምፒውተር ሌላ ሶፍትዌሮችን (ለምሳሌ መደበኛ የድር መዳሰሻዎን) በመጠቀም የሚሠሯቸውን ስራዎችን ድብቅ አያደርግም።

 

የቶር ብራውዘር በንድልን ማግኘት Anchor link

እንደ ሞዚላ ፋየርፎክስ ወይም ኢንተርኔት ኤክስፕሎረር ያሉ የድር ማሰሻን ይክፈቱ እና በURL አሞሌው ላይ https://www.torproject.org/projects/torbrowser.html.en ይህንን ይጻፉ። የቶር ብራውዘር በንድልን ለመፈለግ የፍለጋ ፕሮግራሙን የሚጠቀሙ ከኾነ የጻፉት URL ትክክል መኾኑን ያረጋግጡ።

How to Use Tor 1

የቶር ብራውዘር በንድል የመጫኛ ፕሮግራሙን ለማግኘት ዳውንሎድ የሚለውን ትልቅ ሃምራዊውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

How to Use Tor 2

ድረ ገጹ በኮምፒውተርዎ ላይ የተጫነውን ስርዓተ ክወና ያጣራና ለዊንዶስ ትክክለኛ የኾነውን ፋይል ያወርድልዎታል። በማንኛውም ምክንያት የተለየ የመጫኛ ፋይል ማውረድ ከፈለጉ ወደ ቶር ብራውዘር ዳውንሎድ ክፍል ቁልቁል ማሸብለል ይችላሉ።

How to Use Tor 3

አብዛኞቹ የድር ማሰሻዎች ይህንን ሰነድ ማውረድ እንደሚፈልጉ ማረጋገጫ ይጠይቅዎታል። የኢንተርኔት ኤክስፕሎረር 11ኛው ስሪት በድር መዳሰሻው ገጽ የታችኛው ክፍል ላይ ብርቱካናማ ክፈፍ ያለው አሞሌ ያሳያል።

How to Use Tor 4

ለማንኛውም የድር ማሰሻ እጅግ በጣም ተመራጭ የሚኾነው ወደሚቀጥለው እንቅስቃሴ ከመግባትዎ በፊት ያወረዱትን ሰነድ ማስቀመጥ ነው። ስለዚህም “ሴቭ” የሚለው አዝራር ላይ ጠቅ ያድርጉ። ይህ ምሳሌ ይህን መመሪያ በጻፍንበት ወቅት የመጨረሻ ስሪት የነበረውን ቶር ብራውዘር በንድል 3.6.2 መሠረት የተዘጋጀ ነው። ይህን በሚያነቡበት ወቅት ከዚህ የቀረበ አዲስ ስሪት ለማውረድ ተዘጋጅቶ ሊያገኙ ይችላሉ።

 

ቶር ብራውዘር በንድልን መጫን Anchor link

ቶርን አውርዶ ከጨረሰ በኋላ ፋይሉ የወረደበትን ማህደር መክፈት የሚያስችል ምርጫ ሊያገኙ ይችላሉ። በነባሪ የሚወርድብት ሥፍራ የማውረጃ ማህደሩ ነው። torbrowser-install-3.6.2_en-US.exe የሚለው ፋይል ላይ ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ።

How to Use Tor 5

በቶር ብራውዘር መጫኛ ላይ ሁለቴ ጠቅ ካደረጉ በኋላ ስለ ሶፍትዌሩ ስርዓት ጠባይ የሚያስጠነቅቅ መልዕክት የያዘ መስኮት ይከፈታል። ሁልጊዜም እንዲህ ዓይነቱን ማስጠንቀቂያ ከቁም ነገር መውሰድ እና መጫን የፈለጉትን ሶፍትዌር እንደሚያምኑት እና እውነተኛ ቅጂውን ደህንነቱ የተመሰከረለት ግንኙነትን በመጠቀም ከኦፊሴላዊ ድረ ገጹ ላይ እንዳገኙት ማረጋገጥ ይገባዎታል። የሚፈልጉት ምን እንደኾነ፣ ሶፍትዌሩን የት እንደሚያገኙት ስለሚያውቁ እና ያወረዱት ደህንነቱ ከተመሰከረለት የቶር ፕሮጀክትስ HTTPS ድረ ገጽ ላይ እስከኾነ ድረስ ይቀጥሉ እና "ራን" የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

How to Use Tor 6

ትንሽ መስኮት ይከፈት እና በምን ቋንቋን ቶር ብራውዘር በንድሉን መጠቀም እንደሚፈልጉ ይጠይቅዎታል። ብዙ አማራጮች አሉ። የሚፈልጉትን ቋንቋ ይምረጡ እና "ኦኬ" የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

How to Use Tor 7

የቶር ብራውዘር በንድሉ በኮምፒተርዎ ላይ የት ቦታ እንደሚጫን የሚነግርዎት አዲስ መስኮትን ያገኛሉ። በነባሪ የሚጫንበት ስፍራ ዴስክቶፕ ላይ ነው። ከፈለጉ ይህንን ወደተለየ ቦታ መለወጥ ይችላሉ፤ ነገር ግን ለአሁን በነባሪው ይተውት።

How to Use Tor 8

የመጫን ሂደቱ የሚያበቃው የመጫን ሂደቱን ጨርሰዋል የሚል መልዕክት የያዘ መስኮት ሲያዩ ነው። "ፊኒሽ" የሚለውን አዝራር ጠቅ ሲያደርጉ የቶር ብራውዘር ወዲያውኑ ይጀምራል። ለአሁን “ራን ቶር ብራውዘር በንድል” የሚለውን አያመልክቱት። የቶር ብራውዘር በንድልን መጠቀምን ከትንሽ ጊዜ በኋላ እንመለስበታለን። አመልካች ሳጥኑን ሳያመለክቱ ካለፉ እና የቶር ብራውዘር ሥራውን ከጀመረ ለጊዜው መስኮቱን ይዝጉት።.

How to Use Tor 9

የቶር ብራውዘር በንድል በኮምፒውተርዎ ላይ ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር አብሮ አይጫንም እናም የ"ስታርት" ምናሌ ውስጥ አይታይም።

 

How to Use Tor 10

 

ቶር ብራውዘር በንድልን መጠቀም Anchor link

ቶር ብራውዘርን ለመጀመሪያ ጊዜ ማስጀመር

የቶር መጫኛ የአጫጫን ሂደቱን ሲጨርስ ቶር ብራውዘርን እንዳያስጀምር መርጣችኋል ስለዚህ አሁን ይቀጥሉ እና ቶር ብራውዘርን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀምሩት። የመጫኛውን የነባሪ መዋቅሮች ሁሉንም ከተከተሉ በዲስክቶፕዎ ላይ ቶር ብራውዘር የሚል ማህደር ያገኛሉ።

How to Use Tor 11

የቶር ብራውዘር ማህደርን ይክፈቱ እና "ስታርት ቶር ብራውዘር" የሚለው ፋይል ላይ ሁለቴ ጠቅ ያድርጉ።

How to Use Tor 12

የቶር ብራውዘርን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያስጀምሩት አስፈላጊ ከኾነ አንዳንድ መዋቅሮችን መቀየር የሚያስችልዎ መስኮት ይመጣልዎታል። አንዳንድ መዋቅሮችን ተመልሰው መቀየር ሊያስፈልግዎት ይችላል። ለአሁን ግን ይቀጥሉ እና ኮኔክት የሚለውን አዝራር ጠቅ በማድረግ ከቶር አውታረ መረብ ጋር ለመገናኘት ይሞክሩ።

How to Use Tor 13

ኮኔክት የሚለውን አዝራር ጠቅ ካደረጉ በኋላ እንደ ቶር ሶፍትዌር የአጀማመር ሂደት መጠን አብሮ እያደገ የሚሄድ አራንጓዴ አሞሌ ያለው አዲስ መስኮት ይከፈታል።

How to Use Tor 14

የቶር ብራውዘር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጀምር ከተለመደው ትንሽ ሊዘገይ ይችላል። ነገር ግን ትዕግስተኛ ይሁኑ። ከትንሽ ደቂቃ በኋላ ቶር ብራውዘር መክፈቱን ይጨርስ እና እንኳን ደስ አለዎት የሚል የቶር ድር መዳሰሻ ይከፈትልዎታል።

How to Use Tor 15

JavaScript license information