የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃል

የማለፊያ ቃል አብዛኛውን ጊዜ በከፊል ቋሚ ነው። አንዴ ካዋቀሩት እስኪቀይሩት ወይም መልሰው እስኪያዋቅሩት ድረስ መጠቀም ይችላሉ። የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃል የሚያገለግለው ለአንዴ ብቻ ነው። አንዳንድ የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃል ስርዓቶች የሚሠሩት በርካታ የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃሎችን መፍጠር የሚችሉ መሣሪያዎችን ወይም ፕሮግራሞችን በመጠቀም ነው። እነዚህን የአንድ ጊዜ የማለፊያ ቃሎች ተራ በተራ መጠቀም ይችላሉ። ይህ የሚጠቅመው የማለፊያ ቃልዎን ማስገባት ባለብዎት ስርዓት ውስጥ የቁልፍ መዝጋቢ እንደተጫነ ከጠረጠሩ ነው።

JavaScript license information